>

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቁጥራቸው የበዙ ፖሊሶች ከቢሮ ወሰዱት! (ታሪኩ ደሳለኝ)

ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ቁጥራቸው የበዙ ፖሊሶች ከቢሮ ወሰዱት!

ታሪኩ ደሳለኝ

ዛሬ ከቀኑ ስምንት ሰዓት አካባቢ ቁጥራቸው የበዙ ፖሊሶ ፍትሕ መጽሔት ወደሚገኝበት ቢሮ ከደረሱ በኋላ ተመስገን ደሳለኝን የት እንዳለ ጠየቁ። በወቅቱ እርሱ ቢሮ ውስጥ ስላልነበረ አዘጋጁ ወደ ተመስገን ደወለ። ከፖሊሶቹ ውስጥ አንዱ የአዘጋጁን ስልክ ተቀብሎ፤ እንደሚፈልጉት እና የት እንደሚገኝ ጠየቀው። ተመስገንም ይዘው የመጡት መጥሪያ ወይም ክስ ካለ ቢሮ አስቀምጠው እንዲሄዱ ነገራቸው። የሚያናግረው ፖሊስ ግን የሚፈልጉት እርሱን እንደሆነና ያለበትን እንዲነግራቸው ጠየቁት። እርሱም “ግድ የለም እኔን ከፈለጋችሁኝ ቢሮ እመጣለሁ” የሚል ምላሽን ሰጥቶ ወደ ቢሮው ተመለሰ። እንደደረሰም፤ ተዘጋጅተው እየጠበቁት ስለነበር ጭነው ወሰዱት።

 

 

Filed in: Amharic