>

ኢትዮጵያ ያለባት መሠረታዊ ችግር የወታደሮች አቅም ሳይሆን ልጓም ነው...!!! (ስዩም ተሾመ)

ኢትዮጵያ ያለባት መሠረታዊ ችግር የወታደሮች አቅም ሳይሆን ልጓም ነው…!!!

ስዩም ተሾመ

 

ቤተመንግሥት ውስጥ ሊያውም ካሜራ ፊት ወታደሮች ሲንፈራገጡ ማየት ያስጠላል‼️
ወታደር በተመደበበት ቦታ ላይ ሥራውን ሲሰራ እንጂ ቤተመንግሥት ውስጥ ሲንፈራገጥ ማየት አይመቸኝም። የህዝብን ሰላምና ደህንነት እንዲጠብቅበት የታጠቀውን የጦር መሣሪያ ይዞ ከካሜራ ፊት ሲውተፈተፍና ሲያቅራራ ማየት ያስጠላኛል። ይህ የሆነው መቀሌ ሆነ አዲስ አበባ አሊያም ካይሮ ለእኔ ልዩነት የለውም‼️ ዛሬ ቤተመንግሥት ውስጥ የታየውን ትዕይንት #ወያኔ ትግራይ ውስጥ በእየለቱ የሚያደርገው ቢሆንም አሊያም ደግሞ “ትዕይንቱ እንደ ግብፅ ላሉ የጠላት ሃይሎች ወታደራዊ አቅምና ዝግጅትን ለማሳየት ነው” ቢባልም ስለ ጉዳዩ ያለኝን አመለካከት አይቀይረውም።
ኢትዮጵያ ያለባት መሠረታዊ ችግር የወታደሮች #አቅም ሳይሆን #ልጓም ነው። አቅሙን ማሳየት የሚፈልግም ከሆነ በየግዜው የሚከሰቱ ግጭቶችን ቀድሞ በመግታት ማሳየት ይችላል። አሊያም ደግሞ ከሰሞኑ በአፋርና ኦሮሚያ ላይ ለጎርፍ አደጋ የተጋለጡ ዜጎችን በመርዳት በተግባር ችሎታውን ማሳየት ይችላል። ነገር ግን መሃል ከተማ፣ ያውም ቤተመንግሥት ውስጥ በቴሌቪዥን የቀጥታ ስርጭት ወታደሮች ሲዘሉና ሲራገጡ ማየት ያስጠላኛል‼️ ይኼው ነው‼️
Filed in: Amharic