አንሙት አብርሐም
ተቋምን ማመን ስለምፈልግና መሆን ስለሚገባው በፍትሕ ጉዳይ እሰሩ ፍቱ የሚል ንቅል አቋም አራምጄ አላውቅም!ውሳኔው በግለሰብና አክቲቪስት የሚመራ ተቋም ነገ የጋራ ቀውስ ስለሚወልድ! ስለሆነም ፎቶ እየሰቀልኩ እገሌን ፍቱልን የሚል ነገር ላይ የለሁበትም! አንዳንድ የልጅና የጅል ነገር ግን ይገጥማል!
አስራት ቴቪ በሐጫሉ ሁንዴሳ ግድያ ዙርያ አንዲት ዘገባ አልሠራም! ጣቢያው ተዘግቶ ነበር። ሠራተኞቹም ስራ ፍለጋ ላይ ነበሩ።
መንግስት በአርቲስቱ ሞት ምክንያት በጀመረው ጅምላና የእስር ኮታ ምክንያት ግን ጋዜጠኞቹ እስርቤት ናቸው። አሁን ክሱ “አማራ ተበደለ እያላችሁ ትዘግቡ ነበር” ሆኗል።
አማራ ለሶስት አሠርት አመታት ዘር ማጥፋት ሲፈፀምበት ዝም ማለት ነው ወንጀል!! ሕግ ጠፍቶ እንጂ በዘር ማጥፋት የሚከሰስ ሞልቷል!
የዘር ማጥፋት ጥሪ ያቀረቡት የOMN , DW እና ትግራይ ቴቪ ጋዜጠኞች ግን ዛሬም በኦሮሚያ ሰልፍና መንገድ ይዘጋ እያሉ ጥሪ እያቀረቡ ነው። በአንድ አገር እየኖርን! ልዩነታችን ሐሞት ያለው ተቆርቋሪ ጉዳይ ብቻ ነው!

በየNGO እየዞሩ የሰብዓዊ መብት ጠበቃ መስለው ይናገሩ የነበሩት እነዳንኤል በቀለ ÷ መዓዛ አሸናፊ ÷ ወዘተ ወድቀዋል!!በኢትዮጵያ የማሟያ የኮታ እስር በመዓዛ አሸናፊ ዘመን እንደነበረ ታሪክ ይመዘግበዋል!