>

በመተከልና ኦሮሞ ክልል እየተካሄደ ያለውን የዘር ጭፍጨፋ ዋና ዋና አቀናባሪዎቹን ተዋወቋቸው (ጌትነት ይስማው)

በመተከልና ኦሮሞ ክልል እየተካሄደ ያለውን የዘር ጭፍጨፋ ዋና ዋና አቀናባሪዎቹን ተዋወቋቸው

ጌትነት ይስማው

አማራን ከኦሮሞ ክልል, ቤንሻንጉል ጉምዝና አዲስ አበባ አካባቢዎች የማፅዳትና የማዳከም ስራውን የሚመሩት የደህንነትና የመከላከያ ሰራዊት አዛዦች የሚከተሉት ዋና ዋናዋቹ ናቸው:-
አማራው በተለያዩ የኦሮሞ ክልል አካባቢዎች ማፈናቀል, መገደልና የንብረት ውድመት ማድረስና እንዲሁም አማራውን በቤንሻንጉል ጉምዝ አካባቢዋች በመጨፍጨፍ አማራን የማዳከም አቅዱን ያወጣቱ ሌተናል ኮሎኔል #ከፍያለው_ተፈራና #አብይ_አህመድ ናቸው::
ሌተናል ኮሎኔል ከፍያለው ተፈራ የአገር መከላከያ ሰራዊት አባል የነበርና በኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት #ስታፍ_ኮሌጅ ለ2 ዓመት ተኩል ያክል የከፍተኛ መኮነን ስልጠና የወሰደና በወቅቱ ከነበሩ ስልጣኞች መካከል 2ኛ ደረጃ በመውጣት የብር ሜዳልያ ተሸላሚ ነበር:: ከፍያለው መከላከያ ውስጥ ከወያኔ ሰዎች ጋር ስላልተስማማ ወያኔ አባራው ሲኖር አባይ አህመድ ወደ ስልጣን ሲመጣ የኦሮሞ ክልል ፓሊስ ኮሚሽን ኮሚሽነር ሆኖ ኦሮሞ ክልል ከ100,000 በላይ ልዩ ኃይል እንዲያሰለጥን እቅድ አቅዶ በተግባር ስራ የሰራ ሰው ነው:: የኦሮሞን ሰራዊት ከአደራጀ በሗላ በአብይ አህመድ አማካኝነት የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት ኤጀንሲ(ኢንሳ) ምክትል ዳይሬክተር ሆኖ ተሹሟል:: ዋናው የኢንሳ ዳይሬክተር( ዶ/ር ሹመቴ_ግዛው) ምንም ስለ ደህንነትና ውትድርና የማያውቅ ሰው ነው ነገር ግን በአማራ ስም አማራ ተብሎ የተቀመጠ ሰው ምንም የማይሰራ ተላላኪ ሰው ነው:: ኮሎኔል ከፍያለው ከብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር
 አቶ #ደመላሽ_ገብረምካኤል( ኦሮሞ), ከመከላከያ ደህንነት መምሪያ ዋና አዛዥ ሌተናል ጀኔራል አስራት_ደኔሮና ከአዳነች_አበቤ ጋር በመመሳጠር ከፍተኛ የሆነ የጦር መሳሪያና ብረት ለበስ ተሽከርካሪዎችን ጭምር ከውጭ አገር በመግዛት ወደ ኢትዮጵያ በማስገባት ለኦሮሞ ክልል ልዩ ኃይልና ለኦነግ ሰራዊት በግፍ መሳሪያ አስታጥቀዋል:: አብይ አህመድም መሳሪያው እንዲገዛ መፈረሙ ታውቋል::  ከላይ የገለፅኩት እንደተጠበቀ ሆኖ ለኦነግ ሰራዊት የሚሰጠውን መሳሪያ ማን ነው የሚያደርሰው የሚለውን ልንግራችሁ::
ጀኔራል #ነገሬ_ቶሊና :- ለኦነግ ሰራዊት ከለላና መከታ ከመስጠት ጀምሮ በመከላከያ ሰራዊት መኪና ጭኖ ለኦነግ መሳሪያውን የሚያደርሰው ከፊል ወለጋንና መተከልን የሚቆጣጠረው የ22ኛ ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል #ነገሬ_ቶሊና ነው:: ይህ ጀኔራል የቤንሻንጉል ጉምዝን አካባቢ የሚቆጣጠረውን የጦር ሰራዊት የሚመራ ሰው ነው:: ለኦነግ ሰራዊት የሚሆን የመከላከያ ዩኒሮርምን ከመከላከያ ሎጀስቲክ ዋና መምሪያ ሜጀር ጀኔራል #አብዱርአማን_ኢስማሄል ጋር በመመሳጠር ኦነግ የመከላከያ ሬንጀርን እየለበሰ አማራዎችን ቤንሻንጉል ጉምዝ ውስጥ እየገባ እንዲጨፈጭፍ እገዛ የሚያደርግ ጀኔራል ነው::
 ሌተናል ኮሎኔል ገዓሊ_ከማል
ኦነግንና ሌሎችን አማራ ጠል ኃይሎች በማስተባበር ከጀኔራል ነገሪ ጋር አብሮ የሚሰራው ሌላኛው ወንጀለኛ  የቀድሞው ሌተናል ኮሎኔል የአሁኑ የኦሮሞ ክልል ልዩ ኃይል የምዕራብ ዕዝ አዛዥ ረዳት ኮሚሽነር #ገዓሊ_ከማል ጋር በመቀናጀት አማራውን ከቤንሻንጉል ጉምዝ( መተከልና ወለጋ) የማፅዳት ስራውን በተቀናጀ መልኩ እየሱሩበት ይገኛሉ:: በአዲሱ ዓመት በ2013 አማራው የከፋ አደጋ ተጋርጦበታል ለዚህም አደጋ ተጠያቂው የአማራ ህዝብ ዘላለማዊ ጠላት ብአዴን ነው::
አብይ አህመድ አዲስ አበባን በአንድ ክፍለ ጦር ሰራዊትና በኦሮሞ ፓሊስ አስከብቧታል:: አዲስ አበባን በከበባ የያዘው የደጀን ክፍለ ጦር አዛዥ ብርጋዴር ጀኔራል #ግዛው_ኡማ ከአዲስ አበባ ልዩ ኃይል( ሪፓብሊካን ጋድ) አዛዥ ከሜጀር ጀኔራል #ብርሃኑ_በቀለ ጋር በቅንጅት  እየሰሩ ነው:: የደጀን ክፍለ ጦር ሰራዊት የተለያዩ ሬጅመንቶቹን በሰሜኑ የኦሮሞ ክልል ማለትም #ሰላሌና #ደራ አቅጣጫም አሰማርቷል:: አዲስ አበባን የመክበብ ሌላኛው እየተሰራ ያለው ሴራ የአዲስ አበባ ህዝብ ጥያቄ ቢያነሳና ሰላማዊ ስልፍ ቢወጣ መንግዱን ከጅቡቲ መስመር መዝጋት የሚችል ከ5000 በላይ የኦሮሞ ልዩ ኃይል ሰራዊት #በውልንጭቴ, #መተሃራና አፋር ክልል #አዋሽ_7 ድረስ ሰራዊት አሰማርተዋል:: በተጨማሪም በደብረዘይት አየር ኃይል በሽዎች የሚቆጠሩ አየር ወለዶቻቸውን አዘጋጅተዋል:: በስተ ደቡብ በኩል ያለውን ለመደምሰስ አዋሳ ውስጥ ልዩ ኃይሎችና ኮማንዶዎችን አዘጋጅተው ኦሮም ክልልን አየጠበቁ ነው::
ድሮ የምናውቀውን የትህነግ ገዳይ ቡድን የአጋዚ ኮማንዶ ክፍለጦሮችን አፍርሰው በራሳቸው በኦህዴዶች አደረጃጀት አደራጅተው ከአዲስ አበባ ውጭ በደብረ ዘይት, ድሬዳዋ, አዋሳና በህዳሴ ግድብ በኩል ያለውን የኦሮሞ ሰራዊት ሜጀር ጀኔራል #ሹማ_ያዴታ ይመረዋል:: አዲስ አበባና በዙሪዋ ያለውን ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ በቀለ ይመረዋል:: በነገራችን ላይ ሜጀር ጀኔራል ብርሃኑ በቀለና ሌተናል ኮሎኔል ክፍያለው ተፈራ የኦነግ አባል ናችሁ ተብለው ከሰራዊት ተባረው የነበሩትን ሰዎች ናቸው አሁን ላይ አብይ አህመድ ወደ ቦታቸው የመለሳቸው:: አማራን በተደራጀና በተቀናጀ መልኩ ሰላምን የመንሳት ስራን ሆን ተብሎ በእነ አብይ አህመድ አቀናባሪነት የተደረገ ነው:: ከዚህ ጋር መረሳት የሌለበት የአብይ አህመድ አማካሪዎች የኦነግ መስራቾች ዶ/ር ዲማ ነገውና ሌንጮ ባቲ መሆናቸው ነው:: የሽመልስ አብዲሳ አማካሪ የኦነግ ዋና ፀሐፊ የነበረው ዶ/ር ኑዑር ሐሰን ነው:: ይህንን መረጃ ብአዴን 100% ያውቃል; ምን ማድረግ እንዳለበትም ብዙ አማራጭ ሃሳቦች ተነግሮት ነበር ነገር ግን በባርነት ያደገ ስነ ልቦና እንዴት ድፍረት ያገኛል?!
አማራው ብአዴንን ሳታስወግድ ወደ ነፃነት ማማ እወጣለሁ ብለህ ካሰብክ የሞተ ሰው ተመልሶ ይመጣልኛል ብለህ እንደማሰብ ነው::
እኔ በግሌ የችግሩ ውስብስብነትና ያለንን ወቅታዊ ጥንካሬ በማሰብ ብአዴንን ስደግፍ ነበር ግን እነሱን አማራ ከማድረግ ትህነግን አማራ ማድረግ ስለሚቀል እነሱን ከማስወገድ ውጭ መፍሄ የለም ብየ ደምድሚያለሁ ምክንያቱም ከዚህ በላይ ለማሰብ አቅሙ የላቸውም::
የብአዴንን አከርካሪ በመስበር አማራን መታደግ ታሪካው ኃላፊነት አለብን!
መፍትሄዎች
========
1. የአማራ ብሄርተኝነትን በአንድነት መንፈስ ማቀጣጠል
2. ብአዴንን በማስጨነቅ ከመከላከያ ሰራዊት በትህነግ ዘመን የተባረሩትን የመከላከያ መኮነኖች ወደ ልዩ ኃይሉ እንዲቀላቀሉ ማስገደድ
3. ማንኛውንም ምርኩዝ ያለውን የአማራ ገበሬ ማደራጀት
4. የአማራ አክቲቪስቶችን አንድ እንዲሆኑና አብረው እንዲሰሩ ማድረግ
5. መንደርተኛን አከርካሪውን መስበር ወዘተ
ሌሎችን በግል እንወያያለን
Filed in: Amharic