>

ኦሮሙማ አጀንዳ ባለበት ሁሉ አማራ ይታረዳል...!!! (በመስከረም አበራ) 

ኦሮሙማ አጀንዳ ባለበት ሁሉ አማራ ይታረዳል…!!!

(በመስከረም አበራ)

ቤኒሻንጉል የኦሮሙማ አይን ካረፈባቸው ቦታዎች አንዷ እንደሆነች ኦቦ ሽመልስ መዝሙረ ኦህዴድን ባነበነቡበት አይን ገላጭ ሃተታቸው ነግረውናል። የኦሮሙማ አጀንዳ ባለበት በእዛ አማራ መታረዱ አዲስ ነገር አይደለም። ዛሬ አገውም አብሮ የሚታረደው ደግሞ በአማራው ላይ ፊቱን እንዲያዞር ከተቻለም ጦር እንዲያነሳ ቢጎተጎት በጄ ስላላላቸው ነው። አገውን እና አማራን መነጠል እንደማይቻል ለማወቅ ከተራ የዘውግ ፖለቲካ ምልምልነት ያለፈ ነገር ያስፈልጋል።
የሆነ ሆኖ አማራ እና  አገው በሚያሳዝን መንገድ ማንነታቸውን መሰረት ያደረገ አረመኔነት የወለደው፣ጥላቻ የቆሰቆሰው  እርድ ተፈፅሞባቸዋል። የሰዎቹን አሟሟት የሚያሳዩ ፎቶዎችን ማየት መፈጠርን ያስጠላል።ብአዴን ለዚህ ያለው መልስ የሰላም ኮንፍረንስ የማዘጋጀት ቀልድ ነው።ይህ ለቅሶቤት ገብቶ እንደ መደነስ ያለ በህዝብ ላይ ማፌዝ ነው። ነገ ደሞ ገዳዮችን ባህር ዳር ላይ ጠርተው እንኳን ህዝቤን ገደላችሁልኝ ሲሉ ቀይ ካባ  ያጎናፅፋሉ።
 የሚገርመኝ ነገር ኢትዮጵያን የሚገዙ ነገስታት የብአዴን መሪዎችን ከየት ምድር ፈልገው እንደሚያመጧቸው ነው? እንደ አገኘሁ ተሻገር፣እንደ ተመስገን ጥሩነህ ያለ ሰው ፈልጎ ማግኘት ቀላል ነገር ነው? አሁንም የመፍትሄው መንገድ ህዝብ እነዚህን ሰዎች ከትከሻው ላይ አሽቀንጥሮ መጣል ብቻ ነው!
Filed in: Amharic