>

"ከመጠምጠም መማር ይቅደም...7ኛ-ጨ!" (ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ)

“ከመጠምጠም መማር ይቅደም…7ኛ-ጨ!”

ኤርሚያስ ለገሰ ዋቅጅራ

“ደርማሹ” የሚል የዳቦ ስም እንደተሰጠኝ ሰሞኑን ሲደጋገም ነው ያወቅኩት። በዳቦ ስሙ በጣም ደስተኛ ነኝ። ጥያቄዬ “ምን ሰራሁና ይሄን ያህል የሰማይ ስባሪ የሚያክል ስም አሸከሙኝ?” የሚለው ነው። መቼ ተደረመሰና? …ሳልሰማ ህገ-መንግስቱ ተደረመሰ እንዴ?… የክልሎች ህገ-መንግስት ተደረመሰ እንዴ?… የዘር ፓለቲካው ተደረመሰ እንዴ?…ተረኝነቱ ድርምስምሱ ወጣ እንዴ?… የክልል ልዩ-ሃይል ተደረመሰ እንዴ? የክልል ሚዲያ ደፈረሰ እንዴ?…የአዲስ አበባ ቻርተር ተደረመሰ እንዴ?…ኧረ ስንቱ!!!
 የስያሜው አውጭዎች የለውጥ አመራር ባለሙያ ወይንም በዘርፉ እውቀት ያላቸው ይመስላል። ምን አልባትም በሊደርሺፕ ሞዴሎች ዙሪያ አብረን ፕሮግራም ሰርተናል ብዬ አስባለሁ። ሜንቶሮቼም ሊሆኑ ይችላሉ።
 በርግጥ ትርጉሙን ሳያውቁት የሚጠቀሙበት የገዥውንና ተደጋፊ ተደማሪውን ፓለቲካ አጣምረው በደመነብስ የሚመሩት “7ኛ-ጨ” ዎች እንደሆኑም አይቻለሁ ። ሁሌም ይሄን ሳስብ ለኢትዮጵያ አዝናለሁ።
ለማንኛውም Kurt Lewin የሚባል የሊደርሺፕ ሳይንቲስት ታስቦና ታቅዶ የሚመጣ ለውጥ “ሶስት የለውጥ ሞዴሎች ወይም ደረጃዎች” አሉት ብሎ ያምናል። እነዚህም፣
#ደረጃ አንድ :-  ረግቶ የቆየውን መበጥበጥ(“መደርመስ”)(” ማደፍረስ”)…Unfreezing—መ-ደ-ር-መ-ስ!!
Unfreezing : involves breaking down the existing status quo before you can builed up a new way of operating. “ያልደፈረሰ አይጠራም!”
#ደረጃ ሁለት :- መለወጥ…Change( Moving)
Moving : is the stage where people are encouraged to accept a new ideas and new ways of working.
#ደረጃ ሶስት:- መልሶ ማርጋት…Refreezing
Refreezing :- is the process of fixing these new ideas into the minds of the employees and Managers so that they form the new set of beliefs , values , and norms of the organization.
እናም ይሄንን “Kurt Lewin’s Change model” ተምሬ፣ አንብቤ፣ ተርም ፔፐር ሰርቼ ነበር ለውጥ መጣ የተባለ ሰሞን ምክረ-ሃሳቤን ያቀረብኩት።
በተለይም የለውጡ የጫጉላ ሽርሽሩ ወቅት ጠቅላይ ሚኒስትሩ ወደ ዲሲ በመጡ ማግስት እሳቸውን አጅበው ከመጡት LTV ሚዲያ ጋዜጠኛ ቤቴልሄም ታፈሰ ጋር ከሁለት ሰአት በላይ ተወያይተናል። ስለ ረግቶ የቆየውን “መደርመስ” ፣ መለወጥና መልሶ ማርጋት ወቅታዊ ምሳሌዎች በማንሳት ለውጡ እንዴት መሄድ እንዳለበት እንደ አቅሚቲ አስረድቻለሁ። ይሄን ለመናገር ለሊት ተነስቼ ኮንቬንሽን ሴንተር ወረፋ መያዝ አይጠበቅብኝም ነበር። ወይም የወተር ጌት ቅሌት የተፈጸመበት ሆቴል የ3 ሰአት ተማጽኖ ማቅረብ አልነበረብኝም።
ከሁሉም የሚገርመው ብዙዎቹ ዛሬ በበታችነት ስሜት እና እውቀት አልቦነት በወለደው ጋጠወጥነት የሚሰድቡኝ ሰዎች ከጋዜጠኛዋ ጋር የተደረገውን ውይይት እየተቀባበሉ ሲያስተጋቡት ነበር። “የእኛ ባትሆን ይቆጨን ነበር” ያሉኝም አልጠፉም።
 ይህም ሆኖ በወቅቱ ጋዜጠኛ ቤቴልሄም ታፈሰ ከአንድ ሰአት ተኩል በላይ ቆርጠሽ አውጪ የሚል ጫና ስለደረሰባት ቆርጣ ለማውጣት መገደዷን ከይቅርታ ጋር ነግራኛለች። እኔም ይቅርታውን ተቀብዬ አደባባይ ሳላወጣው ቆይቻለሁ። ጋዜጠኛ ቤተልሄም በወቅቱ ያጋጠማትን አስቸጋሪ ሁኔታ በመጽሀፋ እንደምትጽፈው አጫውታኛለች። ማስተማሪያ የሚሆን መጽሀፍ መፃፍ እንዳለባት፣ በመጽሐፏ ላይ የደፋርነቷን ስፍራ መልቀቅ እንደሌለባት ተስማምተን ተለያይተናል።
ከመጠምጠም-መማር-ይቅደም!
– 7ኛ-ጨ!
Filed in: Amharic