>

“ኦሮሞ ካልሆንክ አታድግም፤ አትሾምምም!” (አምባቸው ደጀኔ)

“ኦሮሞ ካልሆንክ አታድግም፤ አትሾምምም!”

አምባቸው ደጀኔ


ይሄ ድቅድቅ ጨለማ እስኪነጋ ስንትና ስንት ጉድ ተቆልሎ በየቀኑ ዕይታችንን እንደሚያደበዝዝ ወይ እንደሚጋርድ አላውቅም፡፡

አንድ ወቅት አንድ ጸሐፊ ወዳጄ “ፂላ ካልሆንክ አትሠራም” በሚል ርዕስ አንድ መጣጥፍ ጽፎ በዚሁ በድረገጽ ማንበቤ ትዝ ይለኛል፡፡ እኔም ከርሱ ኮረጅኩ፡፡ ከቀሪ እንስሳት በእጅጉ እንደሚበልጥ የሚታመንበት የሰው ልጅ ሠልጥኖ የትና የት በደረሰበት በዚህ የኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ዘመን የኛ የፕሪካምፕሪያን ዘመን (Precambrian Era) የአውስትራሎፒቴከስ (Australopithecus)  ዝርያ ሰው መሳይ ዝንጀሮዎች ምን እየሠሩ እንደሆነ ጥቂት ላውጋችሁ፡፡ የሰው ሰውነቱ የሚረጋገጠው በግብሩ እንጂ በቅርጹ እንዳልሆነ እነዚህ ከዝንጀሮም ያነሱ ፍጡራን እያስመሰከሩ ነው፡፡ የትምህርት ትርጉም “የአስተሳሰብና የአመለካከት እንዲሁም የባሕርይ ለውጥ ማስገኘት ነው” የሚለው ነባር እሳቤ በነሱ ቤት በፍጹም አይሠራም – ለዚህም እንደዋቢ ዋናውን የደናቁርት አለቃ “ዶክተር” ገመቹ መገርሣን ጨምሮ እንደሕዝቅኤል፣ ፀጋየ፣ ሽመልስ አብዲሣ፣ አቢይ አህመድ፣ ጃዋርና የመሳሰሉትን እንስሳት ማየት ነው፡፡ እግዜሩም ሰውም ይቅርታ ያድርጉልኝና ከነዚህ “ምሁራን” ተብዬዎች ይልቅ የለዬለት ከብት ይሻላል፡፡ ወደፍካሬያዊ ፍቺ ገብታችሁ ያልተገባ ትርጉም በመስጠት ፀጉር ስንጠቃ ውስጥ መግባት የለባችሁም፤ ነገሬና ጥሌ አክራሪ ኦሮሞዎችና ወያኔዎች ጋር ብቻ ነውና፡፡ በነባሩ ብሂል  “እግዚአብሔር ያሳያችሁ፣ ክርስቶስ ያመላክታችሁ” እንደምንለው  መቼም እነዚህ ከእንስሳም የወረዱ ዐረመኔዎች ሰው ቢሆኑ ኖሮ “ቤንሻጉል ጉሙዝ 37 በመቶ ኦሮምኛ ይነገራል፤ ሐረርንና ሶማሌን ተቆጣጥረናቸዋል፤ አማርኛን ገድለነዋል….” እያሉ በአደባባይ አይናገሩም በድርጊትም አማራን በተገኘበት አያስጨፈጭፉም ነበር፡፡ እነሙሃዘ ጥበባት ዲያቆን ጋንኤል ክብረትና ነቢዩ ባዬ የተባሉት ጉዳጉዶች እንግዲህ ከነዚህ ብኤል ዘቡሎች ጋር በመተባበር ነው የአማራን ዕልቂት እያቀነባበሩ ያሉት፤ ብአዴንስ አንዴውኑ ለይቶለት የወያኔና ኦህዲድ ኮንዶም መሆኑ ይታወቃል፡፡ ብዙ የሚያሣፍሩ ዜጎችነና ብዙ የሚያሣፍሩ ድርጊቶችን እየመዘገብን ነው፡፡ ሁሉም ዋጋውን እስኪያገኝ የችግራችን ጣርያ ለከት አጣ፡፡ እግዜሩ ሥራችንን አይቶ ጨከነ፤ እኛመ ከርሱ ራቅን፤ ስለዚህ የማይቀረው የነፃነታችን ዘመን በየሰበብ አስባቡ መዘግየቱና ከአንዱ እሳት ወደሌላውና ወደባሰው እሳት መግባታችን አሳዛኝ ዕጣችን ሆነ፡፡ 

ከሁለት ዓመታት በፊት በነበረው የሕወሓት መንግሥት ትግሬነት ከወርቅና ከዕንቁ በላይ ነበር፡፡ ትግሬ መሆን ከሎተሪም፣ ከኮንዶምንየምም፣ ከመሬትም፣ ከገንዘብም፣ ከእግዜርም፣ ከአላህም፣ ከቡድሃም፣ ከሂንዱም… የሚበልጥ ነበር፡፡ አንድ የጎሣ ስብስብ ጨርቁን ጥሎ እንዲህ ሲያብድ ማየት ስምአልባ አግራሞትን ይፈጥራል፡፡ ብዙውን ነገር ሲመለከቱት የእውነት አይመስልም፡፡ ለምንም ጥቅም ይሁን አፍ ያልፈታችን ሕጻን ከእናቷ አንቀልባ አውርዶ ከነእናቷ የሚያርድ ጭራቅ በኢትዮጵያ ቀርቶ በየትም ይኖራል ተብሎ አይጠበቅም፡፡ ይህ እየሆነ ያለው ደግሞ የአኩኩሉ ጨዋታውን በልጅነቱ ያልጠገበው አቡሽዬ በሚመራት ኢትዮጵያ ውስጥና አሁን ነው፡፡ቁጥር ሥፍር የሌለው ጉድ እየታዘብን ነው – የሚያሣዝንም የሚያስፈግግም፡፡

ደጋግ ኦሮሞዎች በምለው ቅር እንደማትሰኙ እገምታለሁ፡፡ የዛሬ ሁለት ዓመት ገደማ ሙልጭ ያለ ድሃ ምናልባትም ጎዳና ተዳዳሪ የነበረ ኦሮሞ አሁን ዕድሜ ልኩን ቆጥሮ የማይጨርሰው የብዙ ሚሊዮን ብር ጌታ ነው፡፡ በቄሮ ስም የነገደውና በእውኑ ቀርቶ በህልሙ ያላሰበውን ገንዘብ እያከማቸ የሚገኘው ኦሮሞ እጅግ ብዙ ነው፡፡ ለአንድ ብልጣብልጥ ቄሮ አንድ ዲፎርዲ የሕዝብ ማመላለሻ መኪና በጣም ተራ ነገር ነው፡፡ ከነውጡ ማለትም ከለውጡ  በፊት የአንድ ዘመዴ ተላላኪ የነበረ አንድ ወጣት አሁን ቢጠሩት የማይሰማ ቱጃር ነው፡፡ በወያኔ ዘመን ከሽሬ ሲጓዝ አድሮ አዲስ አበባ ሲደርስ የአንድ ብቻ ሣይሆን የብዙ ኮንዶምንየም ቤቶች ባለቤት ይሆን እንደነበረው ሁሉ ዛሬ ደግሞ ከጊምቢና ከአምቦ በሰዓታት ውስጥ ተጉዞ አዲስ አበባ ይገባና የሚሊዮን ብሮች ጌታ ይሆናል – “ዕድለኛ” ባለጊዜ፡፡ በትምህርት ረገድ እነዚህ ሰዎች ቢፈተሹ ምናልባት ብዙዎቹ ማንበብ መጻፍ ቢችሉ እንጂ ድፍን ማይማን ናቸው፡፡ የማይምነት ዋነኛ ግንኙነት ደግሞ ከንዋይ እንጂ ከፍትኅና ከጥበብ ጋር አይደለምና ያኔ አገር ትፈርሳለች፡፡

ትናንት እንዲህ ገጠመኝ፡፡ ለአንድ የማውቀው ሰው ደወልኩ፡፡ “በመሥሪያ ቤታችሁ እንትና አለ ወይ?” ብዬ ጠየቅሁት፡፡ “ተሾሞ ወደ ሌላ ቦታ ተዛውሯል” አለኝ፡፡ የምጠብቀው መልስ ነበርና “ጉርሜሣ መሆኑ ጠቅሞታላ!” ብዬ ቀለድኩ፡፡ እርሱም ከት ብሎ ሣቀና ለቀጣይ ጥያቄየ የርሱን ባለበት ቦታ መጽናት ነገረኝ፡፡ ጥያቄየን ቀጠልኩ፤ “አለቃችሁ የነበረው ‹አገሩ አበረ›ስ እንዴት ነው?” አልኩት፡፡ “እርሱ ከሹመት ወርዶ በተራ ሠራተኝነት ወደ ሌላ ቦታ ተዛውሯል” አለኝ፡፡ ብዙ ጥያቄዎችን ጠየቅሁ – ያገኘሁት መልስ ግን እጅግ የሚሰቀጥጥ ነው፡፡ ኦሮሞዎች አልተቻሉም! መጨረሻውን ያሳምርላቸው፡፡ እዚህ ላይ ግን በትግሬዎቹ ዘመን ብዙ መልካም – ሣምራውያንና ሣምራውያት – ትግሬዎች እንደነበሩና በደናቁርቱ ዕኩይ ተግባር ይተክዙና ያፍሩም እንደነበር ሁሉ አሁንም በዚሁ ሁኔታ በርካታ ውሁድና ውሁድ ስለመሆናቸው የማያውቁ ኦሮሞዎች በነዚህ ኦነግ/ኦህዲዳውያን ሀገርን የማፍረስ ሥራ እንዴት እንደሚናደዱና እንደሚያፍሩ መገመት አይከብድም፡፡ ዱሮ የመንግሥት መሥሪያ ቤት ቋንቋ ትግርኛ እንደነበረው አሁን ደግሞ ኦሮምኛ ሆኗል፡፡ ችግሬ የቋንቋው አይደለም – በጭራሽ! የኔ ችግር አለዕውቀትና አለትምህርት በዘር እና/ወይም በሃይማኖት መሥፈርት ብቻ እየተጠራሩ ሌላውን ባይተዋርና በገዛ ሀገሩ ባዕድ ማድረጋቸው ነው፡፡ ይህም ብቻ ሣይሆን ጥቅማችንን ይቀናቀናል ወይም ይቃወመናል የሚሉትን ሁሉ በፈጠራ ክስና በህገወጥ ግድያ ድራሹን ማጥፋታቸውም ነው፡፡ ዕውቀት ከሌለ ፈሪሃ እግዚአብሔር የለም፤ የሞራል አጥር የለም፤ ባህልና ወግ የለም፡፡ ዋናው ገዢ ሆድና ሥጋዊ ፍላጎት ብቻ ነው፡፡ እንጂ በብቃትና በችሎታ ከሆነ ሁሉም ሹም ኦሮሞ ወይም ጉራጌና ከምባታ ቢሆን ጉዳየ አይደለም፡፡ እውነቴን ነው! (አምስት ስድስት ትራፊክ ፖለሶች ሰብሰብ ብለው ብታይ ሁሉም በኦሮምኛ ነው የሚያወሩት፤ ስላየሁ ነው፡፡ ይህ አጋጣሚ ከሆነ ፍርዱ የናንተው ነው፡፡) አዲስ አበባ ያለች ትመስላለች እንጂ የለችም – ለይምሰል “የሁሉም ናት” ይባላታል እንጂ ኦህዲድ ተቆጣጥሯታል፡፡ አቢይ ጭምብል ነው፡፡ 

ማሙሽ ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ ሀገር በአንበጣና በእምቦጭ ተወርሮ፣ ዘረኝነት ባመጣው ጦስ ጥምቡስ የሕዝብ የእርስ በርስ ዕልቂት ከፊታችን ተደቅኖ፣ ወያኔና ኦህዲድ በአማራው ላይ ባወጁት የዘር ማጽዳትና የዘር ፍጂት (Ethnic cleansing  and genocide) ሳቢያ በመተከልና በኦሮሞ አካባቢዎች አማሮችና ኦርቶዶክስ ክርስቲያኖች አንገታቸው እየተቀላ …. ማሙሽ በመዝናኛ መናፈሻዎች ከቢጤዎቹ ጋር ይቦርቃል – መቦረቁን ይቦርቅ – መብቱ ነው፤ ግን ጊዜው አይደለም፤ መጸዳጃ ቤት ውስጥ ቁጭ ብሎ ምሣውን ወይ እራቱን የሚበላ ካለ እንደአቢይ አህመድ ለይቶለት ቀውሷል ማለት ነው፡፡ ዝንጀሮዋም እኮ ነፍስ አውቃ “የትኛውን እሾህ እንንቀልልሽ?” ብለው ሲጠይቋት “ቀድሞ የመቀመጫየን” ነው ያለችው፡፡ ታዲያ አንድ የሀገር መሪ መላውን የሀገሩን ሕዝብ ለርሀብ የሚያጋልጥ አምበጣ አገር ምድሩን ወርሮ ያገኘውን አረንጓዴ ቅጠል ሁሉ እየረመረመ ባለበት ቅጽበት እንደሞኝ እየሣቀና አሽከር ገረዱን እያስጨበጨበ በሕጻናት መኪና ሲታይ በትንሹ ማሙሽ ብሎ ከመጥራት ውጪ ሌላ ምን ሊባል ይችላል?  ለስሙ ክርስቲያን ነኝ ይል የለምን? “መጽሐፈ ምሣሌ ምን ይላል?  ክርስቶስስ ምን ይላል?” ብላችሁ ጠይቁት የምትቀርቡት፡፡ “ ወደ ሠርግ ቤት ከመሄድ ወደ ልቅሶ ቤት መሄድ ይሻላል፤ ባለጠጋዎችን ግብዣ ከመጥራት ምንዱባንንና ያጡ የነጡትን መጋበዝ ይሻላል፤ አጠገቡ ያለውን የሚያየውንና የሚያውቀውን የሚጠላ ወይንም የማይወድ እኔን የማያውቀኝንና የማያየኝን ሊወድ አይችልም፤ ባልንጀራህን እንደራስህ ውደድ፤  አትግደል፤ አትስረቅ፤ አታመንዝር፤ በሀሰት አትመስክር……” የሚለው የአምስትና አሥር ሚሊዮን ብር እራት የሚያሰናዳው ቅንጡው አቢይ አህመድ ሣይሆን እመራበታለሁ የሚለው መጽሐፍ ቅዱስ ነው፡፡ ማሞ ሌላ መታወቂያው ሌላ፡፡ ይህንንም ለነጋንኤል ክብረት ንገሯቸውና ይንገሩት፡፡ በጌታ ቤት ቁማር የለምም በሉት፡፡

 ልጁ ልጅነቱን ሳይጨርስ ለዚህ ኃላፊነት መብቃቱ ነው ትልቅ ችግር የደቀነብን – ደግሞም እናቱ ናቸው ጥፋተኛ፤ ያንን የሰባተኛ ንጉሥነት ትንቢት ነግረው ጉድ ሠሩን! እርሱንም ለቅዠት ዓለም ዳርገው ዕረፍት ነሱት፡፡ እናም ሰው እያለቀ፣ እምቦጭ የውኃ አካላትን እያደረቀ፣ ሸመልስ አብዲሣ አማራን እየረፈረፈ … እርሱ ግን እንጦጦ መናፈሻና ጂማ ከቤቢሲተሮቹና ከአለቆቹ አለቃ ጋር ጮቤ ይረግጣል፡፡ (በዛሬው ዕለት ራሱ 21 አካባቢ አማሮች እንደተገደሉ አሁን እየተነገረ ነው – እርሱ ግን ምንተዳው! ከአንድ ጎምቱ ወፈፌ ጋር አሼሼ ገዳሜ ይላል፤ ጓደኛው እርሱ ብቻ ሆኖ ቀረ ማለት ነው – “ዚአከ ለዚአየ” ማለት ይሄኔ ነው)፡፡ አቡሽዬ ሲፈልግ እንጀራ ይጋግራል – ጋጋሪ ጠፍቶ፡፡ ማሙሽ ካሰኘው አትክልት ይኮተኩታል – ኮትኳች ጠፍቶ፡፡ ማሙዬ ሲሻው አትክልት ያጠጣል – አጠጪ ጠፍቶ፡፡ አቡዬ ሲፈልግ ትራፊክ ፖሊስ ይሆናል – ትራፊክ ፖሊስ ጠፍቶ፡፡ አቡጡ ሲሻው ፓይለትና ሆስተስ ይሆናል – ፓይለትም ሆስተስም ጠፍቶ፡፡ አቢቲ ከፈለገ ታክሲ ነጂና ወያላ ይሆናል – ታክሲ ነጂና ወያላ ጠፍቶ፡፡ ብቻ ምን አለፋችሁ የማይሆነው የለም፡፡ የሥነ ልቦናና የሥነ አእምሮ ተመራማሪዎች ትልቅ የቤት ሥራ አገኙ፡፡ በሉ መጻሕፍትን ገልበጥ ገልበጥ አድርጉና በዚህ ሰው ማለቴ በዚህ ልጅ ላይ አንዳች ነገር ጣል አድርጉልንማ፡፡ በነገራችን ላይ ይህችን ጽሑፍ ጀምሬ በመሃል ድረገፆችን ስዳስስ በኢትዮሪፈረንስ ላይ ስለ `Narcissist Personality Disorder` አንድ ግሩም ጽሑፍ አነበብኩ፤ ጋበዝኳችሁ፡፡ https://www.ethioreference.com/archives/24665

Filed in: Amharic