>

የሀጫሉ ነገር. . . ?!? (ዳግማዊ አለሙ)

የሀጫሉ ነገር. . . ?!?

ዳግማዊ አለሙ

ያው በሀገራችን ባህል የሞተ ሰው አይወቀስም ብለን ዝም ስንል ይቺን ልጅ በራሳቸው ሚዲያ ክበው ክበው የሌለውን ስም እየሰጡ በግድ ጀግና ካላደረግነው አሉ። እርግጠኛ ነኝ እሱ ራሱ ከሞት ቢነሳ “ይሄ ሁሉ ለኔ ነው?” ብሎ ተመልሶ በድንጋጤ ይሞት ነበር።
ሀጫሉ በትምህርት ዘርፍ ይሄ ነው የሚባል አስተዋፅኦ አላደረገም። በህይወት ዘመኑ ለአንድ ትምህርትቤት አንድ መፅሀፍ ገዝቶ ሰጥቶ አያውቅም። በስሙ ግን  ትምህርት ቤት ተሰይሞለታል።
የአውሮፓ የስእል አድናቂዎች እጅግ የተከበሩ የአለም ሎሬት ሜትር አርቲስት አፈወርቅ ተክሌ የሳሏቸውን ስእሎች በሚሊዮን በሚቆጠር ገንዘብ ለመግዛት ዛሬም ድረስ ይቋምጣሉ። ለሎሬቱ ሀውልት የሌላት ኢትዮጵያ ግን ሁለት አልበም ለሰራው ሀጫሉ ሀውልት ካላቆምኩ ትላለች 🤣
ጥላሁን ገሰሰን የሚያህል የምስራቅ አፍሪካ እንቁ ያላት ሀገራችን ኢትዮጵያ ለሀጫሉ መንገድ ትሰይማለች።
የኢንጅነር ስመኘው አባት ባዘነበለ ጎጆ ውስጥ ሲኖሩ የሀጫሉ ቤተሰቦች አስር ሚሊየን ብር እና ኮንዶሚኒየም  እኔ በምከፍለው ግብር በነፃ ይበረከትላቸዋል።
በሀጫሉ ሞት ምክንያት አንገታቸው እየተቆረጠ የተገደሉ ደመ ከልብ ሰዎች ፍትህ አጥተው ደማቸው ጠረፍ ላይ ሲጮህ መሀል ላይ ለሀጫሉ ፓርክ ይሰራል።
ደብዛው የጠፋው በአሉ ግርማ ሀገሩ ውስጥ አንዲት በስሙ የተሰየመች ጠጠር የለችም… ሀዲስ አለማየሁ ሀውልት የለውም… አበበ ቢቂላ ፓርክ አልተገነባለትም… ስመኘው በቀለ አደባባይ የለውም!
ሀጫሉ ትምህርትቤት አለው! ኮንዶሚኒየም አለው! አደባባይ አለው! ድልድይ አለው! ሀውልት አለው! ዩኒቨርሲቲ አለው! ምክንያቱም . . .
ነጋቲ ቡላ ለማንኛውም!.. ነፍስ ይማር!
Filed in: Amharic