*******
የኮሮና ቫይረስ/ባለፈው ዓመት የካቲት ላይ በዓለማችን መሰራጨት ከጀመረ ወዲህ፡ ከ 35 ሚሊዮን በላይ ሰዎችን ለህመም፡ በትንሹ አንድ ሚሊዮን 50 ሺህዎችን ደግሞ ለህልፈት ዳርጓል፡፡
ኦፊሴላዊ ዘገባዎች እንደሚያረጋግጡት ዛሬ በምድር ላይ በቫይረሱ ያልተጠቃ አንድም ሃገር የለም፡፡ ኢትዮጵያችን አንዷ ስትሆን / እስካሁን ካጣናቸው ከ1200 በላይ ወገኖቻችን መካከል / ትላንት በ አዲስ አበባ የቀብር ስነስርዓታቸው የተፈጸመው እንቁ የሰብዓዊ መብቶች ታጋይና ታላቅ ምሁር / ፕሮፌሰር መስፍን ወልደ መማሪያም አንዱ ናቸው፡፡ ፕሮፌሰር መስፍን ከ 5 ዓመታት በፊት ለህክምና ወዲህ ወደ ዩናይትድ ስቴትስ ብቅ ባሉበት ወቅት ከቅርብ ወዳጃቸውና የትግል አጋራቸው ከነበረው ጋዜጠኛና ደራሲ / ከአቶ ሙሉጌታ ሉሌ ጋር አረፉበት ሆቴል ልንጠይቃቸው በሄድንበት ጊዜ ለመጨረሻ ጊዜ ለማየት እድሉን አግኝቼ ነበረ፡፡
ሁለቱ ወዳጆች / ከቅርበታቸውና ጥልቅ ትውውቃቸው የተነሳ ይመስለኛል ተቃቅፈው ከተሳሳሙና ሊወርድ የተቃረበ እንባቸውን ካይኖቻቸው ከጠራረጉ በኋላ ወዲያውኑ የፍቅር ብሽሽቅ ነበረ የጀመሩት፡፡
“እንተ ሽማግሌ አሁንም መጮህ አላቆምክም? ብሎ ጠየቀና፣ ሙሌ / ውነትክን ነው / አይጥ ወልዳ ወልዳ ጅራቷ ሲቀር ሲጥ እንዳይሆን / በርትተህ ግፋበት፣ መሄጃችንም ሩቅ አይመስለኝምና፣ / ወደኋላ የለም” አለ፡፡
መስፍኔ መለስ አደረጉና / “ከርቀትም ቢሆን እኮ አንተም አልቦዘንክም ይኸው መጫጫርህን እንደቀጠልክ አይደል እንዴ! በተለይ የቅርብ ጊዜዋ “ሰው ስንፈልግ ባጀን” ስትል ያቀረብካት ጽሁፍ ድንቅ መልዕክት አስተላልፋለች ብዙዎቻችን ወደናታል” አሉት፡፡
ሁለቱ ጉምቱ የሀገርና የወገን ጠበቆች / ትክ ብለው ሲተያዩ ቆዩና / እራሳቸውን በመነቅነቅ “አይዞኝ በህይወት እስካለሁ ድረስ / ትግላችን አይቆምም በሚል ዓይነት / ብሽሽቃቸውን ባጭር ገቱ፡፡
እጅግ አድርጌ በምኮራባቸውና ከልቤ በምወዳቸው በነዚህ ሁለት የወገን ጠበቆች አጭር የቃላት ልውውጥ ተመስጬ ከቆየሁ በኋላ እራሴን መጠየቅ ጀመርኩኝ፡፡ እኔስ ለሃገሬና ለወገኔ ምን አድርጌአለሁ? ስል ጠየቅሁ፡ በቁጭት በእነሱ ቀናሁ፡፡ በመካከላቸው በመገኘቴም ተደሰትኩኝ፡፡
ሙሌ ከሀገር የተሰደደው ወያኔ / ማሰሩና ማዋከቡ ሲሰለቸው፣ የዜና ማደራጃ ቢሮውን ካቃጠለበትና / መኪናውን በካምዮን አስገጭቶ ለመግደል ያደረገው ሙከራ ከከሸፈ በኋላ ነበር፡፡
መስፍኔም / በሽምግልና ዕድሜው በእስር ቤት / ቁም ስቅሉን ሲያይ ቆይቷል፡፡ ከተፈታ በኋላም በለፈው ሳምንት በሞት እስከታለየን ድረስ / አልጋ ላይ ሆኖ / ለወገኖቹ ሲጮህ ቆይቷል፡፡ እና ታዲያ / የሁለቱ ሰዎችህ የዓላማ ጽናት አያስቀናም? እኔስ ያሚል ቅናት አይጭርም?
ጋሼ ሙሉጌታና ፕሮፌሰር መስፍን በነበረው የሀገሪቱ መቅታዊ ሁኔታ ዙሪያ በስፋት ሲያወጉ ቆዩና/ ይዘናት የሄድነውን ምግብ ቀማምሰን ወጣን፡፡ በቅርቡ ተመልሰን ለመተያየት ቃል በመግባት፡፡
አቶ ሙሉጌታ/ የረዥም ጊዜ የቅርብ ወዳጁን በማየቱ በደስታ ይፈነድቃል የሚል ግምት ነበረኝ፡፡ ከሆቴሉ ወጥተን ብዙም አልተጓዝን / ጋሽ ሙሉጌታ ስቅስቅ ብሎ ማልቀስ ጀመረ፡፡ ክፉኛ ደንግጬ / ምን ነካህ ስል ጠየቅሁት፡፡
ሰለሞን አታይም እንዴ? ጓደኞቼ እኮ በሞት እየተለዩኝ ብቻዬን እየቀረሁ ነው፡፡ ይኸው ወዳጄ መስፍንም ታሟል፡፡ እንዳይሞትብኝ ሰጋሁ፡፡ የኔም ጊዜ ደረሰ መሰለኝ ብሎ / አነባው፡፡
“ጋሽ ሙሉጌታ ከመቼ ወዲህ ነው የታመመ ሁሉ ሲሞት የታየው? ዝም ብለህ ነው፡፡ ይልቅ በጸሎትህ እርዳው ምንም አይሆንም ይድናል” ብዬ አጽናናሁት፡፡
ብዙም አልቆየ ነገሩ ፊትና ኋላ ሆነ፡፡ ያ “የኢትዮጵያ ትንሳዔ ደርሷል፡፡ ሀገራችን እና ህዝቧ ነጻ ሊወጣ ነው፡” እያለ / በዚያን ሰሞን ድምጹን ከፍ አድርጎ ሲናገር የቆየው ታላቁ ብዕረኛ ድንገት አረፈ፡፡ አጽሙ እንኳ ለሀገሩ አፈር ሳይበቃ ተሰድዶ በቆየበት ባዕድ ሀገር ተቀበረ፡፡
መስፍኔ በሁኔታው መሪር ሀዘን ቢሰማቸውም / እርሳቸውም ታመው ስለነበር / በጓደኛቸው የቀብር ስነ ስርዓት ላይ መገኘት አልቻሉም፡፡ ስለወዳጃቸው እንዲናገሩ ተይዞላቸው በነበረው መርሃ ግብር ላይም መገኘት ሳይችሉ ቀርተዋል፡፡
እግዚአብሄር የሁለቱን አድባሮች ነፍስ ይማርልን፡፡ እሜን
* * *
ስናወራ አረጀን – ሰው ስንፈልግ ባጀን የምትለውን የጋሽ ሙልጌታን ግጥም ለትውስታ…..
ምስክር
ምስክር…አንድም ማርኮ አይኮራ
…አንድም ጥሎ አይፎክር
…ልቡን የሚገዛ
…ነፍሱን የሚዘክር
…ውድድር ድርድር
…አያውቅም ክርክር
…ቃሉን አያብልም
…ምንም ጆሮው ቢያክር
…ላልቶ አይፍረከረክ
…ጠንቶም አይጠነክር
…የሽረሪት ፈትል
…ቀጭን የጥበብ ክር
…ለአንቀፀ መስቀሉ
… በክርስቶስ ምክር
ወስብሐት ለእግዚአብሔር
ሲገዙን ጎመጀን
ሲሸጡን ጎመጀን
ስናወራ አረጀን
ሰው ስንፈልግ ባጀን…
ብሏል ባለቅኔ ሙሉጌታ ተስፋዬ (አያ ሙሌ)አጃኢብ ነው እናንተው፡አኑቡትማየነቢያት ጉባኤ እሱም ከነቢያት ወገን ነበር እንዴ ያላላቹ፡እንደሆን ቱ ከምላሴ ጸጉር ይነቀል!!!!