>
5:18 pm - Friday June 14, 4391

እንግዲህ ፓትርያርኩም ም/ጠ/ምኒስትሩም "ተደራጁ" ብለዋችሗል...!!! (ዘመድኩን በቀለ)

እንግዲህ ፓትርያርኩም ም/ጠ/ምኒስትሩም “ተደራጁ” ብለዋችሗል…!!!

 
ዘመድኩን በቀለ
 
• እኔን እንደ እብድ ብቻዬን የሚያስጮኸኝ እናንተንም እስቲ ያስጩሃችሁ። እኔን እና ጥቂቶችን ብቻ እንቅልፍ የሚያሳጣኝ እስቲ እናንተም ሞክሩት። ዐማራ ዘሩ እንዴት እየጠፋ እንዳለ ከጅምላ እርዱ ተመልከቱ።
 
• ኢሳያስ አፈውርቂ የመጣው የመተከሉን እርድ ለማስቀየስ፣ የአንበጣውን ውድመት ለማስቀየስና አጀንዳ ለማስቀየር መሆኑ ግን ሁሉ ይወቅ። 
 
 “ Network Against Hate-Speech ቾች” ግን በዚህ ደግሞ እንዳያኮርፉኝ።  አደራ  !!
•••
“ቤተ ክርስቲያን ልጆቿን አስተባብራና አደራጅታ ራሷን ለመከላከል የተገደደችበት ዘመን ላይ ደርሰናል። አለበለዚያ ዕጣ ፈንታዋ እጅግ አስጊ እየሆነ መጥቷል። ልጆቿ እየተገደሉባት፣ ነጻነት አጥተውና ተሳቅቀው እየኖሩ ቤተ ክርስቲያንን ጠበቅን ማለት አይቻልም!
 [ ብፁዕ ወቅዱስ ፓትርያርክ አቡነ ማትያስ ] ”
•••
የአካባቢው ነዋሪ ራሱን አደራጅቶ  አስፈላጊውን ትጥቅ ታጥቆ የተጠናከረ የመከላከል አቅም መገንባት አማራጭ የሌለው ጉዳይ ነው” ምክትል ጠቅላይ ሚንስትር ደመቀ መኮንን
•••
እኔ ዘመዴም አስቀድሜ ያልኩት ይሄንኑ ነበር። ከአዲስ አበባ የሚነሣውና ከአቢይ (አብዱ) አሕመድ የብልፅግና ቤተ መንግሥት ድጋፍ በሚያገኘው በማኅበረ ቅዱሳኑ አባል በእነ ቀሲስ ሙሉቀንና ዮሴፍ አባይ የሚመራው በኢዜማ መሪዎችና ደጋፊዎች በብርሃኑ ነጋ አምላኪዎች በእነ ኢዮብ አለነ በሚታገዘው Network Againest hate-Speech አማካኝነት በተደረገ ውትውታ ከዩቱዩብ ላይ እንዲወርድ የተደረገው ቪድዮዬ ላይ የልኩት የተናገርኩትም ይሄንኑ ነበር። እኔ ቀደም ብዬ ተናገርኩትና አሁን ቅዱስነታቸውና ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ አቶ ደመቀ መኮንን ትናንትናና ዛሬ የተናገሩት አንድና ተመሳሳይ ነው። አሁን እነሱ ጻድቅ ሆነው እኔን ትክክል አይደለህም ሲሉኝ የነበሩ አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና፣ እንደተሳዳቢም ቆጥረው ከፌስቡክም ከዩቲዩብም እንድወርድ ሲወተውቱ የነበሩ የግንቦት ሰባት አባላትና አመራሮች ምን ይሉ ይሆን? አሁንስ ለዩቲዩብ እና ለፌስቡክ ይህን ራስን የመከላከል ዜና ሪፖርት ያደርጉ ይሆን? ወንድሜ ዮሐንስ ሞላም ይሄን ጥቆማዬን ይዘህ አንተ ራስን መከላከል ኃጢአት ነው ባይ ነህና ለፌስቡክም፣ ለዩቲዩብም ሪፖርት ታደርግባቸው ዘንድ ጥቆማዬን አቀርብልሃለሁ።
•••
መጪው ጊዜ ለኢትዮጵያ ከባድ ነው። የውጭ ጠላት ሁሉን ሊያርድ ሁሉን ሊበላ አሰፍስፎ ከደጅ ቆሟል። የሚያሳዝኑት የቤታችን ጉዶች፣ ሰው መሳይ በሸንጎዎች፣ ጎጠኛ መንደርተኛ፣ ለመጣ ሥርዓት ሁሉ አለቅላቂዎች፣ ገንዘብ መሰብሰብ እንጂ ሌላ ህልም የሌላቸው ከንቱዎች፣ ሌላ ሰው መጥቶ ድምጹን ከፍ አድርጎ ሲያሰማና ሲደመጥ የተሸፈኑ የሚመስላቸው ነውረኞች፣ በጓዳ መርዝ የመርዝ ብልቃጦች፣ በአደባባይ በሸንጎ ሰው መሳዮች። የቤት ውስጥ ቀጋ የውጭ አልጋዎች እነሱ ናቸው የሚያሳዝኑኝ።
•••
ሁለተኛ ዙር “ የበረኞቹ ” መልእክት መጥቷል። ደርሶኛልም። አውርተውኛልም። ሰሞኑን ለህዝቡ ሁሉ በቴሌግራሜ እለቀው ዘንድም አውርተውኛል። ልቀቀው ባሉኝ ቀን እለቀዋለሁ። ንስሐ ገብቶ ተዘጋጅቶ መጠበቁ የግድ ነው። የዘንድሮው የዐብይ ጾም ደግሞ ከአምናው የከበደና የባሰ ሳይሆን አይቀርም። የማይነቅዝ እህል እና ጨው አስቀምጡ ብለው ከዛሬ ዓመት በፊት በእኔ በኩል የነገሯችሁን ምክርም ምን ያህሎቹ ተግባራዊ እንዳደረጋችሁ አይታወቅም። ወደ መትረፊያ ገዳማትም ላኩላቸው የተባለውንም እንዲሁ አድርጉ።
•••
ባለፈው መስከረም 5/2013 ዓም በረኸኞቹ  ባስተላለፉት መልእክት ላይ “የኢትዮጵያ ብር የወረቀት ያህል እንኳ ዋጋ አያገኝም” ያሉትንም አሁን እያየነው። በከተማ የምትኖሩ ዜጎች በገጠር ለሚኖሩ ቤተሰቦቻችሁ ከፎርጅድ ብር እንዲጠነቀቁም አድርጉ። ሥርዓተ መንግሥቱ ከሽፏል። የዱርዬ ስብስብም ሆኗል። ምከሩም። ራቡ ግልጽ ነው። በሽታውም ተከታይ ነው። ጦርነቱም የሚታይ ነው።
•••
በአቢይና ሽመልስ የሚታዘዝ ጦር ዐማራን፣ ባለማተቦችን ከመተከል ከርስቱ የማጽዳት ሥራውን ቀጥሎበታል። በደቡብ ጉማይዴም ዐማሮች እየታረዱ ነው። ምንም ሲያዩአቸው ቢያስጨንቁም በነገው ዕለት ቪድዮዎቹን እለቅላችኋለሁ። እነ ዮሐንስ ሞላ፣ ጴጥሮሳውያን የቤተ ክርስቲያን መብት አስጠባቂዎች ነን ባዮቹ እነ ቀሲስ ሙሉቀን፣ እነ ዮሴፍ አባይን የመሳሰሉ እኩያን፣ ከሃይማኖታቸው ዘራቸውና ፍርፋሪ የበለጠባቸው አንዳንድ የማኅበረ ቅዱሳን አባላትና መሪዎችም ይበሳጫሉ፣ ይናደዳሉ ብዬ፣ የኢዜማ ግንቦት ሰባት መሪዎችና ደጋፊዎች፣ እነ ህወሓት ብልፅግና፣ ኦነግና ብአዴኖች ያኮርፉኛል፣ ይበሳጩብኛል ብዬም እኔ ዘመዴ በአደባባይ ለሚታረደውና ዘሩ ከምድረ ገጽ እንዲጠፋ ለተፈረደበት ምስኪኑ ዐማራ መጮሄን አላቋርጥም።
•••
ዛሬ ዐማራው ሲታረድ፣ ሲሰደድ፣ ሲሰቃይ፣ ዘሩ ሲጠፋ ከዳር ቆማችሁ ያያችሁ፣ ዝም ጭጭ ያላችሁ፣ በደስታም ጮቤ የረገጣችሁ፣ እግዚአብሔር ፍርዱን ይስጣችሁ፣ እነዚያን ምስኪኖች ያገኘ፣ ስብራትና ሃዘን እናንተንም ያግኛችሁ። በላያችሁም ላይ ይውደቅ። በቤታችሁና በራሳችሁ የእኔ በምትሉትም ሁሉ ላይ ደርሶ ያሳያችሁ። “ አቢይ እሱ ምን ያድርግ? ብላችሁ ለዐብይ ጥብቅና የቆማችሁ፣ በእናንተ ደርሶ ዐብይ ምንያድርግ? ብዬ እናንተን ለመጠየቅ ያብቃኝ። የህጻናት፣ የእናቶችና የአባቶች ደም ይፋረዳችሁ። እንቅልፍ፣ ሰላም፣ እረፍትም ያሳጣችሁ። ቤታችሁ በሃዘን ይጎብኝ፣ ማቅ ያልብሳችሁ፣ ኃዘን ከቤታችሁ ይግባ፣ ከአቢይ አህመድ መንግሥት ጋር ቆማችሁ ለምስኪኖች ላለመድረስ የተለጎማችሁ ዲዳም ዱዳም ያድርጋችሁ። በራስ በቤተሰባችሁ ስብራት ይድረስ። አሜን !!
….
ፎቶዎቹን ለብልጽግና ደጋፊዎችና አባላት፣ ለሄት ስፒች ተሟጋቾች፣ ለጠልፎ ጣይ አፈጻድቆች ሁሉ አድርሱልኝ።
•••
በግፍ የታረዱትን ዐማሮች ነፍስ ይማር  !!  
ሻሎም !   ሰላም !  
ኢትዮ ሪፈረንስ :- ፎቶዎቹ ዘግናኝ ስለሆኑ አላወጣነውም። እኛም ለተጎጂዎች ነፍስ ይማር እናላለን።
Filed in: Amharic