>

ግርማዊ ጃንሆይ ይማሩን...!!! (አልማዝ ጣሰው መኮንን)

ግርማዊ ጃንሆይ ይማሩን…!!!

አልማዝ ጣሰው መኮንን

ደጉ የሰላሙ መሪ ንጉሳችን ግርማዊ ቀዳማዊ ኃይለስላሴ ሆይ  የእንባ እርግማንዎን እባክዎ በዚህ አዲስ አመት ያንሱልን !
43 አመት ካለምንም ምክንያት እርስ በርስ ተባላን  ኢትዮጵያ የመጣ መሪ  ቢመጣ አልረጋ አልገዛ  ብላ አስቸገረች  ህዝቡም እምነት ፍቅር   ስምምነት  አጣ  ::
ንጉስ ሆይ ይማሩን ይቅርም ይበሉን !
   ዓመቱ የሰላም የጤና የፍቅር የብልፅግና  እንዲሆንልን እባክዎ  በእንባ  የታጀበው እርግማንዎትን  ከኛ ከህዝብዎ   ላይ ያንሱልን  በቃችሁ ልጆቸ ብለው ከልብ ይማሩን ::
      እኛም ወጥተን እንግባበት  አምሽተን እንንቃም ወልደን እንሳም ውለን እንግባ ዘመድ ከወገን በፍቅር በመተሳሰብ እንደ  ድሮው  እንደ ጥንቱ እንኑርበት ::
ግርማዊ ሆይ እንሆ አባቴ ይቅር ይበሉን :
   በትራስ አፍነን  ከሆነየገደልንዎ እንሆ በተምች በሽታ መድኃኒት ባልተገኘለት አፍ እና አፍንጫችን አፍነን  እኛም መተንፈሻ አተናል ::  ቆሎ  ባጣ  ሆዳችን  ለእግር ጫማ በሌለው ኑሮአችን በቀን አስር ግዜ እጃችን ከውሃ ጋር ሲጫወት ይውላል ::
ንጉስ ሆይ ይማሩን !
በግፍ  ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርካችንን እና ባለሥልጣኖችዎን  ገለን እኛም እርስ በእርስ  ቀይ ሽብር ነጭ ሽብር እያልን የሞት ብልት እያወጣን እርስ በርስ ተላልቀናል::ግርማዊ ሆይ  በዚህም አላቆምንም  በዚህ በሰለጠነው ዘመንም በሜንጫ እየተፋለጥን  ተዘቅዝቀን አየተሰቀልን በመቶ አስር አመት ታሪክ እየተናቆርን አንተ ትብስ አንች ትብሽ ቀርቶ የታባህ የታባሽ ነግሶ  : ፍርድ እርትእ ጠፍቶብን ፍርድ ቤት ሲፈታ  ፖሊስ እያሰረ  እንሆ 43 አመት አስቆጠርን::
እባክዎ ግርማዊ ሆይ በነበርዎት የድሮ የህዝብዎ ፍቅር ሲሉ ዘንድሮን  ይማሩን !
አዲስ አመት ወንዱ ሴቱ ትልቁ ትንሹ ወጣት አዛውንቱ እንደየ እምነቱ  ነጭ ለብሰን ደምቀን አምረን  አሮጌ  አመት አልፎ አዲስ አመት ሲተካ  እግዚአብሔርን ሊያመሰግን በመንገድ ላይ ሲተራመስ  ይታይ ነበር ::
በተለይ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ውበትዋ ይህ  እለት ነበር ::እንዲሁም አኑዋር መስጌድ
አሁንማ ንጉስ ሆይ እርግማንዎ  እንሆ  የእምነት አባቶቻችንን ወደውስጥ አስገብቶ እኛው ሃጤያተኛ ልጆችዎን ሌባ ሌባ  ሌባ  ባልንበት አፋችን ተለጉመን ቤተክርስትያን እንዳንደርስ  ሁነናል
እሬሳችንም  ለጥንብ አንሳ ከተሰጠን ሰነባበትን ፍትሃት አይታሰብም  እናማ  !
ደጉ መሪያችን ግርማዊ ሆይ እባክዎን ይማሩን !
መጭው አመት ቤተ መንግስትዎ  እና ቤተእምነት  ተረጋግቶ ሰላም ፍቅር እምነት አንድነት መዋደድ መከባበር  ትህትና እና ብልፅግና
በሀገራችን በኢትዮጵያ  ሰፍኖ የምናይበት በአለም ዙሪያ  ተበትኖ ያለው ኢትዮጵያውያን ለሀገራቸው መሬት የሚበቁበት  የታሰሩ ተፈተው የታመሙ ድነው  ተምች ከአለም ጠፍቶ  ሀገረ ሰላም ኢትዮጵያን  ለማየት  ያበቃን ዘንድ  ንጉስ ሆይ ይማሩን !!!
መልካም አዲስ ዘመን እንዲሆንልን ይቅርታን እናስቀድም ::  ለመላው የኢትዮጵያ ህዝብ በሙሉ እንኳን ለአዲሱ አመት በሰላም በጤና አደረሳችሁ::
Filed in: Amharic