>
5:28 pm - Sunday October 10, 5294

አይ ኢትዮጵያ ሁሌም ስሙ እንጂ ነገርየው የለም...የለም... ምንም የለም...!!! (ሀይማኖት ፍቃዱ)

አይ ኢትዮጵያ ሁሌም ስሙ እንጂ ነገርየው የለም…የለም… ምንም የለም…!!!

ሀይማኖት ፍቃዱ
ሠንጋ ተራ ሠንጋ የለም እንቁላል ፋብሪካ እንቁላሉን ተወውና ፍርፍሩ የለም ጠመንጃ ያዥ ጠመንጃም ያዡም የሉም ቦንብ ተራም ሽቅላጂ ቦንብ ወፍ
.
ሽሮ ሜዳማ ደና ሽሮ ቤትም የለም መገናኛ ትጠፋፋለህጂ አትገናኝም አዲሡ ገበያ ደሞ ከማርጀቱ የተነሳ አዲሡ ስትል ገና ሳቅህ ያመልጥሃል ቡፍ,,,,
.
ሶማሌ ተራን ጉራጌ ተረክቦታል ሶማሌ ይናፍቅሃል ጎጃም በረንዳንም ስልጤ ቀሽቦታል ዶሮ ማነቂያ ኪስህንጂ ዶሮ አይታነቅም ተረት ሠፈር ተረብጂ ተረት የለም…..
,
ጎፋ መብራት የሚባል ሠፈር ደሞ አለለህ መብራት የለም:- ንፋስ ስልክም ንፋስጂ ስልክ አይሠራም ፡ ውቤ በርሃ ውቤም በርሃውም መንነዋል፡፡ አባ ኮራን ውሸት ነው አይኮሩም….
,
ሠባራ ባቡር ሠባራዋን አንስተዋታል ባቡር የለም ፡ መነን የመነነ አታይም የሚያስመንን ግን አይጠፋም፡ ሾላ ገበያ ገበያው አለ ሾላውን በልተው ጨርሠውታል….
,
አራዳ አራዳዎች የሉም:: የት ሄደው ነው ግን …. ነበሩ ወይ? አደይ አበባ አደይንም አበባንም አታገኛቸውም፡፡ 22 ማዞሪያ 22 ቁጥር ባስ አሁን አትዞርም፡፡ በየት እየዞረች ይሆን? ይቺ ዙረታም…..
ምድነው የሚያስቀባጥረኝ???
ነገሩ ወዲህነው አገሪቱ ሠላም ሚኒስተር አላት – ሠላም ግን የላትም!
Filed in: Amharic