>

የጳጉሜ ምህረት ሊጎበኛቸው የሚገባ አዛውንቶቹ የቀድሞው መንግስት ባለስልጣናት!!! (ጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ)

የጳጉሜ ምህረት ሊጎበኛቸው የሚገባ አዛውንቶቹ የቀድሞው መንግስት ባለስልጣናት!!!

ጴጥሮስ አሸናፊ ከበደ

* ይፈቱ ይበቃል! ለነሱ ሲሆን ይቅርታ ተቀርቅሮ እንቅርት አይሁን፥ ወደ ቤተሰባቸው ይመለሱ- 30 አመት ይበቃል‼️
ላለፉት 29 ዓመታት አዲስ አበባ ቤላ አካባቢ በሚገኘው የጣሊያን ኢምባሲ በቁም እስር ላይ የሚገኙት ከፍተኛ የደርግ ባለስልጣናት
የ84 ዓመቱ አዛውንት ሌተናል ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህና የ76 ዓመቱ ሌተናል ጄኔራል ሀዲስ ተድላ የጳጉሜ ምህረት ሊጎበኛቸው ይገባል።
ሌተናል ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህ በመጨረሻዎቹ የደርግ የስልጣን ዘመናት፣ የመንግሥት ምክር ቤት ምክትል ፕሬዚዳንት የነበሩ ሲሆን፤ ሌ/ጀኔራል ሀዲስ ተድላ በበኩላቸው የጦር ሃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም እንደነበሩ ይታወቃል፡፡
ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አህመድ በ2010 ዓ/ም በሚሊኒዬም አዳራሽ በተዘጋጀ አንድ  መንፈስ አነቃቂ ፕሮግራም ላይ “በኤምባሲ ውስጥ ታስረው የሚገኙ የቀድሞ መንግሥታት ከፍተኛ ባለስልጣናት ይቅርታ አድርገንላቸው ሊወጡ ይገባል” ማለታቸው የሚታወስ ነው፡፡ ቢሆንም ንግግራቸው ከ2 ዓመታት በኋላም ተግባራዊ አልተደረገም።
በህይወታቸው የመጨረሻ ዘመን ላይ በቤተሠብ ናፍቆት፣ ረኃብና በበሽታ በመሠቃየት ላይ የሚገኙት የአቢዮታዊው ጦር ሰራዊት ኤታማጆር ሹም ሌ/ጄ ሀዲስ ተድላና የውጭ ጉዳይ ሚንስትር ኮሎኔል ብርሃኑ ባየህ የጳጉሜ ምህረት እንዲጎበኛቸውና የቀረቻቸውን ጥቂት ዕድሜ ከቤተሰቦቻቸው ጋር እንዲያሳልፉ ይሁን !
CC: Office of the Prime Minister-Ethiopia
      FDRE Attorney General የኢፌዲሪ ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ
Filed in: Amharic