>
5:13 pm - Tuesday April 20, 8466

ትልቁ ችግራችን፦ ጠያቂዎቹ ራሳቸው የማያውቁት "የኦሮም ሕዝብ ጥያቄ" ነው!!! (ወንድማገኘሁ እጅጉ)

ትልቁ ችግራችን፦ ጠያቂዎቹ ራሳቸው የማያውቁት “የኦሮም ሕዝብ ጥያቄ” ነው!!!

ወንድማገኘሁ እጅጉ

 

–  መቼና እንዴት ነው የኦሮሞ ሕዝብ ጥያቄውን የጠየቀው?
–  ጥያቄውስ ምንድን ነው? እንዴት  ነው የሚመለሰው?
– ሕጋዊና ፖለቲካዊ ውክልና ሳይኖራቸው፣ “የኦሮም ሕዝብ ጥያቄ” እያሉ አየሩን ያስጨነቁት ሰዎች በየትኛው የሕግና የሞራል platform ልንሰማቸው የሚገባን?
-ከኦዲፒ እስከ ኦነግ ውስጥ በተሰገሰጉ “ኤሊቶች” ውስጥ “የኦሮም ሕዝብ ጥያቄ” ይሄ ነው የሚል በግልፅ የተቀመጠ ነገር የለም፣ ይልቁንም በየጊዜው እየተለዋወጡ መሰረት በሌለው “የኦሮም ሕዝብ ጥያቄ” ላይ በጥላቻ የተሞላ የፖለቲካ ፕሮፖጋንዳ በመጨመር መሬት መውረርና ሕዝብን እርስ በርስ ከማጫረስ ውጪ ኤሊት ተብዬዎች የፈጠሩት አንድም ነገር የለም!
በ “ኦሮም ሕዝብ ጥያቄ” ትግል ለ40 አመታት፣  20 ሺ ጊዜ እየተሰነጣጠቀ የቆየውን ኦነግ ራሱን  – ለመሆኑ “የኦሮም ሕዝብ ጥያቄ” ምንድን ነው ብላቹህ  ብጠይቁ- መልሱ እንዲህ ነው- “ከተቻለ ራስን በራስ የማስተዳደር መብታችን ተጠብቆ ከሌሎች ብሔር ብሔረሰቦች ጋር ኢትዬጵያ ውስጥ መኖር፣ ካልሆነ ደግሞ መገንጠል” የሚል ግራ የገባው ፣ ቅልጥ ያል ቂላዊ ፖለቲካ፣ ፖለቲካ የማይሸት መልስ ታገኛላቹህ።
በነገራችን ላይ በዚህ የኦነግ መልስ ውስጥ ሁለት ቁልፍ ነጥቦች አሉ፦
1- ወያኔና፣ሻቢያ ለኦነግ በሰጡት አሁን “ኦሮምያ ክልል” እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖሩ ኢትዬጵያኖች መኖር የካደና ልክ እንደ “የጋላ ወረራ” ወቅት ከኦሮሞ ውጪ ያሉትን ማንነቶች የሚሰለቅጥና ሕልውናቸውን የሚክድ ነው።
2- ኢትዬጵያ ውስጥ “ራስን በራስ” አስተዳድሮ፣ የፈለገውን አካባቢ እንዳሻው ወስዶ መኖር፣ የኦሮሞ መብት ብቻ እንደሆነ ታሳቢ ያደርጋል። በሌላ አነጋገር አሁን “ኦሮምያ ክልል” እየተባለ የሚጠራው አካባቢ ውስጥ ሌሎች ኦሮሞ ያልሆኑ ኢትዬጵያን የፖለቲካ፣ማሕበራዊና ኢኮኖሚያዊ ፍላጎት (interest) ሙሉ በሙሉ ይክዳል አልያም አለ ብሎ አያምንም።
ለዚህ ነው ትልቁ ችግራችን- ጠያቂዎቹ ራሳቸው የማያውቁት “የኦሮም ሕዝብ ጥያቄ” ነው። ትክክለኛ መንግሥት ሲመጣ መጀመሪያ መወሰድ ያለበት እርምጃ – ከወያኔ፣ሻቢያና ኦነግ ማኒፌስቶ የተቀዳውን ሕገ-መንግሥት void ማድረግና አሁን “ኦሮምያ ክልል” እየተባለ የሚጠራውን አካባቢ መዋቅር ሙሉ ለሙሉ dismantel ማድረግ መሆን አለበት።
Filed in: Amharic