>

አመድ በዱቄት ይስቃል . . .! (አሳፍ ሀይሉ)

አመድ በዱቄት ይስቃል . . .!

አሳፍ ሀይሉ

 

* …ዓይን ያወጣ ዘረኛ አምባገነን ስለ ትግራዮች ምርጫ እየተሳለቀ፣ ስለ ወያኔዎች የአዕምሮ ድርቀት እየተሳለቀ አስተያየት የመስጠት የሞራል ብቃት የለውም! 
የአዲሳባን ሕዝብ ራሱን የማስተዳደር መብት አፍኖ፣ የቡራዩን የቄሮ ጭፍጨፋ ለማውገዝ ሰልፍ ለምን ወጣህ ብሎ ባደባባይ ሰው በስናይፐር ያስረሸነ፣ ሺህ ወጣቶችን ወደ እስር ያጋዘ፣ እነ እስክንድር ነጋን ለምን ተናገራችሁ ብሎ እስርቤት የጨመረ፣ በሀገር በምድሩ የቄሮ ሜንጨኞች ከተሞችን እያዘጉ እንዲያወድሙና የሰውን ልጅ እንዲዘለዝሉ  ከጀርባ ቆሞ ያበረታታ፣ በቀን ብርሃን የአዲሳባን 95 ሺህ መኖሪያ ቤቶች ለኦሮሞ ዘር መርጦ ያደለ፣ ዓይን ያወጣ ዘረኛ አምባገነን፣ ስለ ትግራዮች ምርጫ እየተሳለቀ፣ ስለ ወያኔዎች የአዕምሮ ድርቀት እየሰለቀ አስተያየት የመስጠት የሞራል ብቃት የለውም!
እሱስ ማን ሆኖ? ሠላም በሌለበት ሀገር የሠላም ኖቤል የተሸለመ የፈረንጅ መሳቂያ አሻንጉሊት አይደለም ወይ ሲጀመር? ፈረንጆቹ ሲተርቱ “A pig in the parlor is still a pig” ይላሉ። “አሳማን ሳሎን ውስጥ ብታስቀምጠው ያው አሳማ ነው፣ አሳማነቱ አይቀየርም” እንደማለት። ጠባብ ዘረኛን፣ እና ጭንቅላቱም ዓይኑም የደረቀን የሥልጣን አሳማ፣ ቤተመንግሥት ውስጥ አስቀመጥከውም፣ ዱክትርና ጫንክለትም፣ ኮሎኔልም ብለህ ሰቀልከው፣ ኖቤልም አሸከምከው… – still, a pig is always a pig – ያው አሳማው አሳማነቱን አይቀይርም! ሌላ ምንም መጠሪያ ቋንቋ የለውም። “አመድ በዱቄት ይስቃል” ነው ነገሩ።  እውነቱ ይሄው ነው!
ሲጀመር “ፊንፊኔ፣ ኦሮሚያ፣ ክልል፣ የቤር ቤረሰቦች ሕገመንግሥት”፣ ገለመሌ እያለ የሚያነበንባቸውን ቃላትና፣ በትልቁ አሰርቶ እየተደገፈ በካሜራ የሚቀረፅበትን አምባሻ የመሰለ ትልቅ የባንዲራ ኮከብ ከነሚኒስትርነቱ ማን ቀብቶ ሸለመውና? የዕድሜውን 80 % የወያኔ ታማኝ ጋሻጃግሬ ሆኖ ሲያደገድግ፣ ከነ አቦይ ስብሃት ሥር እየተልከሰከሰ ለስልጣን ደጅ ሲጠና የኖረ የወያኔ ጆሮጠቢ አይደለም ወይ? አናውቀውም እንዴ?! “ጅብ በማያቁት ሀገር ሄዶ፣ ቁርበት አንጥፉልኝ አለ” እንደተባለው ሆነ እኮ ነገሩ። ይሄኛው ደሞ ይባስ። በሚያውቀው ሀገር ላይ ቆሞ እኮ ነው ቁርበት አንጥፉልኝ የሚለው።
እና አሁን ጠቅላዩ ከኡማዎቹን አቤቤዎቹ ጋር ተግቶ የፊንፊኔን ዲሞግራፊ እያስቀየረ፣  መናፈሻ ላይ ፋውንቴን ፊን ፊን እያረገ፣ ዳቦ እያደለ፣ ጫማ እየጠረገ፣ ችግኝ እየተከለ፣ ውሃ እያጠጣ፣ ማስክ እያደለ፣ በቲቪ ቀርቦ የአሽሙር ቃላት እየወረወረ፣ ሀገር ምድሩን በሆድአደር ካድሬ ጠቅጥቆ መላወሻ መተንፈሻ አሳጥቶ የኦሮሙማ ቁማሩን እያስቆመረ፣ በቃ… ኢትዮጵያን ወርቅ አድርጎ እያስተዳደረ ነው ማለት ነው? በቃ ሀገር አማን ተሆኖ አበቃ? … ለመሆኑ በቀጣይ የትኛው መናፈሻ ይሆን የሚመረቀው? አይ ሀገር!
“ሀገሬ ኢትዮጵያ ሞኝ ነሽ ተላላ
የሞተልሽ ቀርቶ የገደለሽ በላ”
መልካም ጊዜ!
ኢትዮጵያ ለዘለዓለም ትኑር!
Filed in: Amharic