>

"የአባ ገዳ ባንዲራ ነው" የሚባለው ጥቁር፣ ነጭና ቀይ ምልክት የማን ሰንደቅ ዓላማ ነው?!  ( አቻምየለህ ታምሩ) 

“የአባ ገዳ ባንዲራ ነው” የሚባለው ጥቁር፣ ነጭና ቀይ ምልክት የማን ሰንደቅ ዓላማ ነው?! 

አቻምየለህ ታምሩ 

ፋሽስት ወያኔና ናዚ ኦነግ የኢትዮጵያ አርበኞች በሃይማኖትና በነገድ ሳይወሰኑ ከፍ አድርገው ያውለበለቡትን የኢትዮጵያ  ሰንደቅ ዓላማ ለማደብዘብ ያልቀቡት ጥላሸትና ያልደረቱት የብሔር፣ ብሔረሰብ ተብዮ አርማና ምልክት የለም። ከዚህ በፊት እንደጻፍነው ናዚ ኦነግ ዛሬ ባንዲራዬ የሚለውን አርማ የፈጠረው በማዳጋስካር ሰንደቅ ዓላማ  ላይ ዋርካ በመጨመር ነበር።  ፋሽስት ወያኔ የትግራይ ባንዲራ አርማም   ከነ ትርጉሙ ከቻይና ኮምኒስት ፓርቲ አርማ  የተኮረጀ ነው። ይህንን ታሪክ ፋሽስት ወያኔ ራሱ በግንቦት ወር  1975 ዓ.ም. ያካሄደውን ሁለተኛ ድርጅታዊ ኮንፍረስ ካጠናቀቀ በኋላ ባዘጋጀው ድርጅታዊ ሕገ መንግሥት አንቀጽ ሶስት ንዑስ አንቀጽ አንድና ሁለት ላይ ነግሮናል። ሙሉ ታሪኩን ከነዶሴው በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን።
ዛሬ መጻፍ የፈለግሁት ባለጊዜዎቹ የኢትዮጵያ አርበኞች ሰንደቅ ዓላማን አግደው በአዲስ አበባና በልዩ ልዩ ከተሞች በሚገኙ አደባባዮች፣  የሬዲዮና ቴሌቭዥን ሕንጻዎችና ሚኒስቴር መሥሪያቤቶች በማናለብኝነት እየሰቀሉ ስላሉት በተለምዶ “የአባ ገዳ ባንዲራ” ስለሚባለው ጥቁር፣ ነጭና ቀይ ባንዲራ  ሰንደቅ ዓላማ ታሪክ ነው።
ዛሬ “ኦሮምያ” የሆነውን ስም ለመጀመሪያ ጊዜ ያወጣው በሚሲዮን ስም ወደ ኢትዮጵያ የገባው ጀርመናዊው ሰላይ ዮዋን ክራምፍ ነበር። ይህንን ታሪክ ዮዋን ክራምፍ ራሱ አፍሪካ ውስጥ ለጀርመን ቅኝ ግዛት የሚሆን ምድር ማግኘቱን፣ ይህንንም ምድር ኦርማኒያ ብሎ ስም መስጠቱን “ Travels, Researches and Missionary Labours During an Eighteen Years’ Residence in Eastern Africa”  በሚል ርዕስ በ1861 ዓ.ም.  ባሳተመው የጉዞ ማስታወሻ ገጽ 73 ላይ ነግሮናል። ዮዋን ክራምፍ በጉዞ ማስታወሻው ገጽ 73 ላይ ጨምሮ እንደጻፈው  የቦታ መጠሪያ ስያሜ ለማውጣት የገፋፋውን ምክንያት ሲናገር “ጋሎች ለራሣቸው እና ለሚኖሩበት አካባባቢ አጠቃላይ የወል መጠሪያ ስለሌላቸው ነው” ሲል ነግሮናል። የዮዋን ክራምፍ ተማሪዎች የሆኑት ኦነጋውያን የመንፈስ አባታቸው የሆነው ዮዋን ክራምፍ ያወጣውን የቦታ ስም እየተጠቀሙ የስሙ  ፈጣሪ ራሱ ስሙን ለመፍጠር የተነሳሳው  “ጋሎች ለራሣቸው እና ለሚኖሩበት አካባባቢ አጠቃላይ የወል መጠሪያ ስለሌላቸው” መሆኑን እየነገራቸው  እነሱ ግን  “ከጥንት ጀምሮ ኦሮምያ የሚባለ ምድር ነበረን” በማለት ለመመርመር ፍቃደኛ ያልሆነውን መንጋቸውን ያደነቁሩታል።
ዮዋን ክራምፍ በጉዞ ማስታወሻው ገጽ 76 እና 122 ላይ ለጀርመን መንግሥት ምክር የሰጠ ሲሆን “ኦሮሚያ” ብሎ የሰየመውን የኢትዮጵያ ክፍል መቆጣጠር  ማለት ምሥራቅን እና መካከለኛውን አፍሪቃ መቆጣጠር መሆኑን ያወሳና የጀርመን መንግሥት ዐይኑን ወደዚያ ምድር እንዲያነጣጥር  ምክር ይለግሳል። በገጽ 122 ላይ ደግሞ  “ኦሮምያ” ብሎ የፈጠረውን ቦታ “የአፍሪካ ጀርመን” ሲል ይጠራዋል። ዮዋን ክራምፍ “የአፍሪካ ጀርመን” ሲል በጠራውና ኦሮምያ የሚል ስያሜ ባወጣለት ምድር ውስጥ የሚሲዮን ማዕከላትን ከፍቶ ደቀ መዛሙርቱን አሰልጥኗል።
ክራምፍ ኦሮምያ የሚል ስም በሰጠው ምድር  በተለይም የረር፣ ሙገርና ጫሚ በሚባሉ አካባቢዎች የወቅቱን የጀርመን ኢምፓየር  ባንዲራ መለያቸው ያደረጉ የጀርመን ኢምፓየር የሚሲዮ ማዕከል አቋቁሞ Heathen ነበሩ ያላቸውን አስተምሮ ኦሮምኛ ተናጋሪ “የአፍሪካ ጀርመኖችን” በሱ ቋንቋ civilize አድርጓል። ይህን ታሪክ የነገረንም ዮዋን ክራምፍ ራሱ ነው። ክራምፍ ያሰለጠናቸው ኦሮምኛ ተናጋሪ የአፍሪካ ጀርመኖች ክራምፍ የሰጣቸውን ኦሮሞን “የአፍሪካ ጀርመን” የማድረግ ዓላማ ከግብ ለማድረስ በክራምፍ መጠመቃቸውን ከስልጣኔ ቆጥረውት በኦሮሞ መካከል ሲንቀሳቀሱ  ራሳቸውን እንደ አፍሪካ ጀርመኖች ይቆጥሩ ነበር።  እንዲህም በማሰባቸው የአፍሪካ ጀርመኖች መሆናቸውን ለማሳየት ወገናቸው በሆነው በኦሮሞ መካከል ሲንቀሳቀሱ ያሰማራቸው የጀርመን ሚሲዮን አርማ የሆነውን  የጀርመን ኢምፓየር ሰንደቅ ዓላማ አንግበው  እንደነሱ ያሉ “የአፍሪካ ጀርመኖችን” ለመፍጠር ብዙ ታትረዋል። የፈጠሯቸውን የአፍሪካ ጀርመኖችንም  ከሌላው ለመለየት የጀርመን ኢምፓየር ሰንደቅ ዓላማ ወይም ጥቁር፣ ነጭና ቀይ ቀለማት ያሉት ክር በአንገታቸው ላይ ያስሩባቸው ነበር።
እንግዲህ! ዛሬ ኦነጋውያን የአባ ገዳ ባንዲራ ነው የሚሉን ጥቁር፣ ነጭና ቀይ ቀለማት ያሉት ባንዲራ ክራምፍ የአፍሪካ ጀርመኖችን ለመፍጠር ሲል ያሰማራቸው ደቀ መዛሙርት ኦሮሞን ፕሮሬንታንት ለማድረግ ሲዘዋወሩ ይዘውት ይዞሩት የነበረውን ያሰማራቸው የጀርመን ሚሲዮን ድርጅት መለያ የነበረውን  የጀርመን ኢምፓየር ሰንደቅ ዓላማ ነው። በሌላ አነጋገር ኦነጋውያን የአባ ገዳ ባንዲራ ነው የሚሉን ጥቁር፣ ነጭና ቀይ ቀለማት ያሉት ባንዲራ ክራምፍ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ኦሮምያ በሚል የፈጠረውን አካባቢ  የጀርመን ቅኝ ግዛት ለማድረግ የስለላ ስራ ይሰራ በነበረበት ወቅት  በየሚሲዮኑ ያስፋፋውን የጀርመን ኢምፓየር ሰንደቅ ዓላማ ነው። ይህ የጀርመን ኢምፓየር ሰንደቅ ዓላማ በወቅቱ የጀርመን ኢምፓየር በክራምፍ አማካኝነት ኢትዮጵያ ውስጥ በከፈታቸው የሚሲዮን ማዕከላት ሊውለበለብ ይችል ይሆናል። ክራምፍ ራሱ  የጀርመን ኢምፓየርን ሰንደቅ ዓላማ ኢትዮጵያ ውስጥ በተለይም ኦሮምያ በሚል በፈጠረው አካባቢ ይጠቀምበት የነበረው ለጀርመን ሚሲዮን ቤቶች ምልክትነትና  እንደ ጀርመን በአፍሪካ ምድር ቅኝ ግዛት ለመፍጠር  በሚሲዮን ስም  የተሰማሩ አውሮፓውያን ሲያስሱ የጀርመን ሚሲዮኖችን እንዲለዩበት ነበር። ኦነጋውያን ግን የኦሮሞ አድርገው ከክራምፍ የወረሱት ኦሮምያ በሚል ያወጣውን የቦታ መጠሪያ ብቻ ሳይሆን ክራምፍ  ኦሮምያ በሚል በፈጠረው አካባቢ ያቋቋማቸው ሚሲዮኖች  የጀርመን መሆናቸው እንዲታወቅ መለያቸው ያደረገውን የጀርመን ኢምፓየር ሰንደቅ ዓላማ ጭምር ነው።
በነገራችን ላይ ዛሬ የአባ ገዳ ነው የሚባለው ባንዲራ ከክራምፍ ዘመን በኋላ  አዶልፍ ሒትለርም እንደገና የጀርመን ኢምፓየር ሰንደቅ አላማ አድርጎት የነበረ ሲሆን  የናዚ ፓርቲ  ምልክት የሆነው የስዋስቲካ አርማም የተዘጋጀው ከዚሁ የጀርመ ኢምፓየር ሰንደቅ ዓላማ ቀለማት ነው።
ባጭሩ ኦነጋውያን የአባ ገዳ ባንዲራ የሚሉት ክራምፍ በየሚሲዮን የጸሎት ቤቶች የአፍሪካ ጀርመኖችን ሲፈጥር ይጠቀምበት የነበረውን   የጀርመን ኢምፓየር ሰንደቅ ዓላማ ነው። የጀርመን ኢምፓየርን ሰንደቅ ዓላማ  የአባ ገዳ ባንዲራ አድርገው ለአባ ገዳ ተብዮዎቹ  ጭምር ያስተማሩት ኦነጋውያን በተለይም  የሌንጮ ለታ የቤተሰቦች ናቸው። ራሱን እንደ አባ ገዳ  ልጅ የሚቆጥረው ጃዋር መሐመድ ከዓመት በፊት ከመረራ ጉዲናና ከሌንጮ ለታ ጋር በቴሌቭዥኑ ቀርቦ ሲናገር እንደሰማሁት  ያሳደገው አባቱን [የአባ ገዳን ማለቴ ነው]  ባንዲራ ነው የሚባለውን ምልክት ትርጉም ምን እንደሆነ ያስተማረችው የኦነጉ አምበል  የሌንጮ ባለቤት የሆነችው ኦነጋዊቷ “ፕሮፈሰር” ማርታ ቁምሳ [ማተቧን ከበጠሰች በኋላ “ኩዌ” ሆናለች] መሆኑን ሲናገር ሰምቻለሁ።
እንግዲህ! ጀርመናዊው ሚሲዮን ክራምፍ እንዳለው ኦሮሞ “የአፍሪካ ጀርመን ነው” ካልተባለ  በስተቀር ኦሮሞ ኢትዮጵያ በምትባል ሉዓላዊ አገር ውስጥ እየኖረ  የጀርመን ኢምፓየርን ሰንደቅ ዓላማ የሚያውለበልብበት ምክንያት አይታየኝም። ኦሮምያ የሚባለው አካባቢም የጀርመን ኢምፓየር አካል ነው ካልተባለ በስተቀር የጀርመን ኢምፓየርን እንዲሆን በተሰጠው ስም እየተጠራ የጀርመንን ሰንደቅ ዓላማ  የሚያውለበልብበት ምክንያት ሊኖር አይችልም።
የአባ ገዳ ባንዲራ የሚባለው ጥቁር፣ ነጭና ቀይ  ቀለማት ያሉት ሰንደቅ ዓላማ የጀርመን ሰንደቅ ዓላማ እንደነበር በራሱ ማረጋገጥ የሚሻ ቢኖር  በዮዋን ክራምፍ ዘመን ማለትም በ1860ዎቹና በ1870ዎቹ እንዲሁም በአዶልፍ ሒትለር ዘመን  የነበረውን የጀርመን ኢምፓየር ሰንደቅ ዓላማ  “Old Flag of German”  ብሎ ጎግል ላይ በቀላሉ መፈለግ ይችላል።
Filed in: Amharic