>

ፍጹም ሰላማዊው ሰው እስክንድር "አሸባሪ!" ከተባለ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድም ሰላማዊ ሰው የለም!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ፍጹም ሰላማዊው ሰው እስክንድር “አሸባሪ!” ከተባለ ኢትዮጵያ ውስጥ አንድም ሰላማዊ ሰው የለም!!!

ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

 

* እስክንድር በፈጠራ ክስና በሐሰተኛ ምስክርነት በአሸባሪነት የተከሰሰበት ምክንያት አገዛዙ የኢትዮጵያን ሕዝብ “እስክንድርን እንድንፈታላቹህ ከፈለጋቹህ የእነ ጃዋርን መፈታትም ተቀበሉ!” ብሎ ለመደራደሪያነት  እንደ መያዣ እጠቀምበታለሁ ብሎ ነው በፈጠራ ክስና በሐሰተኛ ምስክርነት ይህ የአሸባሪነት ክስ ሊመሠረትበት የቻለው!!!
 
እንደፈራሁት የሰብአዊ መብት ተሟጋቹን፣ ከግፉአን ጋር ሲያለቅስ የሚውለውን ጋዜጠኛ እስክንድር ነጋ የሽብርተኝነት ክስ ተመሥርቶበት ለወያኔው  ዐቢይ አሕመድ መያዣ ሆኗል!!!
በክሱ ላይ የሰፈረውን ክስ አይደለም ሌላ ሰው የእስክንድር ጠላቶች እንኳ እራሳቸው እስክንድርን “ያደርጋል!” ብለው እንደማያምኑ ቅንጣት ታክል አልጠራጠርም!!!
ይሄ የእስክንድር ክስ እነ  ዐቢይ ለራሳቸው እንኳ ፈጽሞ እንደማያስቡና ለሞራልም ሆነ ለሃይማኖታዊ እሴቶች ዋጋ የማይሰጡ፣ ፍጹም ክብርም የሌላቸው መሆናቸውን ነው ያረጋገጠልኝ!!!
ፍጹም ሰላማዊው ሰው እስክንድር ነጋ “አሸባሪ!” ከተባለ እነሱ ምን ሊባሉ ነው በሞቴ??? ለራሳቸው እንኳ አያስቡም እንዴ እነኝህ ንኮች???
እስክንድር በፈጠራ ክስና በሐሰተኛ ምስክርነት በአሸባሪነት የተከሰሰበት ምክንያት አገዛዙ የኢትዮጵያን ሕዝብ “እስክንድርን እንድንፈታላቹህ ከፈለጋቹህ የእነ ጃዋርን መፈታትም ተቀበሉ!” ብሎ ለመደራደሪያነት ነው መያዣ አድርጎ በፈጠራ ክስና በሐሰተኛ ምስክርነት ይህ የአሸባሪነት ክሱ ሊመሠረትበት የቻለው!!!
የኢትዮጵያ ሕዝብ ሆይ! በተለይም አንተ በሞቀ ቤትህ እየኖርክ እስክንድርን የበፊቱ መከራውና የግፍ እስሩ ሳይበቃው ከሚወደው ልጁና ከሚወዳት ባለቤቱ ናፍቆቱን ሳይወጣ ነጥቀህ “ተሟገትልን፣ ታገልልን፣ የጉዳያችን ባለ አደራ ሁንልን!!!” ብለህ ኃላፊነት አሸክመህ ከዚህ ፈተና ውስጥ የከተትከው የአዲስ አበባ ሕዝብ ሆይ! ዛሬም እንደትናንትናው እስክንድርን አሳስረህ ዝም ልትል ነው ወይስ የእስክንድርና የሌሎቹ ንጹሐንና ፍጹም ሰላማዊ ጓዶቹ በግፍ መታሰር ያንተ ጉዳይ ያለቀለት፣ የሞተለት፣ የተፈጸመለት ነገር የመሆኑ ማሳያ ወይም ማረጋገጫ ምልክት መሆኑን ተረድተህ “እንዲህ ከሆነማ ለምኑ ብየ ነፍሴን እሰስታለሁ???” ብለህ በአልሞት ባይ ተጋዳይነት ወኔና ስሜት የመጨረሻ ፍልሚያህን በጠላትህ በአገዛዙ ላይ ታደርጋለህ???

“አሸባሪው” ጀግና!!!

 
እስኬው የእኔ ጌታ፣ የወንድነት ውሐ ልክ፣ የብርታት ተምሳሌት፣ ነዋይ የማያጓጓህ፣ አጎብዳጅ እና ጥቅመኛ ተቃዋሚ ፖለቲከኛ ተብዬዎችን እንድንፀየፍ ያደረግከን የማትውሸለሸል ጀግና። አንተ ማንም ላይደርስብህ ዘጠነኛው ሰማይ ላይ ተሰቅለሀል። ኮቴህ 30 ዓመት መንግሥትን አርበድብዷል፤ እያርበደበደም ነው። ሕወኃታዊ ድራማ ለመቀጠሉ ማሳያ አንተ ነህ። ስለሚፈሩህ “አሸባሪነትን” ይሸልሙሀል። ኢትዮጵያ ውስጥ “አሸባሪ” ለጀግና የሚሰጥ ሽልማት ነውና አይዞህ ወንድሜ! አይዞን ለእኛ! አይዞን ለአዲስ አበባ!
Filed in: Amharic