>

በቅዱስ አባታችን መነገድ ይቁም!!! (ብርሀኑ ተክለያሬድ)

በቅዱስ አባታችን መነገድ ይቁም!!!

ብርሀኑ ተክለያሬድ

* ….የማይናገሩ (አርምሞ ላይ ባሉ) ፓትርያርክ ፊት የሚሰራ ድራማ ና ደባ…!!!

 
-የምናውቀው 2 ፓትሪያርኮች እንዳሉን ነው!
-የምናውቀው “እኔ ቤተክርስቲያን አላቃጠልኩም ይቅርታ አልጠይቅም፣ ካሳም አልከፍልም” ብለህ ያባረርካቸውን የቅዱስ  ሲኖዶስ አባላቶችን ነው!
-የምናውቀው በጥቅምት እና በሰኔ እኛ ኦርቶዶክስ ተዋህዶዎች በዘግናኝ ሁኔታ ስንታረድ ባልሰማ ዝም ማለትህን ነው! 

አብይ በቅራቅንቦ አታታልለንም::…!!!

 
ይህ ጉብኝት ግሁሱና ሁሉ ነገራቸውን ከሰው ነጥለው ለእግዚአብሔር ከሰጡት ከባህታዊው ቅዱስ አባታችን አቡነ መርቆሬዎስ እውቅና ውጪ የተደረገ ጭልጥ ያለ ንግድ ነው። ደግሞም “አስታርቄ አንድ አደረግኳት” ያሏትን ቤተ ክርስቲያን “ለኔ ካልተገዛች ትራበሽ” የሚል እቅድ እንደ መግቢያም ነው።

ነገሩን እናፍታታው?

ይህ ጉብኝት እንዲደረግ የወጠኑ 2 አካላት አሉ
የመጀመሪያው የኦርቶዶክሳውያንን ሞትና ስቃይ በዝምታ ያለፉ፣ከጥቃቶቹ ጀርባ የነበሩ፣ ጥቃቱን በሚዲያ ስንዘግብ እንኳን “አጋነናችሁት” ብለው የተመፃደቁ ከቤተክህነት እስከ ቤተ መንግሥት ያሉ ሸቃጮች ጠቅላይ ሚኒስትሩን አመስግነው ጩኸታችንን የቁራ ጩኸት ለማድረግ የወጠኑት እቅድ ነው።
ሁለተኛው
የብፁዓን አባቶች መጠንከርና ወቀሳ ማሰማት ያልተዋጠላቸው ጠቅላይ ሚኒስትር በቅዱስነታቸው ድንገቴ ጉብኝት ሽፋን “እነ እከሌ ከኔ ጋር ናቸው። እነ እከሌ ደግሞ የነእከሌ አጀንዳ አስፈፃሚዎች ናቸው” የሚል ጨዋታ ለመጫወትና በየቃለመጠይቁ አስታረቅኩት እያሉ የሚመፃደቁበትን ቅዱስ ሲኖዶስ በድጋሚ የኛና የነሱ ብሎ ለመክፈል የታለመ የመጪ ዘመን እቅድ ነው።
ድርጅትንና ግለሰብን ከተጠያቂነት ለማትረፍ ሲባል የኦርቶዶክሳውያን ሰቆቃ እንዲቀጥል የሚያደርግና አንድነታቸውንም የሚፈታተን አደጋ እየመጣ መሆኑን ስንመለከት “ካሳለፍነው ይልቅ የሚቀረን ይበልጣል” እንድንል ያስገድደናል።
ከሁሉ በላይ የሚያበሳጨውና የሚያሳዝነው ራሳቸውን ከሰው ነጥለውና ከአምላኬ ጋር ብቻ እነጋገራለሁ ብለው ያሉትን ቅዱስ አባታችንን አርምሞና የዋህነት እኩያኑ የድራማው አካል ማድረጋቸው ነው።
ንቃህ መዋቲ!!!
Filed in: Amharic