>

እቴጌ ጣይቱ ብርሀን ዘኢትዮጵያ ፤ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መስራች...!!! (አበበ ሀረገወይን)

እቴጌ ጣይቱ ብርሀን ዘኢትዮጵያ ፤ የመጀመሪያው የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ መስራች…!!!

አበበ ሀረገወይን

በኢትዮጵያ ታሪክ የመጀመሪያው ባንክ እኤአ በ1905 በግብጽ ብሔራዊ ባንክ እና በኢትዮጵያ መንግሥት ስምምነት የተመሠረተው ‹‹የሀበሻ ባንክ – Bank of Abyssinia›› ነው። ይህ ባንክ ግን ባለንብረትነቱ የእንግሊዝ መንግሥት ነበር። በስምምነቱ መሰረት ለኢትዮጵያውያን ብድር በወቅቱ ለመመለስ የማይችሉ ከሆነ ከመመለሻ ቀኑ የሚያዘገይቱንም ማሰር ይችሉ ነበር ።  ነገሩን ብዙም ያልተረዳቸው ወገኖቻችን ካላቅማቸው በመበደርና በጊዜ አለመክፈል ሙልጭ እየወጡ እስረኞች ሆኑ ።
እቴጌ ጣይቱ ይህንን በሰሙ ጊዜ  ጊዜ ይህ አሳፋሪና ነውረኛ ተግባር ፈረንጆችን ዱሮም ስለማይወዱ በጣም አናደዳቸው።
እቴጌ ጣይቱ ባላቸውን ዳግማዊ ምኒልክ ጉዳዩን በማማከር እስረኞችን ከማስፈታትና የእንግሊዞችን ባንክ ከመዝጋት ባሻገር ሌላ አማራጭ ብሔራዊ ባንክ ስለመክፈት መከሩ። ከምክክር በኋላም በኢትዮጵያውያን ሲመሠረት የመጀመሪያውና በልማት ባንክ ታሪክ ፈር ቀዳጅ የሆነው ‹‹የርሻና የንግድ ማስፊያ የኢትዮጵያ ማኅበር›› ተመሠረተ።
የኢትዮጵያ ልማት ባንክ የመጀመሪያው አክስዮን ማሕበር ነበር ። የመሰረቱት ኢንቬስተሮች ሰባት የወቅቱ ከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣና ዳግማዊ አፄ ምኒልክና እቴጌ ጣይቱ መሥራች ማኅበርተኛ አባል ሆነው እንዲገቡ ተደርገ።
የምስረታ ቻርተሩም እንዲህ ይል ነበር ‹‹እኛ ዳግማዊ ምኒልክ፣ እቴጌ ጣይቱ፣ ራስ ቢትወደድ ተሰማ ናደው፣ ራስ ወልደጊዮርጊስ፣ ፊታውራሪ ሀብተጊዮርጊስ ዲነግዴ፣ በጅሮንድ ሙሉጌታ ይገዙና ነጋድራስ ኃይለጊዮርጊስ ወልደሚካኤል በዚሁ ወረቀት ግርጌ የእጅ ፊርማችንን ያደረግን የኢትዮጵያ ማኅበር አቁመን ስሙን ‹የርሻና የንግድ ማስፊያ የኢትዮጵያ ማኅበር› ተብሎ እንዲጠራ ተስማምተናል።›› በማለት በማለት ተፈራመው አጸደቁት። አዋጁም ግንቦት 23 ቀን 19ዐ1 ዓ.ም (እኤአ 1909) በይፋ ታውጆ ባንኩ/ማኅበሩ ተመሠረተ። በኋላም ሌሎች ሰዎችና ነጋዴዎች አክሲዮን በመግዛት በማኀበሩ ውስጥ ተሳታፊ ሆኑ።
Filed in: Amharic