>
5:13 pm - Monday April 19, 8686

የተራራ ሌቦቹ ምርጫ! (ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው)

የተራራ ሌቦቹ ምርጫ!

ጋዜጠኛ ጌታቸው ሽፈራው
የፌደራል መንግስቱ ይህን ሕገ-ወጥነት ዝም ብሎ ማየት የለበትም፤
– አብንና አዴፓ እነዚህን የተራራ ሌቦች በተለያየ መንገድ ማጋለጥ አለባቸው፤
– አክቲቪስቱ ትህነግና ጫጩቶቹ የሚያደርጉትን እንዲሁ መመልከት የለበትም!
—-
ወልቃይትና ራያን በኃይል የያዘው ትህነግ/ሕወሓት ይህ አልበቃው ብሎ በትምህርት ስርዓቱ ራስ ደጀን ተራራ የትግራይ ነው ብሎ አስተምሯል። መተማን አልፎ እስከ ቤንሻንጉል የሚደርስ ካርታውን በኢቲቪ አስተላልፏል። በተለያዩ ጊዜያት የተለያዩ ግዛቶቹ በኃይል ተከልለውና ተቀንሰው “አማራ ክልል” ከተባለውም ተጨማሪ ሌሎች ግዛቶችን ለማጠቃለል ጥሯል።
ትህነግ/ሕወሓት ይሄን አላማውን በይፋ ማራመድ ሲያቅተው የወጣት ሊግ አባላቱን ተቃዋሚ ፓርቲ እንዲመሰርቱ አድርጎ ከወልቃይትና ጠገዴ ባሻገር ከአማራ ክልል የሚያስበውን ግዛት አጠቃልሎ በትግራይና በድምፀ ወያነ ቲቪዎች በምርጫ ቅስቀሳ እያስተላለፈ ነው። ከስር ያለው ካርታ ነፃነት የተባለው የትህነግ የወጣት ሊግ በተቃዋሚ ፓርቲ ስም የትህነግን አላማ የትግራይ መንግስት በሚያስተዳድራቸው ቲቪዎችና በፌስቡክ ገፁ በፕሮፖጋንዳ መልክ እያሰራጨ ነው።
ይህ  ካርታና ፕሮፖጋንዳው የትግራይ ምርጫ ላልገባቸው ጥሩ ማሳያ ነው። የዚህ ፕሮፖጋንዳ አላማ ወልቃይትና ጠገዴን በሕጋዊ መንገድ ሊያጡ ሲሆን “ሌላም አለን” ብሎ ማሳሳቻ ብቻ አይደለም። ትህነግ በስልጣን ዘመኑ ያላሳካውን መስፋፋት ሀገር መስርቸ እፈፅመዋለሁ እያለ ነው። ምርጫው የመስፋፋት መሆኑን ማሳያ ነው።  ምርጫው ምርጫ ሳይሆን በኃይል ከያዘው አልፎ ሌላም እፈልጋለሁ የሚል የትንኮሳ መሆኑን ነው። ከምርጫ በኋላ ሀገር መስርተን የአማራ ክልልን ወርረን እንይዛለን እያሉን ነው። ትህነግ/ሕወሓት ትንኮሳ አላደረገም የሚሉ ከዚህ የምርጫ ቅስቀሳ መረዳት አለባቸው!
በሌላ በኩል ግን ትግራይ ውስጥ ምርጫ እንሳተፋለን የሚሉትን ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ እውቅና ሰጥቷቸዋል። በምርጫ ቦርድ እውቅና ያገኘ ፓርቲ መንግስት አስጠብቀዋለሁ የሚለውን የፌደራል ስርዓትና ክልል አፍርሶ የራሱን ክልል ካርታ ሰርቶ የማቅረብ መብት የለውም። መንግስት የሚባል በሚቆጣጠረው ሚዲያ መሰል ካርታ ቀርፆ ፕሮፖጋንዳ የማስተላለፍ መብት የለውም።   የትግራይ ምርጫ ሕገወጥ ነው። ከዚህ ሕገወጥነቱ ባሻገር ሌላውን የኢትዮጵያ ክፍል ከልሎ የእኔ ነው የሚልበት ሲሆን ዝም ሊባል አይገባውም። እነዚህ የለየላቸው የተራራ ሌባዎች ዛሬም የግዛት ሌብነት ላይ ነው ያተኮሩት። የምርጫው አላማም ይሄው ነው። የአማራ ክልል መንግስትና የሚመለከታቸው አካላት ይህን የትንኮሳ ቅስቀሳ ለሕግ ማቅረብ አለባቸው። እነዚህ የተራራ ሌባዎች፣ እነዚህ መርከብ የሰረቁ፣ እነዚህ ግድብ የበሉ፣ እነዚህ ህንፃ ተሰርቷል ብለው የበሉ አጋሰስና ለቁማጣዎች ሕግ ባይገዛቸውም ባለው የሀገር ሕግ ምን እየሰሩ እንደሆነ ማስመዝገብ ያስፈልጋል።
ሌሎችን የአማራ ግዛቶች ብቻ ሳይሆን ወልቃይትና ራያን በሕግም በሌላም መመለሳቸው የማይቀር ነው።  ለሞቹን የአማራ ግዛቶች መልሰው የለመዱትን ጭንጫ መሬት አቅፈው የሚያለቃቅሱበት ጊዜ ሩቅ አይደለም። እስከዛ ግን እየዘለሉ የሚስሉት ካርታ ሕገወጥ መሆኑን በፌደሬሽን ምክር ቤት፣ በምርጫ ቦርድና በሌሎች ተቋማትም ሊያስጠይቃቸው ይገባል!
የፌደራል መንግስቱ ይህን ሕገወጥነት ዝም ብሎ ማየት የለበትም። አብንና አዴፓ እነዚህን የተራራ ሌቦች በተለያየ መንገድ ማጋለጥ አለባቸው። አክቲቪስቱ ትህነግና ጫጩቶቹ የሚያደርጉትን እንዲሁ መመልከት የለበትም!
(ይህ ምስል በቪዲዮ በትግራይ ቲቪና በድምፀ ወያነ የምርጫ ቅስቀሳ ላይ እየተላለፈ ይገኛል። ነፃነት በሚባለው የትህነግ የወጣት ሊግ “ፓርቲ” ገፅ ላይም ይገኛል።)
Filed in: Amharic