>
5:28 pm - Friday October 10, 2887

"መስቀል አደባባይን ለእሬቻ፥ባሕረ ጥምቀትን ለመጫወቻ...!!!" ( ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው)

“መስቀል አደባባይን ለእሬቻ፥ባሕረ ጥምቀትን ለመጫወቻ…!!!”

ቀሲስ ደጀኔ ሽፈራው

* “ከአሁን ቀደም ይህን ቦታ የሚዘሉበት ሌሎች ነበሩ፥ አሁን ግን ለባለቤቱ ተመልሷል!”
የኦሮምያ ቤተ ክህነት ነኝ፤”ባዩ አቶ በላይ
 
*“ዘንድሮ ይኸንን ቦታ ተረክበናል፥ በዚህ አናበቃም፥ በሚቀጥለው ዓመት አዲስ አበባን እንረከባለን!”
  “የአምናው ኢንቨስተር የዘንድሮው ስደተኛ” ወርቁ ደያስ 
 
      የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያንን ጉዳይ እንደ እግዜሩ ተስፋ ባንቆር ጥም እንደ ሰዉ ተስፋ አስቆራጭ ነው።የቀድሞው ከንቲባ ኢንጂነር ታከለ ኡማ አዲስ አበባ ላይ ባልጠፋ ቦታ መስቀል አደባባይ አጠገብ የእሬቻን ቦታ በልዩ ኹኔታ ገንብቶ ሲያ ስረክብ ዓላማው፦የቤተ ክርስቲያኒቱን ጥንታዊ ይዞታ ለሌሎች አሳልፎ የመስጠት ነበር። በመስከረም ፪ሺ፲፪ ዓ.ም. የእሬቻ በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ በአዲስ አበባ ላይ ሲከበር የጃዋር ቴሌቪዥን የኦ ኤም ኤን “ጋዜጠኞች” እየተዘዋወሩ ቃለ መጠይቅ ባደረጉበት ጊዜ፦”የኦሮምያ ቤተ ክህነት ነኝ፤”ባዩ አቶ በላይ፦”ከአሁን ቀደም ይህን ቦታ የሚዘሉበት ሌሎች ነበሩ፥ አሁን ግን ለባለቤቱ ተመልሷል፤”ማለቱን አስታውሳለሁ።ከእርሱ አጠገብ ተቀምጦ የነበረው  “ባለጠጋው” ወርቁ ደያስ ደግሞ፦”ዘንድሮ ይኸንን ቦታ ተረክበናል፥ በዚህ አናበቃም፥በሚቀጥለው ዓመት አዲስ አበባን እንረከባለን፤”
ሲል በእርግጠኝነት ተና ግሮ ነበር።አዲሷ ከንቲባ ወይዘሮ አዳነች አቤቤም፦”ፍየል ከመድረሷ፥ቅጠል መበጠሷ፤” እንዲል፦የይዞታ ማረጋገጫ ካርታውን ለባለ እሬቻዎቹ በተሾመችበት ማግስት አስረክባለች ።ለነገሩ እነርሱ ሥልጣኑን እንደ ዱላ ቅብብል ሯጮች እየተቀባበሉ ሥራቸውን እየሠሩ ነው ።
        እውነት ለመነጋገር የመስቀል አደባባይ ይዞታ ባለቤቶች እኛ ብንሆንም በእኛ ባለቤት ነት ለመቀጠሉ እርግጠኞች አይደለንም፥ምክንያቱም የይዞታ ማረጋገጫ ካርታ አልተሰጠ ንም።የእሬቻው ካርታ ከግዮን ሆቴል ጀርባ ቢሆንም ዓላማው ያንን ይዞ መስቀል አደባባ ይን መጠቅለል ነው።ሌላው የሚያበሳጨው ነገር ደግሞ የጃንሜዳ ጉዳይ ነው።የአትክ ልትና የፍራፍሬ ገበያ ሆኖ መቆሸሹ ሲገርመን የይዞታ ማረጋገጫ ካርታው ለስፖርት ኮሚ ሽን ተሰጥቶአል።በዚህ አይነት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶ ቤተ ክርስቲያን ባለፉት ሠላሳ ዓመታት አያሌ ይዞታዎቿን ተነጥቃለች።የዛሬው ካለፈው የቀጠለ ነው።ስለዚህ ቅዱስ ሲኖዶሱ በዚህ ጉዳይ ላይ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ ተነጋግሮ ጠንከር ያለ ውሳኔ መወሰን አለበት።ከዚህም ጋር ውሳኔውን ተከታትሎ የሚያስፈጽም ኮሚቴ ማቋቋም ይጠ በቅበታል።እኛ ቀድመን ሥራችንን ባለመሥራታችን እነርሱ ከፊት እየቀደሙ የቤት ሥራ እየሰ ጡን ነውና።
Filed in: Amharic