>
5:28 pm - Friday October 10, 2053

"የሕዝብ ሐብት አለአግባብ የማደልና የመቀራመት ዝንባሌ ይታረም" (አቶ ሙሼ ሰሙ)

“የሕዝብ ሐብት አለአግባብ የማደልና የመቀራመት ዝንባሌ ይታረም”

ቶ ሙሼ ሰሙ

ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በሕዝብ ስም ምሎና ተገዝቶ የተገኘን ስልጣን ተገን እያደረጉ፣ ያለአንዳች ሕጋዊ አሰራርና የጋራ አመራር ውሳኔ፣ የመንግስትን፣ የሕዝብና የጋራ ሀገራዊ ሀብት በስጦታና በልግስና ማደልና መቀራመት ባህል እየሆነ እንደመጣ እየታዘብን ነው። በመርህ፣ በሞራልም ሆነ በሕግ አግባብ  የትኛውም የፓለቲካ ተሿሚ ወይም ባለስልጣን በሕግ ከተሰጠው ሀገርን በእኩልነት የማስተዳደር ስልጣን ውጭ የመንግስትንና የሕዝብን ሀብት በችሮታና በልግስና ለማደል የሚያስችል ማዕረግ የለውም፣ ሊኖረውም አይገባም።
የፓለቲካ ተሿሚና የስልጣን ተቀናቃኝ ሁላ ይጠቅመኛል ብሎ ካመነበት ከሾመው የፓርቲ ካዝና ሀብት እየቀነሰ ማደል ይችል ይሆናል እንጂ የግብር ከፋዩን ሕዝብ ሀብት ለፈቀደውና ለወደደው ግራና ቀኝ መርጨት በጊዚያዊ ጉልበት እየታገዙ ካልሆነ አይገባም፣ አይፈቀድም። ስልጣን ላይ የተሰየመ ሃይል በሰበብ አስባብ የመንግስትንና የሕዝብን ሀብት ማደል መብት አድርጎ ከወሰደው፣ ሲሾም ያልበላ ሲሻር ይቆጨዋል፣ የሀገርን ሀብት መቀራመት የትግላችን ዋጋ ነው ሲሉ ከነበሩት ሀይሎች በመፈክር አወጣጥ ተለየ እንጂ ከትናንቱ ስህተት የተማረውም ሆነ ለእኩልነት የተዘጋጀ መሆኑን አያመክትም። ይህ ደግሞ የመከባበር፣ ሳይሆን የመበተን ጎዳና መሆኑ ሳይታለም የተፈታ ነው።
የሕዝብ፣ የመንግስትንና የሀገርን የጋራ ሀብት ያለ ሕጋዊ የጋራ ስምምነት ማካፈልም ሆነ መካፈል አይቻልም። መጀመርያ የተሰራውን ስህተት በራሱ ሚዛን ፈትሾ ከቀጣይ ስህተት እራስን ከማቀብ ይልቅ ሌላ ተመሳሳይ ስህተት በመፈጸም ስህተትን በስህተት ለማረም መሞከር ከሀቅ ለመሸሽ ሲሉ ጥፋትን ከመደራረብ፣ ከእውነታውና ከሀቅ ከመሸሽ ውጭ መፍትሔ ሊሆን አይችልም። ለነገ ሲባል እየተስተዋለ !!!
Filed in: Amharic