“የእኛ እስር ረጅም አይሆንም…ውስጤ የሚነግረኝ ይህንን ነው…!!!”
እስክንድር ነጋ ከቤተሰቡ ጋር ዛሬ በስልክ ሲገናኝ የተናገረው
ሰርካለም ፋሲል (ባለቤቱ)
እስክንድርን በስልክ አሁን ጠዋት 9:00 በዲሲ አቆጣጠር አገኘሁት። ከቤተሰብ ሰላምታ በመቀጠል ክሱን እንዴት ታየዋለህ?…ከእነ ማን ጋር ነው ያላችኹት ብዬ ለጠየኩት ይችን አጭር ምላሽ ሰጥቶኛል:-
“ክሳችን አንዲትም ዕውነት የላትም። ውሸት ደግሞ ሁልግዜ አሸንፋ አታውቅም። የእኛ እስር ረጅም አይሆንም። በዚህ አይዘልቁበትም-ውስጤ የሚነግረኝ ይህንን ነው። የሚሄዱበት መንገድ የሚያዛልቅ አይደለም።
ከግዜያዊነት ባለፈ አይዘልቁበትም(እየደጋገመ የተናገራት ቃል) ያለሁት ከስንታየሁ ጋር በፊት የታሰርኩባት ክፍል ውስጥ ነው። ግቢ ውስጥ
አብረን ያለነው አብዲ አሌ(የቀድሞ የሱማሊያ ክልል ፕሬዚዳንት) ሜጀር ጀነራል ክንፈ ዳኘው እና የደህንነት ኅላፊው ያሬድ ዘሪሁን ጋር ነው” ..
ከእነሱ ጋር ትነጋገራላችኹ? ስል ጠየኩት… እንደመሳቅ ብሎ “በደንብ ነዋ” አለኝ!!.
በመጨረሻም ለማውቃቸው በሙሉ ሰላምታ አቅርቢልኝ ብሎኛል። የሚያውቃችኹ ሰላም ተብላችኅል።
ጥቅምት 2/2013