>
7:53 am - Friday June 2, 2023

የቲም አብይና የህዋሓት የአማራር ቡዱን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ  (አስገደ ገብረስላሴ)

የቲም አብይና የህዋሓት የአማራር ቡዱን የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ 

አስገደ ገብረስላሴ

 ለግንዛቤ ያህል ፦ያለፉት እና ተከትለው ለሁለት አመት ተኩል  የመጡ የለውጥ ጉዞ   ሲቃኙ ፦ይድረስ ለኢትዮጱያ ህዝቦች በየአላችሁበት በሙሉ ክፍል  4 ከ3/01 /20 13  የዞረ ፤የህዋሓት የአማራር ቡዱንና የቲም አብይ አህመድ የአንድ ሳንቲም ሁለት ገጽታ ናቸው ።  ሁለቱም ለትግራይ ህዝብ በአጠቃላይ ለኢትዮጱያ ህዝቦች ጠንቅ ናቸው ።እስከ አሁን ለኢትየጱያ ህዝብ ለጥፋቱ እንጅ በማናቸውም መልኩ ሲጠቅሙት ( ሲፈዩዱት) አላዬንም አንመለከተም ያለን ! !
የቲም አብይ አህመድ ለኢትዮጱያ  ህዝቦች እያጠፋቸው ያለው እንጅ ሁለት አመት ተኩል ምንም እንዳልፈየዳቸው  ከክፍል አንድ እስከ ክፍል ሶወስት ለግንዛቤ ያህል በሚል አርእስት በዝርዝር ተመልክተናል ። በተለይ ደግሞ ለትግራይ ህዝብ  አይበገሬ እልኸኛ በመሆነ ነው እንጅ  ድምጽ በሌለው ተኩስ በአፍ ጢሙ ደፍቶታል ። ሲደፋውም ይታያል ።
የህዋሓት የአማራር ቡዱን ከላሸቀው  ሌባ መዋቅሩም ለትግራይ ህዝብ በታሪኩ ፣በቋንቋው በባህሉ ፣በልጆቹ ፣በአንጡራ ሀፍቱ  ራሱን መስለው ለራሳቸው ፣ለልጆቻቸው ፣ለዘመድ አዝማዳቸው ፣ለትውልድ ሀረጋቸው ፣ለሸሪኮቻቸው በማበልጸግ ለትግራይ ህዝብ ግን  በስሙ እየነገዱ 27 አመት ሙሉ ክደውት የኖሩ በቲም አብይ ተገፍተው   ወደ ትግራይ ሸሽተው  በተደበቁባቸው ሁለት አመት ተኩል ብቻ ሳይሆን 27 አመት ሙሉ ለትግራይ ህዝብ እያጭበረበሩ ከመቃብር በታች ያሰፈሩትን አልበቃችሁም ቡሎዋቸው አሁን ደግሞ ለሁለተኛ ጊዜ ሊገድሉት ኢትየጱያነቱን ቀምተው ጭራሹን ለዘመናት ኢትየጱያ ኢትየጱያ አድርጓት የመጣ ህዝብ  ኢትዮጱያ የምትባል አገር ያንተ አገር አደለችም  ኢትዮጱያ የምትባል አገር ለትግራዋይ ከልሆነች ገደል ትግባ የሚል ሞፎከር በማስተጋባት በመላው  የትግራይ ህዝብ አገሩና ታሪኩ ሲያሳጡት ይታያሉ ።
እነዚህ ከሀዲ የጥፈፋት ቡዱኖች  የጥንት የሩቁን ዘመን የዘመነ ኦሪት ታሪካችን ይቆይልን ደብቀውት የኖሩ  በሽሬ ያለው 5643 አመት  ተቆፍሮ የተገኜው ታሪካችን ለታሪክ ተማራማሪዎች እንተወው።አዲሱ ትውልድ ቆፍሮ ያውጣው። የይሓ ፣የአክሱማውያን ታሪካችንም ይቆይ ።ለመሆኑ እነዚህ አገር የሌላቸው የቅርብ ዘመን እንኳን  እቺ ኢትዮጱያ የምትባል የነ አጼ ዮውሀንስ ፣ራስ አሉላ ፣ደጃት ስባጋድስ  ፣ደጃት የውሳቤስ የሌሎች አገር ወዳድ ትግሪያኖች ታሪክ  ወዴት ፍቀው ሊጡሉት ነው ? እነዚህ ከአፍንጫቸው ውጭ አርቀው የማያስቡ ከሀዲዎች ትግራይ የኢትዮጱያ  መሰረት ሞሶሶ መሆና ረስተው፤  አባት አያቶቻቸው እንደሸጡን ሁሉ  ሊሸጡን ፈልገው ይሆን ? እዋዋ  ወዴት ነውስ ይሆን የሚሸጡን ?ምናልባት ትላንትና ወደሸጣት ኤርትራ ?ወይ ለሱዳን ?ወይ ለግብጽ ? ወይ ወደ  ቻይና ወይ ወደ ምእራብ አገሮች  ደግሞ እንዳይሸጡን ?እነዚህ ደግም ወደ ትግራይ እንዳይገቡ ፣ወይ ትግሪያኖች እንዳይወጡ መንገዱ በመሬትም በሰማይም በአብይ አህመድና ኢሳኢያስ አፈወርቅ ተዘግተናል ። ታድያ መጣያችን የት ይሆን ? ከላይ የተቀመጡ ጥያቄዎች የህዋሓት የአማራር ቡዱን ከነጥገኛ ካድሬዎቹ እንድሁም የቡዱኑ አንጨብጫቢዎች ጽንፈኛ ኢሊቶች  መልሳቸው ምን ይሆን ?
    መጨረሻ ዶ /ደብረጽዮን በነዚህ በጽንፈኛ  ድጅታል ወያነ ፣አዮኻ ናይና (አይዞህ የኛ ) እተባለ እተሞካሼበነዚህ አባታውያን እንደ ጋላቢ  ፈረስ እየተዳ ለትግራይ ህዝብ  ጥፋት የሚሽከረከረው ! እነዚህ ሰዎች ለትግራይ ህዝብ እኮ ወደ ስልጣን እስከ እሚወጡ  በተግሉ ጊዜ ለፋሽሽቶች ታገል በማለት ወደ 27 አመት ሙሉ ባልገው የገዙበት  ወንበር ካወጣቸው በኃላ ከድተውት ለራሳቸው  ከእግዚአቢሄር በላይ በማድረግ በባዶ ሆዱ እያሰገዱ አደሂተውት ገዝተውታል ! እነዚህ የጥፋት ቡዱኖች  ለሆዳቸው ለልጆቻቸው ፣ለመላው ዘራቸው  ጥቅም ሲነዱት ዶ /ደብረጽዮን አሁንም  መንጋ የጥፋት ጽንፈኛ ድጅታልና ጽንፈኛ  ኢሊቶች እየተነዳ ለትግራይ ህዝብ እንዴት ያታልላል ። እኔ የሚገርመኝ እኮ ዶ/ደብረጽዮን  አሁን በማወቅ ይሁን ባለማወቅ በባዶ ሆዱ  አንጻር ጥቅሙ ቢሰለፍም ነገ ጥዋት ተገልብጦ እንደሚውጥህ ይገባሀልን    ?
Filed in: Amharic