>

አሁንም የሽብርተኝነት ክስ? አሳፋሪ የታሪክ ቅብብሎሽ !?! (አቻምየለህ ታምሩ)

አሁንም የሽብርተኝነት ክስ? አሳፋሪ የታሪክ ቅብብሎሽ !?!

አቻምየለህ ታምሩ

የፌደራል ጠቅላይ ዐቃቤ ሕግ እስክንድር ነጋን ጨምሮ 7 ግለሰቦችን በሽብር እና የእርስ በርስ ግጭት መቀስቀስ በሚል የፈጠራ ክስ መስርቶባቸዋል…!!!
 
እስክንድር ነጋ ለኢትዮጵያ ሕዝብ አንድነትና እኩልነት እድሜ ልኩን ሲደክም የኖረ  ዓለም የመሰከረለት የሰላም ሰው ነው። የእስክድር ነጋ ጥፋት በዐቢይ አሕመድ የአፓርታይድ አገዛዝ ድጋፍ እየተካሄደ ያለው የዘር ፍጅት አስቀድሞ የታየው መሆኑና በዐቢይ አሕመድ መሪነት እየተካሄደ ያለውን አዲስ አበባን የመሰልቀጥ የኦሮሙማ ፕሮግራም በግንባር ቀደምትነት መቃወሙ ብቻ ነው።
ከዚህ ውጭ በእውነተኛ ሕግ ፊት በግፍ የሽብር ክስ ከመሰረተበት ከሰላሙ ሰው ከእስክንድር ነጋ  ብቻ ሳይሆን ወንጀለኛ እያለ ከሚከሳቸው ሰዎች ሁሉ የከፋው  ወንጀለኛ ኢትዮጵያ ውስጥ የቆመው የወንጀል ሥርዓት ቁንጮ የሆነው ዐቢይ አሕመድ ነው። የዛሬ የግፍ ፍርድ ወንጀለኛው  እስክንድር ነጋ ግን  የግፍ ፍርድ እንዲበየንበት ትዕዛዝ ከሚሰጠው ከዐቢይ አሕመድ በላይ የነገ ባለታሪክ ነው።
Filed in: Amharic