አዲስ አበባን እንደ ቅርጫት,…!!!
ኤርምያስ ለገሰ
አሁን አዲስ አበባ የሁሉም ፖርቲዎች ማዕከላዊ የትግል አቅጣጫ እየሆነች መጥታለች።
ሁለት ቅርጫት ተዘጋጅቷል ፤ አንደኛው ቅርጫት ብልፅግና ያዘጋጀው ሲሆን አላማውም ፦
አዲስ አበባ በሞግዚት ትተዳደር ፥ የራሷ የሆነ ፖሊስ አያስፈልጋትም የኦሮሚያ ፖሊስ በቂ ነው ፥ የአዲስ አበባ ምክር ቤት ተጠሪነቱ እና ተጠያቂነቱ ለጠቅላይ ሚኒስትሩ ይሁን ፥አዲስ አበባ ከንቲባዋን ጠቅላዩ የኔ የሚለውን ሰው አምጥቶ ይሹም…..በሚል በአናሳ ህሳቤ የታጨቀ ሲሆን ባጠቃላይ የራሷ የሆነ ክልል አያስፈልጋትም የሚል እና የአዲስ አበባን ህዝብ የስልጣን ባለቤትነት የማያረጋግጥ ነው……
ሁለተኛው ቅርጫት ደግሞ ባልደራስ ያዘገጀው ነው።
አላማውም አዲስ አበባ በሞግዚት ሳይሆን በመረጠችው ትተዳደር ፥ የራሷ የሆነ ፖሊስ ይኑራት ፥ የአዲስ አበባ ምክር ቤቱ ሙሉ ለሙሉ ተጠሪነቱ ለወከለው የአዲስ አበባ ህዝብ ይሁን ፥ አዲስ አበባ የአዲስ አበቤነት ስነ ልቦና ያለው የራሷን ከንቲባ ትምረጥ ፥ በአጠቃላይ አዲስ አበባ የራሷ ግዛት ይኑራት ራሷን ታስተዳድር የሚል ከፍ ያለ ዓላማን የያዘ እና የአዲስ አበባን ህዝብ የስልጣን ባለቤትነት የሚያረጋግጥ ነው። ስለዚህ ከ 100 በላይ የሆኑ ፖርቲዎች በአዲስ አበባ ጉዳይ ሁለት ጎራ ፈጥረው በእነኚህ ቅርጫት ውስጥ መግባት ጀምረዋል።የተቀሩት ማለትም መንታ መንገድ ላይ የቆሙት በሂደት የት እንደሚጨመሩ የምናያቸው ይሆናል