>

ታጋይ ዝም አይልም !!  እነ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ነጋ በታጋዮች ላይ የተጫወተት ቁማር !! (ጌታቸው ሺፈራው)

ታጋይ ዝም አይልም !!

 እነ ፕሮፌሰር ብረሃኑ ነጋ በታጋዮች ላይ የተጫወተት ቁማር !!

ጌታቸው ሺፈራው 

 አርበኞች ግንቦት 7 በፍጥነት አፍርሰው አዲስ ፓርቲ ለመመስረት ብዙ ጊዜ አልወሰደባቸውም ነበር ።
 በትግል ወቅት ብዙ ጊዜ እንደ ምሳሌ የሚጠሯቸውን ታጋዮች  እስክሪን ወደ ቤተሰቦቻቸው ሳያደርሱ ፣ በየጫካው የወደቁት  መሰዋእትነት የሁኑት ጀግኖችን ቦታ ሳያገኙ፣  በግዳጅ የላኩትን ሰራዊት የቆሰሉትን ህክምና ሳያገኙ በአጠቃላይ በትግሉ ላይ ብዙ አስተዋጽኦ ያደረገውን ታጋይ ሜዳ ላይ በትነው ። አዲስ ድርጅት መሰረቱ ።
ከምንም በላይ መሰዋእትነት የሆኑት ጓዶች ነገር  መርሳቱ ህሊና ላለው ሰው የሚያም ነው። ፖለቲካ ሲሰሩበት የቆዩበትን ሰራዊት በትነው አዲስ ፓርቲ መመስረት የጀመረው የነብረሃኑ ድርጅት ይመስለኛል ። ከኤርትራ ወደ ኢትዮጵያ ከመምጣታቸው በፊት መጀመሪያ ታጋዮች ተቋቋማለችሁ የቆሰሉት ጓዶች ደግሞ የተሻለ ሕክምና የሚያገኙበትን ሁኔታዎች እናመቻቻለን ፣ ለዛሬው ነፃነት ያበቁንን መሰዋት የሆኑትን ልጆች  መታሰቢያ ሀውልት እናቆማለን ፣ ለቤተሰቦቻቸው እናስረዳለን ፣  ልጅ ያላቸውን እና አቅመ ደካማ እናት አባት ያላቸውን የገንዘብ ድጋፍ እናደርጋለን ብለው ነበር እና ብረሃኑ።
ይህ ሁሉ ተረስቶ ጭራሽ ሰለ ግዳጅ ፣መሰዋእትነት ሰለ ሆኑት ጓዶች በአሁኑ ሰአት ማንሳት  ልክ እንደ ሕወሓት ትቆጠራለህ፣
የአርበኞች ግንቦት7 ታጋዮች አይሆንም ድርጅቱ መፍረስ የለበትም መጀመሪያ የሚቀድሙ ነገሮች አሉ ብለው ብዙ ሞግተዋል ። ነገር ግን አፍ  ቀላጤዎች የእነሱን ሀሳብ የሚጋሩትን ሰዎች በመሰብሰብ የፈለጉትን አድርገዋል ።
ጭራሽ የንቅናቄው ገንዘብ የነበረውን ሁሉ የአዲሱ ፓርቲ ስራ ማስፈፀሚያ አድርገውታል ።
ድርጅቱ ከኤርትራ ያለውን የትጥቅ ትግል አቁሞ ወደ ኢትዮጵያ ከገባ በኋላ በኤርትራ የነበረውን ንብረት ለመሸጥ ኮሚቴዎች አዋቅሮ መልሶ ልኮ ነበር ። ኮሚቴዎች በታዘዙት መሰረት በኤርትራ የሚገኘውን የድርጅቱን ንብረት ሽጠዋል። መኪኖች ፣የኮምፒዩተር ብዛት ስፍር ቁጥር የለውም ፣ የሶላር ብዛትም እንዲሁ ፣ የመኪና ባትሪዎች ፣ ቴለቪዥን ፣እነዚህ ሁሉ ተሽጠዋል ። ኮሚቴው ገንዘቡን አስረክቧል ።
በውጭ ሀገር የሚገኙት ኢትዮጵያዊ ለታጋዮች ለድርጅቱ ስራ ማስፈፀሚያ የሚሆን ብዙ ገንዘቦችን አፍስሰዋል ። በተለይ ለውጥ መጣ ሰለ ተባለ ሁሉም ሰው የአቅሙን ለአርበኞች ግንቦት7 ድጋፍ አድርጓል ።ድርጅቱ ወደ ሀገር ቤት ሲገባ ለአቀባበል  በሚል በመቶ ማሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ ሰብስቦል።
ይህ ገንዘብ ለታጋዮች ማቋቋሚያ በቂ ነበር ነገር ግን መብላት ሰለ ሚፈለጉ ወይም ለአዲሱ ድርጅት አላማ ማስፈፀሚያ እንዲውል አድርገዋል ። ከጀርመን መንግስት የሚለቀቅ ገንዘብ አለ በሱ ታጋቹን እናቋቁማለን የሚል መላ ምት ይዘው የድርጅቱን ገንዘብ አድራሻውን አጥፍተውታል።
ታጋይ አሁንም ይሰቃያል በተቃራኒው የኢዜማ አመራሮች በወር 18 ሺህ ብር ይከፈላቸዋል ። እንደውም የቀድሞው የአርበኞች ግንቦት7 አባላት የሆኑት ሰዎች አሁን በኢዜማ ውስጥ የማደርገውን የፓርቲው ትግል እንለቃለን የሚሉት በርክተዋል ።  ይህ ብቻ አደለም መከፋፈል አለ ። ድርጅቱ አሁን ያለበት ሁኔታ አሳሳቢ ከመሆኑም በላይ መረጃዎች ወደ ውጭ እንዳይወጡ በጥንቃቄ እየሰሩ ነው። የታጋዮች ግፍ እየተፋረደ ነው።እነማን ናቸው የምትለህ ካለህ እበትናቸዋለሁ ስማቸውን!!
  ክብር መሰዋእትነት ለሆኑት ታጋዮች!
Filed in: Amharic