ቀረርቶና ፉከራ አሁን ነው…!!!
ፕሮፌሰር መስፍን ወልደማርያም
አሜሪካ በአንድ መቶ ሠላሳ ሚልዮን ዶላር የኢትዮጵያን እጅ መጠምዘዝ ወሰነች የሚል ወሬ ሰማሁ፤ እቴጌ ጣይቱ ከመቃብር ይጣራሉ፡ የወንድ ያለሁ እያሉ! ዱሮውንም ቢሆን የሰው ጥገኛ መሆን አያስተማምንም፤ አንድ መቶ ሠላሳ ሚልዮን ቀርቶ አምስት መቶ ተሪልየን ቢሆን የአባቶቻችንን ውርስ፣ ነጻነጻችንን፣ ኩራጻችንንና ክብራችንን አንሸጥም፤ በፍርፋሪ የያዟቸውን ስደተኞች እንደኢትዮጵያውያን መለኪያ ቆጥረው ከሆነ በጣም መሳሳታቸውን እናረጋግጥላቸው፤ አሁን ነው ፉከራ! አሁን ነው ቀረርቶ! እርስበርሱ ሥጋን በኩበት ይጠብሱ! የያዙትን መሸጦ ኩበት ሌላ ይጥበሱበት፡፡
NB: ኢትዮጵያዊ ኩበት የኢዮጵያን ሥጋ አይጠብስም!