>
5:28 pm - Tuesday October 10, 8428

አስቴር ስዩም - እንባዋ ሳይታበስ ዳግም ያነባችው ታጋይ ! (ውብሸት ታዬ)

አስቴር ስዩም – እንባዋ ሳይታበስ ዳግም ያነባችው ታጋይ !

ውብሸት ታዬ

 

የዛሬ ዓመት በዚህ ቀን እንዲህ አብረን አሳልፈነው ነበር(fb አስታዋሹ)። ሰፊ ሃሳብና ቀናነት ነበራት። በእኔ ውስን መረዳት፤ ስህተቶች ቢኖሩ እንኳ እየተራረሙና እየተደጋገፉ የአስቴር ዓይነቶቹን በትግል ዕሳት ተፈትነው የነጠሩ የሕዝብ ልጆች ማብቃት ይገባል።
  የሚያወጣን መንገድም ይህ ነው።
አንድ ወቅት ይህን ብለን ነበር…
 
የእናት ምትክ …
 
   “ነሐሴ 28 ቀን 2008 ዓ.ም ቂሊንጦ እስር ቤት እንደተቃጠለ እናቴ ስትሰማ በድንጋጤ ወደቀች። አልተነሳችም፤ በዚያው አለፈች። የእናቴ ማረፍ ብቻ ሳይሆን የተረዳሁበት መንገድ አይረሳኝም። ፖሊሶቹ “ይኸው እናትሽ ሞታለች፤ አንቺ ግን አሁንም ትታገይናለሽ ማለት ነው?” አሉኝ። እናቴ ብታልፍም አገሬ አታልፍም ብዬ ነው ይህን የበጎ አድራጎት ድርጅት “እናት ኢትዮጵያ” ብዬ የመሰረትኩት።”
   ወ/ሮ አስቴር ስዩም አበራ በዛሬው ዕለት ምስረታው ይፋ በሆነው እናት ኢትዮጵያ መንግሥታዊ ያልሆነ የበጎ አድራጎት ማሕበር ላይ ከተናገረችው የተወሰደ።
   ወ/ሮ አስቴር(ቀለብ በሚለው ስሟም ትታወቃለች) ከ2007 ዓ.ም እስከ 2010 ዓ.ም በአስከፊ እስር በጽናት የቆየች ከመሆኗም በተጨማሪ ከብዙ ውጣ ውረድ በኋላ በጤና፣ በዜጎች መፈናቀል፣ በሰብአዊ መብት መከበር እና በመሳሰሉት በጎ አድራጎት ዙሪያ የሚንቀሳቀሰውን “እናት ኢትዮጵያ” በፕሬዝዳንትነት ትመራለች።
በርቺ በሏት !
እግዚአብሔር ኢትዮጵያን ይባርክ !
Filed in: Amharic