>

የቢፍሾቱ ከተማ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌውን  በነፃ አሰናበታቸው ....!!!! (የሸገር ራድዮ)

የቢፍሾቱ ከተማ ፍርድ ቤት አቶ ልደቱ አያሌውን  በነፃ አሰናበታቸው ….!!!!

የሸገር ራድዮ


የቢፍሾቱ ከተማ አንደኛ ደረጃ ፍርድ ቤት የኢዴፓ መስራችና የስራ አስፈፃሚ አባል የሆኑት አቶ ልደቱ አያሌው በተከሰሱበት ጉዳይ ምንም የሚያስጠይቃቸው ነገር እንዳላገኘ በመግለፅ በነፃ እንዳሰናበታቸው ተሰማ፡፡

ሸገር የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ ሊቀ መንበር የሆኑትን አቶ አዳነ ታደሰን በስልክ አነጋግሮ አቶ ልደቱ ተጠርጥረው ለእስር የተዳረጉበት የፍርድ ቤት መዝገብ መዘጋቱን አረጋግጧል፡፡ ፍርድ ቤቱ አቶ ልደቱ ከፖሊስ ጋር ያላቸውን ጉዳይ ጨርሰው እንዲለቀቁ ማዘዙን ሸገር ከአቶ አዳነ ሰምቷል፡፡

አቶ ልደቱ አያሌው የድምፃዊ ሀጫሉ ሁንዴሳን ግድያ ተከትሎ በቢሾፍቱ በተፈጠረው ረብሻ አመፅ በማነሳሳትና በገንዘብ በመርዳት በሚል ጠርጥሬአቸዋለሁ ባለው የቢሾፍቱ ከተማ ፖሊስ አዲስ አበባ ውስጥ በቁጥጥር ስር ውለው በፍርድ ቤት ጉዳያቸውን ሲከታተሉ መክረማቸው ይታወቃል፡፡

Filed in: Amharic