>
5:13 pm - Monday April 19, 7915

ለዜጎች ደህንነት ግድ የማይለው መንግስት፤ መንግስት አይደለም (ዶ/ር በቃሉ  አጥናፉ  ታዬ)

ለዜጎች ደህንነት ግድ የማይለው መንግስት፤ መንግስት አይደለም

 

/ በቃሉ  አጥናፉ  ታዬ


ወያኔ/ኢህአዲግ ለ27 ዓመት ከሰራቸው መንገዶች እና የልማት ስራዎች ይልቅ በሰብዓዊ መብት ላይ ያደረገው ዘርፈ ብዙ የሰብዓዊ መብት ጥሰት ጎልቶ ሲተረክ ይኖራል፡፡ በተመሳሳይ ሁኔታ ኦህዴድ/ብልፅግና እየሰራሁት ነው ከሚለው የዕድገት ቱርፋቶች ይልቅ በየክልሉ የሚሰሙት አሰቃቂ ግድያዎች እና የሰብዓዊ መብት ጥሰቶች ስርዓቱን መንግስት አልባ አድርጎታል፡፡ በአይን ያልታዩ፣ በጀሮ ያልተሰሙ፣ በህሌና ያልታሰቡ የዕድገት ቱርፋቶች፡ ፓርክ፣ መዝናኛ፣ ግንባታ፣ ግድብ፣ መናፈሻ፣ ህንፃዎች፣ መንገዶች፣ ፕሮጀክቶች በሀገሪቱ ላይ ቢሰሩ እና ተሰርተዋል ብለን ብናስብ እንኳን ከሰዎች ህልውና ጋር የሚነፃፀሩ አይደሉም፡፡

ዜጎች አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ እየተገደሉ፣ ሰዎች በማንነታቸው የጥቃት ሰለባ እየሆኑ፣ የሰው ልጅ ያፈራው ንብረት በመንጋ  ጥቃት አመድ እየሆነ እየታየ ገፅታ ግንባታ ላይ ማተኮር ብልህ አያሰኝም፡፡ የረከሰ ስራን የሚሰራን አሸባሪ ቡድን ፀጥ ማድረግ ያልቻለና የዜጎችን ህይወት ከአጥቂዎች መታደግ ያልቻለ መንግስት መንግስት አይደለም፡፡ እንዲሁም የረከሰ ስራን የሚሰራን አሸባሪ ቡድን ወደ ፍትህ አቅርቦ መቅጣት ያልቻለ መንግስት ቅቡልነት አይኖረውም፡፡ ለሰው ልጅ ወይም ለዜጎቹ ክብር እና ደህንነት ትኩረት የማይሰጥ መንግስት መንግስት አይደለም፡፡

Filed in: Amharic