>

"በልደቱ አያሌው ላይ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመፈጸሙ፣  በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንደተደረገ ይቆጠራል" (ተማም አባቡልጉ /የሕግ ባለሞያ/)

በልደቱ አያሌው ላይ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመፈጸሙ፣  በመላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ላይ እንደተደረገ ይቆጠራል”
ተማም አባቡልጉ /የሕግ ባለሞያ/

“በወንጀል ሕግ መርሕ መሠረት፣ የሕግን አግባብ ሳይጠብቁ (With out due process of Law)፣ ሰውን አስሮ ማስቀመጥ አይቻልም። የሰውን ልጅ ከመንግስት የእጅ እልቂት (Abuse) የሚጠብቀው የወንጀል ሕግ ሥነ ስርዓቱ ነው። በወንጀል ሕግ መርሕ፣ በአንድ ሰው ላይ የተደረገ በሁሉም ሰው ላይ እንደተደረገ ይቆጥራል።
 በተደጋጋሚ በአቶ ልደቱ አያሌው ላይ ዋስትና በተመለከተ የፍርድ ቤት ትዕዛዝ አለመፈጸሙ፣ የኢትዮጵያ ሕዝብ በሙሉ እስር ቤት አስሮ፣ ፍርድ ቤት ዋስትና ፈቅዶለት ፓሊስ አልፈትታውም እንዳለው ይቆጠራል።
 በፍትሐ ብሄር ሕጉ ላይ በግልጽ ተቀምጧል። ሰው ዕቃ አይደለም፣ በአደራ አይቀመጥም። ሰውን በአደራ አስቀምጥልኝ አይባልም። ቃሉ በራሱ ነውር፣ ጸያፍና ግብረ ገብነት የጎደለው ነው። ሰውን በአደራ አስቀምጫለሁ ማለት፣ ያለአግባብ እስሬዋለሁ ብሎ ማመን ነው። በአደራ የሚቀመጠው ዕቃ እንጂ ሰው አይደለም። [የፍትሐ ብሄር ሕጉን ስለ አደራ የተጻፈውን ይመልከቱ ] ልደቱ አያሌው መፈታት አለበት።…..”
Filed in: Amharic