>

"ታሪክ እንደሚያሳየው የህዝበኛ አመራሮች መጨረሻ መዋረድ፣ መሰየፍ፣ መታሰር ነው!" (ኢ/ር ይልቃል ጌትነት)

“ታሪክ እንደሚያሳየው የህዝበኛ አመራሮች መጨረሻ መዋረድ፣ መሰየፍ፣ መታሰር ነው!” 
   ኢ/ር ይልቃል ጌትነት

ከታሪክ እንደምንረዳው በጣሊያን ቬኑስን ወደ ቀደመ ገናናነቷ እመልሳለሁ፣ አፈርንም ወደ ወርቅ እለውጣለሁ የሚል አንድ መሪ በ15ኛው ክ/ዘመን መጥቶ ነበር። ህዝብንም አሳምኖ መሪ እስከመሆን ደረሰ።
ሰውዬው ወደ ሀላፊነት እንደመጣ ምንም ለውጥ ጠፋ። ህዝቡም የታለ አፈሩን ወደ ወርቅ ቀይረህ ታሪካችንን የለወጥከው? ብሎ ጠየቀ። ጊዜ ስጡኝ። ብዙ ጊዜ ከሰጣችሁኝ ብዙ ወርቅ ታገኛላችሁ፣  ትንሽ ጊዜ ከሰጣችሁኝ ግን ትንሽ ወርቅ ነው የምሰጣችሁ በማለት ማታለል ጀመረ። በሗላ ተስፋው ሁሉ ጉም መጨበጥ ሆኖ ቀረ።
ዶክተር አብይ አህመድም ወደ ስልጣን እንደመጣ ሌላውን ብንተወው እንኳን፣ ነዳጅ አውጥቼ ኤክስፖርት አደርጋለሁ ብሎ አስጨፍሮ ነበር። የማይጨበጥ ሆኖ ቀረ። ብልፅግና እድል ቢሰጠውም አይጠራም፣ ሀገሪቷን ያሟሟታል እንጂ። ፓርቲው የስነ ልቦና ቀውስ ያለባቸው ሰዎች ስብስብ ነው። በማስመሰል የሚኖር ነው።
በዚህ ስርዓት እየተጠቀመ ያለው ቡድን አሁንም የበለጠ ለውጥ ይፈልጋል። ከዚህ በላይ ሌሎችን መጨቆን፣ ታሪክን ማጥፋት፣ ቤተ ክርስቲያንን ማቃጠል ይፈልጋሉ። የሚያሳዝነው ይሄ ሁሉ ጉዳት የሚደርስበት አማራ ደግሞ የባሰ አታምጣ ብሎ ተቀምጧል። በግሌ የባሰ አታምጣ የሚለው አባባል ለሀይማኖት እንጂ፣ ለፖለታካ አይጠቅምም ባይ ነኝ።
(ኢ/ር ይልቃል ጌትነት – ለአሀዱ ቲቪ የተናገረው)
Filed in: Amharic