>

ጸብ ቀን የምትቃጠሩ ፓለቲከኞች እባካችሁ ልብ ግዙ!!! (ያሬድ ሀይለማርያም)

ጸብ ቀን የምትቃጠሩ ፓለቲከኞች እባካችሁ ልብ ግዙ!!!

ያሬድ ሀይለማርያም

ከመንግስት ጋር ያላችሁን ማንኛውንም ልዩነት የፈጀውን ጊዜ ይፍጅ በውይይት እና በድርድር ለመፍታት ሞክሩ። እሱ እንኳ ባይሳካ ሌሎች ሰላማዊ የመታገያ መንገዶችን ምረጡ። ቀን ቀጥሮ መንግስት የለም፣ አይኖርም እያሉ ማወጅና መፎከር የፈረደበትን ያንኑ ደሀ ሕዝብ ከማስጨረስ ያለፈ ፋይዳ አይኖረውም። ለጸብ የምትቃጠሩ ፖለቲከኞች እና የለውጥ አቀንቃኞች ልብም፤ አደብም ግዙ። ሁሌም ጸብ ጠማቂዎች ግጭት ሲነሳ ዳር ቆመው ተመልካቾች ናቸው። በገባውም፤ ባልገባውም የሚሞተው የድሃ ልጅ ነው። መንግስትም ጃስ ባሉህ ቁጥር ለጸብ ማቆብቆብህን አቁም። ሕዝብ በመንደር ታጣቂዎች ሲያልቅ ድምጻቸው የማይሰማ ወታደራዊ ሹማምንት ሳይቀሩ መንግሥትን ትነኩና ወየውላችሁ እያሉ የዛቻ መአት በሚዲያ ማዥጎድጎድ ሕዝቡን ማሸበር ነው።
መስቀልንም ሆነ የኢሬቻን በአል በሰላም እንደምናሳልፍ ሙሉ ተስፋ አለኝ። መልካም የመስቀል በዓሌ።
Filed in: Amharic