>
5:28 pm - Tuesday October 10, 8186

ግልጽ ደብዳቤ ለውድ ወንድሜ ለኤርምያስ ለገሰ (መስፍን አረጋ)

ግልጽ ደብዳቤ ለውድ ወንድሜ ለኤርምያስ ለገሰ

መስፍን አረጋ      


“በመጀመርያ ይንቁሃል፣ ቀጥለው ይዘልፉሃል፣ ከዚያም ይፋለሙሃል፣ በመጨረሻ ትረታቸዋለህ::” 

“First they ignore you, then they ridicule you, then they fight you, then you win”

ማህተማ ጋንዲ (Mahatma Gandhi) 

 

 

ይንቁ የነበር እየተሳለቁ

ንቀታቸው ሲናቅ ስለሚጨነቁ፣

እንደሚመቱበት በርግጥ እያወቁ

ዱላ ያነሳሉ ባነሱት ሊወቁ፡፡

 

ለውድ ወንድሜ የኢትዮ360ው አቶ ኤርምያስ ለገሰ፡፡ በኔ አመለካከት አብይ አህመድን በትክክለኛው መንገድ ተረድተው በትክክለኛው መንገድ ከሚታገሉት ጥቂት ሰወች ውስጥ አንተ ኤርምያስ አንዱና ዋናው ነህ፡፡  የምትታገለው ደግሞ የጦቢያን ካዝና በብቸኝነት ከሚቆጣጠር፣ ማናቸውንም ሆድአደር በጠየቀው ምንዳ ምንደኛ ለማድረግ ከማያቅማማ፣ በስልጣኑ ከመጡበት እርምናው ወደር ከሌለው ሊቀሰይጣን ጋር መሆኑ ካንተ የተሰወረ አይደለም፡፡  

ጦቢያችን ደግሞ ባለመታደል በቀላሉ ሊመነደኙ (ምንደኛ ሊደረጉ) የሚችሉ ሆድአደሮች ሆልቆ መሳፍርት የሆኑባት አገር ናት፡፡  ስለዚህም የዐብይ አህመድ ሆልቆ መሳፍርት ወራዶች የሚያወርዱብህን ውርጅብኝ ከቁብ ሳትቆጥር፣ በበለጠ ቆራጥነት በያዝከው ፈር ትቀጥል ዘንድ ወንድማዊ ማበረታቻየን ልገልጽልህ እወዳለሁ፡፡  

በትልቁ ሥዕል ሲታይ፣ ዐብይ አህመድ ከባዶ ፉገራ በቀር የሚያስመሰግነው ምንም ስላልሠራ መመስገን የለበትም፡፡  ዐብይ አህመድን ማመስገን ማለት በማር በተለወሰ መርዝ የሚመርዝን መርዘኛ ለማሩ ማመስገን ማለት ነው፡፡  መርዝም ቢኖረው ለማሩ ሲባል የግድ መመስገን አለበት ከተባለ ደግሞ ምንደኞቹ የሚያመሰግኑት ሲበዛበት ነው፡፡

 ስለዚህም ሚዛናዊ ለመባል ሲሉ ብቻ ዐብይ አህመድን እያወደሱና እያሞገሱ ገባ ወጣ የሚሉ ሊጠነቀቁ ይገባል፡፡  አለበለዚያ አጅሬ ሲገቡለት ጠብቆ እንዳያንቃቸው ያሰጋል፡፡  ዐብይ አህመድ አያሌ ጉምቱወችን ከንቱ በማድረግ የፀረኦሮሙማን ትግል ክፉኛ ያዳከመው በዚህ ዘዴው መሆኑ መረሳት የለበትም፡፡      

ዐብይ አህመድ ገደል አፋፍ ደርሶ ሊንኮታኮት አንድ ሐሙስ እንደቀረው እሱ ራሱ በደንብ ያውቃል፡፡  ለሚያስከትሉበት ከፍተኛ ፖለቲካዊ ኪሣራ ዴንታ ሳይሰጠው የሚሾማቸው ሹመቶች፣ የሚፈጽማቸው እስሮችና ለዘር ጭፍጨፋ የሚያሳየው ጆሮ ዳባ ልበስነት በግልጽ የሚመሰክሩት ተስፋ መቁረጡን ብቻና ብቻ ነው፡፡  ያሁኑ መፈራገጡ ለመላላጥ ብቻ ነው፡፡ 

 ስለዚህ ወንድሜ ኤርምያስ፣ ያብይ አህመድ ውሾች ጌታቸው የሚወረውርላቸው አጥንት እንዳይቀርባቸው ላንቃቸው እስኪሰነጠቅ ለሚጮኹት ጩኸት ጆሮህን ሳትሰጥ፣ ገባ ወጣ ሳትል በርትዕ መንገድህ ቀጥ ብለህ ተጓዝ፡፡  

 

አክባሪህ መስፍን አረጋ      

mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic