>
5:13 pm - Wednesday April 18, 6294

ዛቻን ማስፋራራት ታግሰን  ለሰላም እንራመድ ! ! !  (አስገደ ገብረስላሴ)

ዛቻን ማስፋራራት ታግሰን  ለሰላም እንራመድ ! ! ! 

አስገደ ገብረስላሴ 

 

የፈደራል  ፈደረሽን ምክር ቤት  በትግራይ ህዝብ ዛቻን እና ማስፋራራት   አይጧን ለማቃጠል ብሎ ቤት ከነቁሳቁሱ ማቃጠል (ማውደም) ይመስላል!?!
    
ይህ  ቡዱን በ110 ሚሊዮን ህዝቦች የተሰጠው ሀላፍነት በመካድ የአንድ የህዝብ ይሁንታ  ያልተቸረለት  ብልጽግና  ፓርቲ ተላላኪ መሆኑ፤  በኢትዮጱያ ህዝቦች የተሰጠው ሀላፍነት በትክክል እየፈጸመ  አለመሆኑ ክህደት ከመሆኑም በላይ ለህዝብ  አላስፈላጊ ጦርነት አውጃለሁ አርፋቹሁ አሜን ብላችሁ ተገዙ በማለት ማስፋራራቱ የህዝብ ተወካይ ነኝ ለማለት ይቻላልን?
በትግራይ ክልል እና ህዝቡ ጊዚያዊ የሽግግር መንግስት ፣ጊዚያዊ  ወታደራዊ አስተዳደር ለመስረት ይቻላል ።እስከ ወታደራዊ   እርምጃ ፣ ወ ዘ  ተ እስከመውሰድም ለመሄድ  ይቻላል በማለት ሲዝት በ7 ሚሊዮን ህዝብ ላይ የፋሽሽታዊው ደርጊ ሌጋሲ በመከተል  በትግራይ ህዝብ ላይ ሞት ፍርድ አይሆንምን ?  ይቻላልስ ? ለመሆኑ ፈደረሸን ምክርቤት የጦርነት አስከፊነት ውጤቱ ይገባዋል ?
ምናልባች ፈደረሽን ምክርቤትም  ዶ/አብይ አህመድ በትግራይ የሚካየደው ምርጫ ከተፈጸመ እርምጃ ይወሰዳል ሲሉ ነበር ፣በተጨማሪም ህጋዊ ላልሆኑ ግለሰዎች ፣ቡዱኖች በመሰባሰብ በትግራይ ወታደራዊ እርምጃ እንዲወሰድ  ወደ ፈደረሽን ምክርቤት ክስ አቅርቡ በማለት  በመወትወት  ፣በመገፋፋት አስከሳሽም ክስ ተቀባይ በመሆን  ህዝብና ተፈላጊ ሰዎች በማይለይ ወታደራዊ እርምጃ እንደሚወስዱ ስያስፈራሩ ከርሟል ። እኔ እሚገርመኝ ፈደረሽን ምክርቤት የሚከተለው ያለ አሰራር የሱ ተልእኮ ነውን ? ትእዝብቱ ለኢትዮጱያ ህዝብ ልተወው ?
ፈደረሽን ምክርቤት ግን ከጥንት ጀምሮ  የባእድ ወረራዎች ሳይቀሩ ወደ ትግራይ ህዝብ የተቃጡ ዱላዎች በየመጡበት እየተቀርጨሙ እንደተመለሱ(እንደተቀበሩ ) በመቐለ  እንዳየሱስ ፣በተንቤን ወርሰገ ወርቃንባ ፣ በሽሬ ሰለክለካ ዓቃብ ሰዓት በደንበርቃይ ፣በእንዳባጉና ፣በሽሬ ዓዲዳዕሮ ፣ ዳብረ ፣በኮዓቲት በጉራዕ ፣በደጓዕለ ፣በሳቡሪ  የተቀበሩ ጠላቶች በማን መሆናቸው የታሪክ መጻህፍቶች ገልጻችኃልን ?  ባጭሩ ፈደረሽን ምክርቤት የቱርክ ፣የጣልያን ፣ የግብጾች  ወራሪዎች የፈጸመው የመከላከል እና የመልሶ ማጥቃት ይቆይና  ፋሽሽታዊ ደርግ በ17 አመት የስልጣን ዘመኑ ከ600 ሽ ክስከ አንድ  ሚሊዮን ቅልብ ወታደር አዝምቶ በትግራይ ህዝብ ተውጠው እንደቀሩት ያውቃልን ? ሌላስ በአሁኑ ጊዜ ወደ ትግራይ የሀገር መከላከያ ሰራዊት አዘምታለሁ ካለ ይህ የህዝብ ሰራዊት በትግራይ ህዝብ ላይ  አንድ ዲንጋይም ይወረውራል ብሎ ይጠብቃልን ? በእውነቱ ያሳፍራል ። የሀገር መከላከያም ሌሎች የጸጥታ ሀይሎችም አያደርጉትም ከህዝብ አብራክ የወጡ ናቸውና ።
ትልቁ ጥያቄ ድግም  ትግራይ ክልል ህዋሓት 98 .6 %አሸነፍኩት ያለበት ምርጫ ከምርጫ ቦር ማቋቋም ጀምሮ ፣እስከ  ከህዋሓት ጋር  የተወዳደሩ ህጋዊ ያልሆኑ  የፓርቲ ስም የያዙ ያደረጉት ምርጫ በሞቶ ሽዎች የሚቆጠሩ ታጋዮች  መስዋት የከፈሉበት ህገመንግስት እንደናዱ አያጠያይቅም ፤ ህገመንግስቱ መናዱ የሚያስጠይቅ ይሆናል ፤
በሌላ በኩል  በዶ/አብይ አህመድ የሚመራ የብልጽግና ፓርቲ ቡዱንም ስልጣን ከያዘበት ጊዜ 6 ወር አከባቢ ወዲህ ሁለት አመት ሙሉ በህገመንግስቱ የተቀመጡ አንቀጽ በአንቀጽ በመናድ (በመርገጥ )በሁሉም የሀገራችን ክልሎች ግጭት ተሰፋፍቶ በስቢል  ማስተዳደር ተስኖች በሁሉም አከባቢዎች ጊዚያዊ ወታደራዊ አስተዳደር በማወጅ በወታደራዊ ሀይል አሸማቅቆ እየጨፈጨፈ እያሰረ ፣እየገደለ ሲገዛ ይታያል ።ትግራይ ክልል ቀርታበት  የነበረች አሁን ወደ ትግራይ  ፊቱ በማዞር  ፈደረሽን ምክርቤት በመሳሪያነት  እንደ ቧንቡላ በመግፋት ጦርነት አውጆ ህዝብ አንበርክኮ የመግዛት ምልክት እንመለከታለን ።ይህ ያዋጣዋል አያዋጣውም  በእኔ እምነት ወደ አያዋጣውም ። እንዳው ወደ የማያባራ ጦርነት ገብቶ ሀገራችን እና ህዝቦቻ ሽግር ላይ ይገባሉ ። ተንኮታኩቶ ያለው ኢኮኖሚያችንም ጨርሶ ይጠፋል ።
ቀጥሎም የትግራይ ንጉሰ ነገስታት የሆኑ የህዋሓት አማራሮች  የዝህች ሀገር እጣ ፈንታ  በራሳቸው ቫዮሎጅካል እድሜ እየለኳት እኔ ከመትኩ ሰርዶ አይብቀል እንዳለቹ አህያዋ ልጆቻቸውና ዘር ዘራቸው ሀፍታቸው ውጭ ሀገር አስፍረው ፤አሁን ላለው የጦርነት ድባብ ወደ ሰላማዊ መፍትሄ ለመውሰድ እንደመሄድ ፈንታ  የጦርነት ነጋሪት ፣ጡርባ በመንፋት የክተት አዋጅ  ሲያውጁ ይታያሉ ። እነዚህ ሰዎች በዝህች ሀገር ይኑሩ አይኑሩ ማሰብ አቁመው እድሜ የማስቀጠል የእግዚአብሄር ፈቃድ ሆኖ ፤ለትውልድ በማሰብ   ወደ ሰላማዊ ውይይት መግባባት ቢሄዱ   ጠቃሚ ይመስለኛል ። ፈረንጆች እኮ ለ1000 አመት ከዛ በላይ  ትውልድ የእድገት ስትራተጅ ይነድፋሉ እነሱ የሚኖሯት ከሞቶ አመት በታች ነው።
 በአንባገነኑ የብልጽግና ፓርት ቡዱንና   በአንባ ገነኑ የህዋሓት የአመራር ቡዱን ያለ የጦርነት ፍጥጫ በምን እናርግበው ?
   1ኛ ይህ አደጋ የአንድ የትግራይ  ክልል  ህዝብ ብቻ ችግር አይደለም በህዋሓት ቡዱን እና በብልጽግና ቡዱን ያለ የጦር ፍጥጫ ከተቀጣጠለ እሳቱ የሚበላው የድሀው  ጭቁን ኢትዮጱያዊ መሆኑ መታመን አለበት ።በመሆኑም ሁላችንም ኢትዮጱያውያን ከወጣት እስከ የሸምግልና   እድሜያለን፣        መሁራን ፣ተመራማሪዎች የሀይማኖት ተቋማት ፣ባለሀፍቶች ፣ነጋዴዎች ጦርነት እልቂት ፣የሀፍት ውድመት ይቁም በማለት አደባባዮች በመውጣት ለሰላማችን እንቅፋት የሚፈጥሩ በግልጽ ተቃውማችን እናሰማ ፤
2ኛ  የሀገራችን ጸጥታ ሀይሎች በሙሉ በአሁኑ ወቅት የፈደራልና የክልሎች ነገስታት የፈጸሙትና እየፈጸሙት ያሉ ገመና ለመደበቅ (ለመሸፈን ) የጦርነት ሴራ በመጠንሰስ ወደ አላስፈላጊ ጦርነት በመጋበዝ ለወላጆቻችሁ  ፣ህጻናት ለወጣቶች ወንድሞቻችሁ እህቶቻችሁ  ለመጉዳት መግባት የለባችሁም ፣ህገመንግስቱን የሚኑዱ የፈደራልና የክልል መሪዎች ህገመንግስት አክብረው እንዲሄዱ  ለመድረግ አቅም መብቱም አላቹሁ ። እስከ አሁንም አንቃላፍታችሁ
3 በሀገራችን ያላቹ ተፎካካሪ ፓርቲዎች አሁን ችግራችን በውይይት በመግባባት እች አገር  በሰላማዊ የሚመራ በሰላማዊ መገድ በገለልተኛ ምርጫ ቦርድ የሚመራ ነጻ ታማኝ ግልጽ ምርጫ በማድረግ በህዝብ ይሁንታ የተመረጠ መንግስት ይቋቋም የሚል እምነት ቀጡሉበት ።ይይ ሁሉ ሊፈጸም በወህን ቤት ያሉ  የተፎካካሪ ፓርቲ መሪዎች አባሎቻቸው፣ደጋፊዎቻቸው በቅድሚያ ይፈቱ።
4 በገዥ ፓርቲዎች ጎን በጥቅም ታሳስራቹሁ በፈደራል መንግስትና በክልልል ንጉሶች እንዲሁም በህዝብ እና መንግስት መካከል ጦርነት ተከፍቶ ፤ህዝብ ከህዝብ  ከተጨፈጨፈ በኃላ ተጠቃሚ እንሆናለን በማለት ለጥቅማችሁ በመሞዳሞድ ለጦርነት ስትገፋፉ የምንመለከታችሁ ቡዱኖች አላቹሁ ። እናንተም ዘላቂ ጥቅማችሁ ከሰላም መሆኑ አምናችሁ ብትታገሱ ያሻችኃል ።
5 የመንግስት ፣የፓርት ፣የግል ሚዲያዎች የዩቲቭ ቻናሎች ፣የፌስ ቡክ ጸሀፊዎች በየአላችሁበት እባካችሁ ለጥቃቅን ጥቅም ተገዝታችሁ ህዝብ ለህዝብ ፣ዘር ከዘር ፤ሀይማኖት ከሀይማኖት ጋር ጠብ ግጭት ከመፍጠር ታቅባችሁ ስለ ሀገራችንና ህዝባችን ብላችሁ ለሰላማ አነሳሱ ።
    ይቀጥላል ፤ 
                     
        መቐለ ፤ 
      24 /01 / 20 12
 
Filed in: Amharic