>
5:18 pm - Friday June 15, 2840

አብይ አህመድ አሊን እንዳጠናሁት...!!! (Psychiatric analysis ዶ/ር ዮናስ አበራ)

አብይ አህመድ አሊን እንዳጠናሁት…!!!

Psychiatric analysis
ዶ/ር ዮናስ አበራ

 


 

አብይ አህመድ አሊ በተደጋጋሚ “ኢትዮጵያን የምታፈርሰው እኛን አፍርሰህ ነው” የሚላትን ነገር ሁሌ ሳስባት ትገርመኛለች። ንግግሯ ተራ ድንፋታ የምትሆንብህ ሰውዬው ከንግግሯ ጋር የሚሄድ አንድም ነገር ሲሰራ አለማየትህ ነው።
ሰውዬው ተራ narcissist መሆኑን ደግሞ በተደጋጋሚ አይተናል። Narcissismን በቅጡ ወደ አማርኛ የመለሰ ሰው እስካሁን አላየሁም። በ vocabularyው በጣም የማደንቀው ጋዜጠኛ ቴድሮስ ፀጋዬ Narcissismን “በለከት የለሽ የራስ ፍቅር የመውደቅ ልክፍት” ብሎ የተረጎመው ነገር ልክፍቱን ከሞላ ጎደል ይገልፀዋል ብዬ እገምታለሁ። Narcissist ሰዎች በየቦታው አሉ፤ ኑሯቸው አሳዛኝ ነው፤ ወዳጅ አይበረክትላቸውም፤ ፍቅረኛ አይበረክትላቸውም፤ ጉራቸው አየሩን ስለሚቆጣጠረው ሰው አጠገባቸው አይቆይም። የ Narcissismን ልክፍት ከሁሉ የከፋ የሚያደርገው narcissistቱ ሰው ሃብት ያገኘለታ፣ በስሩ ሰዎች ማስተዳደር የጀመረ ለታ፣ ወይም ወደ መንግስት ስልጣን የወጣ ለታ ነው፤ በተለይ የሃገር መሪ የሆነለታ!! በበኩሌ አንድ narcissist ዙፋን ላይ ሲቀመጥ እንደማየት የሚያስፈራ ነገር ያለ አይመስለኝም!! ዙፋን፣ መሃተም እና ሽጉጥ ከናርሲሲስት ጋር !! Deadly combo!!
የnarcissist ሰዎች መገለጫዎች የተለያዩ ናቸው። እኔ ቆንጆ ነኝ፣ እኔ ጂኒየስ ነኝ፣ ሳር ቅጠሉ ሳይቀር ሁሉም ይወደኛል፣ ሴቶች ይወዱኛል፣ እናቶች ይወዱኛል፣ የሃይማኖት አባቶች ይወዱኛል፣ የአለም ታላላቅ ሰዎች በእኔ ይደነቃሉ፣ ተራው ዜጋ አይመጥነኝም፣ ያለጊዜው የተፈጠርኩ የወደፊት ዘመን ሰው ነኝ….  ወዘተ ብለው ያስባሉ… ማሰብ ብቻ ሳይሆን ነኝ ሲሉ ያምናሉ።
በአንድ ወቅት አንድ በሌላ ህመም መጥቶ ያከምኩት ሰው ስለ ግል ህይወቱ ሳልጠይቀው ሲያወራኝ ሚስቱን በወሲብ ረሃብ መቅጣት እንደሚያስደስተው ያወራኝ ነገር ስለ narcisssiቶች ባሰብኩ ቁጥር ሁሌ ትዝ ይለኛል። Narcissistቶች እዚህ ድረስ antisocial ናቸው!!
ባጠቃላይ የሚያስቡት ነገር Delusion of Grandiosity ካለባቸው psychoticኮች የሚለዩት insight (ቀልብ) ስላላቸው ብቻ ነው ብል ብዙ ማጋነን አይመስለኝም።
ናርሲሲስቶች ሁሉን ነገር አውቃለሁ ባይ ናቸው። ሁሌ እኔ ብቻ ጎበዝ ነኝ ባይ ናቸው።
አብይ ከተናገራቸው ውስጥ እስኪ አንዳንዱን እንይ፦
 እኔ ስፖርተኛ ነኝ፣ እኔ ምርጥ ክርስቲያን ነኝ፣ አንባቢ ነኝ፤ በየቀኑ አነባለሁ፤ ሳታነብ እደር ካልከኝ አብዳለሁ፣ ጦርነት ያደግሁበት ነው፣ የከተማ ጦርነት ሊያስተምሩን ይፈልጋሉ፣ ንጉስ እንደምሆን ከህፃንነቴ ጀምሮ አውቅ ነበረ፣ እናቴ በህፃንነቴ ሰባተኛው ንጉስ እንደምሆን ነግራኝ ነበር ፣ አንዲት ጣሊያናዊት ላግባህ ስትለኝ አለቀስኩ (ይሄንን ደግሞ ትናንት ነው የሰማሁት)፣ እኔ አሻግራችኋለሁ፣ ለሁለት የተከፈለውን ሲኖዶስ እኔ ባላስታርቅ ኖሮ ኦርቶዶክስ አብቅቶላት ነበር፣ ሁለት ቦታ ተከፍለው የነበሩት ሞስሊሞች በጋራ መስገድ የጀመሩት በእኔ ጊዜ ነው፣ በአሁኑ ሰዓት ከአፍሪካ እንደ እኔ የህዝብ ተወዳጅነት ያገኘ መሪ የለም፣ እኔ ዴሞክራት መሪ ስለሆንኩ የውይይት አጀንዳ ነው የማመጣው፣ 5 ቢሊዮን ዛፍ ሊተከል የቻለው ህዝብ ስለሚወደኝ ነው (500 ሺህ አይሞላም እኮ የተተከለው)፤ አሜሪካና ቻይና እንትከል ቢሉ አይችሉም፣ እኔ የተከልኩት ዛፍ ዝናብ አምጥቶ ደርቆ የነበረው ሃሮማያ ሃይቅ ሞላ፣ ኧረ ሰውዬው ምንን ያላለው አለ?! እስኪ እናንተም ጨምሩበት….
ናርሲሲስቶች እነሱ የሚሉትን ሌሎች ሰዎች ካላደነቀላቸው፣ አብሯቸው ካላሸበሸበ ወይም ከተቻቸው ሊያብዱ ይደርሳሉ፤ የሚይዙት የሚጨብጡትን ያጣሉ፣ እንቅልፍ አይወስዳቸውም፣ ያንን ሰው እጅግ አድርገው ይጠሉታል!! ይከራከሩታል፣ ለማሳመን የማያደርጉት የማይቧጥጡት ተራራ የለም። እሱም ካልተሳካ ድንፋታ ውስጥ ይገባሉ!! አብይ ከደነፋቸው ውስጥ ደግሞ ጥቂቶቹን እንይ፦
 በእኔ ጊዜ ነው ሃገር ቤት ገብታችሁ ዘመድ መጠየቅ ይቻላችሁት፣ ምን እኔን ትጨቅጭቁኛላችሁ? እኔ አላቃጠልኩም፤ እኔ ይቅርታ አልጠይቅም (ቤ/ክ ለምን ይቃጠላል ስለተባለ የሰጠው መልስ)፣  እኔ አላፈናቀልኩም፣ እኔ ወረዳ ድረስ ወርጄ መንደር ለመንደር እየዞርኩ ፀጥታ ላስከብርልህ ነው እንዴ?! ጠ/ሚሩ የስራ ድርሻውን ጠንቅቆ ያውቃል፣ እኔ ልቆጣጠራችሁ ስለማልችል ፈጣሪ ይፍረድባችሁ (ዳያስፖራውን)፣ የኛ ሃገር ምሁር መኪና እንኳን መግዛት የማይችል ቀበሌ አስተዳድሮ የማያውቅ ከንቱ ነው፣ ግልፅ ጦርነት ውስጥ እንገባለን (እስክንድርን ነው)፣ ኦሮሞ ሃገር መምራት ሲጀምር ነው እንዴ ሃገር የሚፈርሰው?!! (ያለ’ኮ የለም፣ እርኩስ!!)፣ ወዘተ…..
ናርሲሲስትን አዎ! አዎ! አዎ! ልክነህ !! ፓ! ፓ!! እያልክ ካደነቅህ አበቃልህ!! አናትህ ላይ ልሽና ይልሃል!!
እንግዲህ ለአብይ አህመድ አሊ በስልጣን ላይ ጭብጨባ ጨምርለት፣ በዚህ ላይ እሱን ከቦንብ ጥቃት ለማዳን የአ.አ ወጣቶች ምስዋት ሆኑለት የሚለውን ዜና ጨምርለት፣ ካላንተ አንድንም ባዮቹን እንከፎች ጨምርለት፣ በዚህ ላይ “ፓ አብይ!! በ6 ወራት ኢትዮ ኤርትራን ሰላም አደረገ!!” የሚል ፉጨት ነገር ጨምርለት፣ በዚህ ላይ የአባይ ግድብ በሱ የሰልጣን ዘመን ስኬታማ ሆነ የሚለውን ተረት ጨምርለት፣ በዚህ ላይ በአለም ታላቁን የሰላም የኖቤል ሽልማት ጨምርልኝ፣ “መሪስ ተገኝቶ ነበር ተከታይ ህዝብ ጠፋ እንጂ” እየተባለ በአለቅላቂዎቹ የተደፋለትን እጣቢ ጨምርልኝ!!! ….ያኔ……
….. ያኔ …..
ይሄ ሁሉ ሙገሳና እልልታ አንድን እንደ አብይ አይነቱን ደካማ ጨቅላ ናርሲሲስት ወደ Megalomania ያለመውሰዱን ስትመለከት የፈጣሪ ተአምር እንደሆነ ይገባሃል!!
ሰውዬው እንኳን ሃገር ሊመራ እራሱ በደስታ ከፎቅ ላይ ተወርውሮ ሳይሞት ማደሩም ሊገርምህ ይገባል….. እንኳን ኢትዮጵያን የምታክል ታላቅ ሃገር ሊመራ ጉራውን ሲቸረችር ስለሚውል ዝናሽንም በቅጡ “ማስተዳደሩን” እንጃ (NB: ማስተዳደር ከአዳር ጋር ግንኙት ሊኖረውም ላይኖረውም ይችላል)…. LOL
Fast Forward
Narcissists always fail, and fail big time. And they don’t do good with failure!!
Abiy is failing big time!!
እመነኝ ሰውዬው በመጨረሻ ይሸሻል፣ ይደበቃል፣ ከዚያም በገዛ ፍቃዴ ስልጣኔን ልቅቄያለሁ ይለናል፣ እሱ ከሌለ ሃገር ይፈርሳል ይሉ የነበሩ ሰዎችን እንባ ይሰበስባል!! በገዛ ፍቃዱ ስልጣኑን የለቀቀ የኖቤል ሎሬት ተብሎ በታሪክ መታወስ የመጨረሻ ድሉ እንድትሆን ይመኛል።…. ሌላ ርካሽ ፉጨት፣ ሌላ መናኛ ጭብጨባ ይሸምትብናል….. At the expense of the Nation …..
Filed in: Amharic