>

ብአዴንና ኦሕዴድ በአማራ ነጋዴዎችና ሾፌሮች እየፈጸሙት ያለው ግፍ ህዝቡን ማኅበራዊ እረፍት የመንሳት የወያኔ ተልእኮ አካል ነው!!! (ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው)

ብአዴንና ኦሕዴድ በአማራ ነጋዴዎችና ሾፌሮች እየፈጸሙት ያለው ግፍ ህዝቡን ማኅበራዊ እረፍት የመንሳት የወያኔ ተልእኮ አካል ነው!!!
ሠዓሊ አምሳሉ ገ/ኪዳን አርጋው

በቀደምለታ በጀርመን ራዲዮ  ሾፌሮች “ከደጀን እስከ ባሕርዳር ድረስ በተቋቋሙ ከዐሥር በላይ ከሕግ ውጭ በሚሠሩና በሚንቀሳቀሱ ቀረጥ አስከፋይ አዳዲስ ኬላዎች ፈጽሞ መሥራትና መንቀሳቀስ አልቻልንም!” ማለታቸው ተዘግቦ ነበር፡፡ የጀርመን ድምፅ ራዲዮ “የሚመለከተውን የአማራ ክልል መንግሥት አካል ጠየኩ!” ብሎ ባቀረበው ምላሽም ኬላዎቹ ሕገወጥ መሆናቸውንና በአንድ ዕቃ ላይ ተደጋጋሚ ቀረጥ ማስከፈል ሕገወጥ መሆኑን የተጠየቁት የመንግሥት ባለሥልጣን ተናግረው ነበር!!!
እንግዲህ እግዚአብሔር ያሳያቹህ! እነኝህ ሕገወጥ ቀረጥ አስከፋይ የአገዛዙ አካላት ሕገወጥ ከሆኑ ማን አሠማራቸው ታዲያ??? የየአካባቢው የአገዛዙ አካላትስ እንዴት ዝም ሊሏቸውና ሾፌሮችና ነጋዴዎች በእነኝህ ሕገወጦች “ካልከፈላቹህማ!” እየተባሉ ታርጋቸው የተፈቱ ተሽከርካሪዎቻቸውን በባሕርዳር ጎዳናዎች ላይ ደርድረው ባሕርዳር ታርጋቸው በተፈቱ መኪኖች ተጨናንቃ ለአገዛዙ አቤት እያሉ ባሉበት ሁኔታ እንዴት መፍትሔ ሊጠፋና ሕገወጥ ኬላዎችም አሁንም በሥራቸው ላይ ሊቀጥሉ ቻሉ ታዲያ??? ይሄ ምን የሚሉት ሴራና አሻጥር ነው???
ባሕርዳር በዚህ ብቻ ሳይሆን ሰሞኑን ሰዎች ማን እንደገደላቸው ሳይታወቅ በየምሽቱ ሰዎች በየስፍራው እየተገደሉ በመገኘታቸውም ጭንቀት ላይ ወድቃለች፡፡ በእርግጥ እንዲህ ዓይነቱ ነገር በዚህ አገዛዝ ዘመን አዲስ አይደለም፡፡ አገዛዙ “ሕዝብ ሊያምጽብኝ ይችላል!” ብሎ በገመተ ቁጥር ሕዝብ በፍርሐት እንዲዋጥና ከዐመፅ እንዲታቀብ ለማድረግ በየስፍራው እንዲህ ዓይነት የነሲብ ግድያ መፈጸምን፣ ዝርፊያና ውንብድና እንዲስፋፋ ማድረግን፣ የሸቀጥ እጥረት እንዲከሰት ማድረግን፣ ውኃና መብራት ለተከታታይ ቀናት ማጥፋትን የመሳሰሉት ለዘመናት በተደጋጋሚ ሲፈጽማቸው የቆያቸው ግፍ የተሞሉ ዐመፅን የመቆጣጠሪያ ስልቶቹ ናቸው!!!
የአማራ ነጋዴዎችና ሾፌሮች መከራ ከላይ በገለጽኩት የግፍ ሴራ አላበቃም፡፡ ትናንትና ደግሞ ገብረጉራቻ ላይ ከምሽቱ አምስት ሰዓት ላይ የኦሮሚያ ልዩ ኃይል የሚባሉት የልዩ ኃይሉን ተሽከርካሪ እዚያው ላይ አቁመውና የደምብ ልብሳቸውን እንደለበሱ ከባሕርዳር መስመር የመጡ አምስት ተሽከርካሪዎችን ጎማዎቻቸውን በጥይት በመምታት እንዲገለበጡ አደረጉ፣ አራት ሾፌሮችን ገደሉ፣ የተቀሩትን አቆሰሉ፣ ሁለቱን ተሽከርካሪዎች አቃጠሉ፣ ገንዘብና ንብረት ዘረፉ!!!
ይሄስ ምን ማለት ነው???
በእነዚህ ችግሮች ምክንያትም ባለው የኑሮ ውድነት ላይ በተጨማሪ ጎንደርና ጎጃም የሸቀጥ ዕቃዎች ዋጋ ንሯል!!! አያሳዝንም???
ይሄንን ሕዝብ ከዚህ የወንበዴ አገዛዝ ማን ይታደገው???
ሕዝቡ እንደምታዩት ለራሱ ያለው እራሱ መሆኑን፣ እራሱን ነጻ ሊያወጣ የሚችለው እራሱ መሆኑን፣ ከራሱ ውጭ ማንም ዋጋ ከፍሎለት ነጻ ሊያወጣው የሚችል አካል ሊኖር እንደማይችል መረዳት ተስኖት የሆነ ነጻ የሚያወጣውን አካል እየጠበቀ እንደምታዩት ለሽ ብሎ ተኝቷል!!!
ምን ይሻላል???
Filed in: Amharic