>
5:18 pm - Wednesday June 16, 0945

ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. በብልፅግና ወንጌል ተጠምቆ..... (ከሽግዬ ነብሮ - ኢጆሌ ባሌ)

ኢ.ሕ.አ.ዴ.ግ. በብልፅግና ወንጌል ተጠምቆ

  “ቢቀና ቢቀና ኢሕአዴግ ከማጭድ አይቀናም”

ከሽግዬ ነብሮ – ኢጆሌ ባሌ)

 

ብልፅግና ወንጌል

የመነቃቃት ፈውስ ወይም Healing Revival እ.አ.አ በሰኔ ወር 1946 በአሜሪካ ተጀምሮ በ1950 የብልፅግና ወንጌል  (Prosperity Gospel) ሊፈጠር ችሏል። ይህ ወንጌል የማሳመን ችሎታ ባላቸው ከጴንጤ ቆስጤ ባፈነገጡ ፓስተሮች እየተመራ ብዙ ተከታዮችን በማፍራት በ1980 የቴሌቪዥን ስብከት (Televangelism) በመጀመር በመላ ዓለም ሊያድግና ሊስፋፋ ችሏል። 

 

ብልፅግና ወንጌል በማደግ ላይ የሚገኝ ከጴንጤ ቆስጤና ከኤቫንጃሊዝም ተነጥሎ የወጣ የራሱ የሆነ የክርስትና ሃይማኖት ያለው ዕምነት ነው። የሰው ልጅ ባለፀጋና ጤነኛ ሊሆን የሚችለው በብልፅግና ሃይማኖት ፀንቶ ሲቆይና መጽሐፍ ቅዱስን እንደኮንትራት ውል አድርጎ ሲቀበል ብቻ ነው ብሎ ይሰብካል። በደዌ መሰቃየትና በድህነት መማቀቅ የሀጢአት ውጤት ስለሆነ ሐዋሪያ (Apostle) እና ነብይ (Prophet) የሚሏቸው ፓስተሮቻቸው ከፈጣሪ ጋር የተአምር የቀጥታ ግንኙነት ስላላቸው ትፈወሳላችሁ በሚል ምዕመኑን በማፍዘዝ ወይም (Hypnotise) በማድረግ ለቤተ ዕምነቱ ያላችሁን ገንዘብ አበርክቱ እግዚአብሔር በመቶ እጥፍ አድርጎ ይመልስላችኋል፤ ጤናችሁ ይመለሳል እያሉ ከፍተኛ ገንዘብ ይሰበስባሉ። የሚቀባ ዘይት ወይም (Ointment Oil) ከበሽታ ይፈወሳል፤ የእግዚአብሔርን ቡራኬ ይሰጣል በሚል ለሽያጭ ያቀርባሉ። በአሁኑ ጊዜ የዚህ ወንጌል ተከታዮች ቁጥር ከተለመዱት ከጴንጤ ቆስጤ፣ ከመካነ እየሱስ፣ መሠረተክርስቶስ፣ ቃለ ሕይዎትና ሙሉ ወንጌል የፕሮቴስታንት ሃይማኖቶች ልቆ በመገኘት ላይ ነው። የሰባኪዎቹ ስትራቴጂ ገንዘብ መሰብሰብ ስለሆነ በተለያዩ አጋጣሚዎች ዲታ የሆኑ ተከታዮቻቸውን በአስረጅነት በማቅረብና ገንዘብ በመክፈል ለተዋናይነት ብቁ የሆኑ ሰዎችን በመመልመል መድረክ ላይ አውጥቶ በርኩስ መንፈስ እንደተያዙና እንደአካለስንኩል እንዲታዩና በፓስተሩ ልዩ ተዓምር እንደተፈወሱ በማሳየት ለፈዘዘው ተከታያቸው የገንዘብ አምጡ ጥያቄአቸውን በማቅርብ ምስኪኑን ምዕመን ያራቁቱታል። እንደ እዩ ጩፋ፣ ዮናታን አክሊሉ፣ ብርቱካን ጣሰው (ወ.ዘ.ተ.) ያሉ ተከታይ ባፈሩ ፓስተሮች ለኪሣራ የተዳረጉ ምዕመናን እሮሮ በየጊዜው ይሰማል። አንዳንዶቹም በመገናኛ ብዙሐን ቀርበው ሌላውን ለማሳመን ስለተደረገላቸው ክፍያና ስላሳዩት የመድረክ ድራማ (ትዕይንት) ተናዘዋል። 

 

በዕምንት አማካኝነት የሚሰበሰብ ምፅዋዕተ ሙዳይ ለተቸገሩ መደጎሚያ፣ ለታመሙ መታከሚያ፣ በአጠቃላይ ለነዳያን መዋል ሲገባው የብልፅግና ወንጌል ፓስተሮች ግን እራሳቸውን እያበለፀጉ በተንደላቀቀ የኑሮ ሁኔታ ይምነሸነሹበታል፤ ይዘንጡበታል። ከፍተኛ ወጭ በማድረግ በቴክኒዎሎጂ በተራቀቀ ተመልካችን በሚስብ (HD) ቴሊቪዥን ሥርጭት (Televangelism) በቢልቦርድ፣ በበራሪ ወረቀቶች (ብሮሹር) (PR) ለማስታወቂያ ሥራ የሚያባክኑት ገንዘብ ከፍተኛ ነው። የፓስተሮቹ ዝነጣና በውድ ልብስ ሽክ ማለት የአሜሪካኑን Nation of Islam መሪን ሉዊስ ፋራክሃንና አባሪዎቹን ያስመስላቸዋል። 

 

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ አህመድ መደመር የሚለውን ፍልስፍና ፈጠርኩ ይበሉ እንጅ ምንጩ ከ19ኛው ክፍለ ዘመን የአሜሪካ መንፈሳዊ ንቅናቄ ብልፅግና ወንጌል የመጣ እንደሆነ የሚያመለክቱ ብዙ ፍንጮች ይታያሉ። ብልፅግና በወንጌል ሳይሆን የሚያተኩረውና አፅንዖት የሚሰጠው በትንቢት ላይ ነው። ዶ/ር አቢይም ወደስልጣን እንደመጡ የወላጅ እናታቸው ትንቢት እንደነበረ ቢነግሩንም ፓስተር ወይም ነቢይ ብርቱካን ጣሰው ከሰባት ዓመት በፊት ጠቅላይ ሚኒስትር እንደሚሆኑ እንደገለጡላቸው አላሳወቁንም። (ቪዲዮው አለ) (21 March 2018 Shukshukta) ብሎ በዩቱዩብ ማግኘት ይቻላል።  (ሁሉም ፓስተሮች ነቃ ያለ ካዩ ፕሮፌሠር፣ ዶ/ር፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ትሆናለህ ወዘተ ማለት ልማዳቸው ነው።) ኢ.ሕ. አ.ዴ.ግ. በብልፅግና ወንጌል ተከታዮች ከተተካ በኋላ ስሙንና አርማውን (ሎጎውን) (ወደ ላይ እንደፌንጣ የሚዘሉ ሦስት የብልፅግና ወንጌል ተከታዮች ባሉበት፣ ቀለሙም ትርጉም ይኖረዋል፣ ምክንያቱም የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ ስላልሆነ) በመውሰድ እራሱን ብልፅግና ፓርቲ ብሎ ጠርቷል።  

ይህ ሁሉ መመሳሰል የአጋጣሚ ጉዳይ ወይስ ሆን ተብሎ ታስቦበት የተወረሰ?

 

ጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ከብልፅግና ወንጌል የኮረጁት ስሙንና አርማውን ብቻ ሳይሆን መርሁንም ጭምር እንደሆነ የብልፅግና ፓርቲ ለካድሬዎች ማሰልጠኛ ጥር 2012 ዓ.ም. ያወጣውን ጽሑፍ ማየቱ ገላጭ አስረጅ ነው። ጽሑፉ በጥቅሉ ከፕሮቴስታንት (ብልፅግና) ዕምነት ውጭ ያሉት ሃይማኖቶች ለሰማያዊ ሕይዎታቸው እንጅ ለምድራዊ ሕይዎታቸው ደንታ ስለሌላቸው ለሀገርም ሆነ ለሰው ልጆች ብልፅግና እንቅፋት ናቸው። እንዲያውም አንዳንዶቹ ቤተ ዕምነቶች (ኦርቶዶክስ ክርስትና፣ እስልምናና ካቶሊክ) ሃብት የሀጢያት ምንጭ ነው ብለው ስለሚያምኑ ለሕዝብና ለሀገር ብልፅግና እንቅፋት ናቸው። ስለሆነም 

 

ለሀገርና ለሕዝብ ልማትና ብልፅግና ተስማሚው የአይሁድና የፕሮቴስታንት (ብልፅግና) ዕምነት ነው በማለት ሀገሪቱን በሙሉ የብልፅግና ወንጌል ተከታይ ለማድረግ ደፋ ቀና እያሉ ነው። ይህንንም ዕውን ለማድረግ በየቦታው ቁልፍ ቦታዎች የሚሾሙት የዚህ ወንጌል ተከታዮችና የኦሮሞ ተወላጆች ናቸው። 

የብልፅግና ፓርቲ ጥር 2012 ለብልፅግና ፓርቲ ካድሬዎች ማሰልጠኛነት ካዘጋጀው ጽሑፍ የተወሰደ፣

 

ጠቅላይ ሚኒስትሩና ባለቤታቸው፣ የቀድሞው የአዲስ አበባ ከንቲባ ታከለ ዑማ፣ የኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ሽመልስ አብዲሣ፣ አባ ዱላ ገመዳ እንደ ጆከር በየቦታው የሚመደቡት ወ/ሮ አዳነች አቤቤና ሌሎቹም በባንክ አመራርነትና በድርጅቶች ባለስልጣን በመሆን የሚሾሙት በጥቂቱ የሚጠቀሱ ናቸው። 

በብሔርና በሃይማኖት ተኮር ሽብር ሀገሪቱ ስትናወጥ ዜጎች የሕይዎትና የአካል ጉዳት ሲደርስባቸው እንደሰላማዊ ትግል በዝምታ ለማለፍ ተሞክሯል። በብልፅግና ወንጌል ጥሩ ጥሩውን ከመናገር ውጭ አስከፊና አሳዛኝ ሁኔታዎችን ካለመቀበል፣ ከመካድና በሀጥአን ላይ ከእግዚአብሔር እንደወረደ ቁጣ አድርጎ ከማሳየት የመነጨ ነው። ጭፍጨፋውና ውድመቱ በኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያንና በዕምነቱ ተከታዮች ላይ በተለይም ደግሞ አማራ በሆኑት ላይ በመሆኑ ከላይ እስከታች ያሉት የጊዜው ነገድ ተሿሚዎች የዚህ መጤ ሀይማኖት ተከታይ በመሆናቸው አይተው እንዳላዩ ወይም በወገንተኝነት አድልዖ ምክንያት ማስቆም ሲቻል ብዙ ጥፋት ተፈፅሟል። ሀገሪቱም የዜግነትና የሰብአዊ መብት የሚጣስባት ሲዖል እየሆነች በመምጣት ላይ ናት። 

የኢትዮጵያ ሕዝብ በተልይ አማራው የኢትዮጵያን አንድነት ለማስከበር የከፈለው መስዋዕትነት አሁንም ሀገርን ለማቆየት የሚከፍለው ፍዳ እየተባባሰ ከሚችለው በላይ ሆኗል። “ለምጣዱ ሲባል፣ አይጧ ትለፍ” ብሎ ትዕግሥቱን ቢያሳይም በተረኝነት የሚደረግበት ዘመቻ ንቀትን የተላበሰ ሆኖ ማንነቱንና ሃይማኖቱን እስከመድፈር ተደርሷል። 

“Down Down Ethiopia”, “Down Down Amhara” ኢትዮጵያን ባስተዳደሯት በየትኛውም መንግሥት ዘመን ያልሰማነው መፈክር ነው። እንስሶች እንኳን የገዛ ቤታቸውን አያፈርሱም። “አህያ ምንም ያክል መጽሐፍ ብትሸከምም አህያነቷን አትረሳም” እንደሚባለው የሚሲዮን ጡጦ እየጠቡ ያደጉ ተማርን ባይ የኦሮሞ ከብቶች ለልጆቻቸው ያስተማሩት ውጤት ነው። የአቢይ መንግሥት ሀገር ውስጥ አስገብቶ ያልሆነውን ካባ አልብሶ ከፍተኛ ገንዘብ በመለገስ የዜና አውታር እንዲዘረጋና ሀገርና ሕዝብ እንዲዘልፍ የፈቀደለት ጃዋር መሐመድ የረጨው መርዝና የእሱ ባለሟል በቀለ ገርባ የአደረጉት የአዕምሮ አጠባ (Brain washing) ፍሬ ነው። 

ብልፅግና ፓርቲ – ኢሕአዴግ ተከሽኖ፣ 

የኢትዮጵያ ዋና ዋና ሃይማኖቶች የኦርቶዶክስ ክርስትናና የሱኒ እስልምና ሃይማኖቶች ሆነው ሳለ እነኚህን ሁለት ሃይማኖቶችን በማግለል መጤ ሃይማኖት ለመጫን የሚደረገው ሩጫ ወደ ብጥብጥ እንዳያመራ ከፍተኛ ስጋት አለ። በፀጥታና በኮቪድ 19 (ኮረና) አሳቦ የመስቀልን በዐል ሕዝበ-ክርስቲያኑ እንዳያከብር የጊዜው ሹመኞች ያደረጉት ትንኮሣ መንግሥት የሃይማኖትን ነፃነት አከብራለሁ እያለ በጎን የሚያደርጋቸውን ሙከራዎች አመላካች ነው። “ጠርጥር በገንፎ ውስጥ እንዳለ ስንጥር” እንዲሉ።

ባለጊዜዎቹ የፕሮቴስታንት ሃይማኖት (የብልፅግና ወንጌል) ተከታዮች ነን ቢሉም፣ ለራሳቸው ነገድ ወይም ተቀባይነት ለማግኘት ዕምነታቸውን ክደው ከመንገዳቸው ውጭ ሲሄዱ ተስተውሏል። የኢሬቻ በዐል የባዕድ አምልኮ እንደሆነ ይታወቃል። የብልፅግና መንግሥት ግን ከደብረዘይትና ሆራ ሐይቅ ስቦ አምጥቶ በአዲስ አበባ የባለቤትነት ካርታና ሰርተፊኬት በማዘጋጀት አባገዳ ለሚሏቸው ፊውዳሎች እርስት አስረክበዋል። “ከወገብ በላይ ታቦት፣ ከወገብ በታች ጣዖት” የሩቅ ጊዜ ስትራቴጃቸው አዲስ አበባን የኦሮሚያ የማድረግና የኦሮሙማ ዕቅድ እንደሆነ ፍንጭ ከሚሰጡ ከብዙ ምልክቶች አንዱ ነው። 

የኢሬቻ በዓል በተከበረበት ወቅት የግብፅን ሠንደቅ ዓላማ በመሰለ ጨርቅ አዲስ አበባ ተሸፍና ስትውል ለምልክት እንኳን የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ እንዳይታይ ተድረጓል። ይህ ዝግጅት በመንግሥት የተቀናበረ ስለሆነ ወደዳችሁም ጠላችሁ ኦሮሙማ ተግባራዊ እየሆነ ነው ለማለት የታለመ ነው። የኢትዮጵያ ሠንደቅ ዓላማ በማንኛውም ክበረ በዐል ሲያዝ ነዋሪዎች ሲቀሙና ሲመነጫጨቁ ነው የሚታየውና! የኦሮሚያ መንግሥት እያለ ወ/ሮ አዳነች አቤቤ ከአዲስ አበባ አስተዳደር በኦሮሚያ የፊንፊኔ ልዩ ዞን ለትምህርት ቁሳቁስና ምግብ በሚል ለክልል ዋና ከተሞች ከሚሰጠው በጀት በላይ የ669,210,780 ብር ስጦታ አስረክበዋል። (ይህ በጀት ከደሴና ከጎንደር በጀት በላይ ነው።) ይህም ማለት የኦሮሚያ ልዩ ጥቅም በአዲስ አበባ ማለት ነው። የሴትዮዋን በዚህ ስልጣን ላይ መቀመጥ ብዙ ዜጎች አለመውደዳቸው ዓይን ያወጡ ዘረኛና ምኅረተቢስ ስለሆኑ ይህንኑ አድሎአዊና ጠባብ ዘረኝነታቸውን በመፍራት እንደሆነ ይታወቃል። ለማንኛውም የኢትዮጵያ ዜጋ በትክክለኛው መንገድ ድጋፍ ቢደረግ የሚደገፍ ቢሆንም፣ በተረኝነትና በማንአለብኝነት የሚሰጥ ችሮታ ከሕወሓት – ኢሕአዴግ ማን አለብኝነት የሚለይ አይደለም።  

አዲስ አበባ የኢትዮጵያ ዋና ከተማ፣ የአፍሪካ ሕብረት መቀመጫና መዲና በመሆኗ የብዙ ዓለም አቀፍ ድርጅቶችና ኤምባሲዎች መገኛ ናት። ከተማዋን የማፅዳቱና የማስዋቡ እንቅስቃሴ ከብልፅግና ወንጌል ገፅታ ግንባታ ጋር የተያያዘ ቢሆንም ሊደገፍና ሊበረታታ የሚገባው ነው። መሬት የያዘ ነገር አይጠላምና!

ሁሉም የክልል መንግሥታት የሚገኙት በየክልሉ ሆኖ ሳለ የኦሮሞ ክልላዊ መንግሥት ጽ/ቤት ግን የሚገኘው አዲስ አበባ ነው። በ1997 በተደረገው ሀገራዊ ምርጫ በሽንፈት የተዘረረው ወያኔ ገና ለገና የአዲስ አበባን አስተዳደር ቅንጅት ይይዛል በሚል ሕግ አውጥቶ ናዝሬት የነበረውን የኦሮሚያ ክልል መቀመጫ ቦታ አዲስ አበባ አምጥቷል። ይህ ሁኔታም የሕዝብ ቁጥሬን አዲስ አበባ ላይ ጨምሬ ዲሞግራፊውን እቀይራለሁ ብለው ለተነሱት ተረኞች ምቹ ሁኔታ ፈጥሮላቸዋል። በተለያዩ ጽሕፈት ቤቶች ስም ብዙ ሕንፃዎችን ተቆጣጥሮ ከተለያዩ የኦሮሚያ ክፍሎች ሰዎች በማስመጣት የአዲስ አበባ የነዋሪነት መታወቂያ በመስጠት ደሀው ቆጥቦ የሠራውን የኮንዶሚኒየም ቤቶች አድሏል። አዲሷ ከንቲባም የታከለ ዑማን ፈለግ በመከተል ግምት ተሰጥቷቸው ለተነሱ ሰዎች ዕደላውን እቀጥላለሁ ብለዋል። በዕርግጥ ተነሺዎቹ ድጋፍ ሊሰጣቸው ይገባል። መሬታቸውን የተቀሙት በአነስተኛ ገንዘብ እንደሆነ ስለሚታመን እነሱ በሚፈልጉት መልክ መንግሥት ሠርቶ ማቅረብ ሲገባው ለብዙ ዓመታት ለመቆጠብ ሲል በችግር ሲቆራመድ ከኖረው የኢትዮጵያ ሠፊ ሕዝብ ነጥቆ በመስጠት መሆን አልነበረበትም። 

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ 7 ሄክታር መሬት ከስድሳና ከሰባ ዓመታት በላይ የኖሩ የ37 አባዎራዎችን ቦታ ለኦሮሚያ ፕሬዚዳንት ጽሕፈት ቤት ማስፋፊያ ያስፈልገናልና መነሳት አለባችሁ ተብሎ በአግባቡ በደብዳቤ ሳይሆን በስልክ እንጨት ላይ የሰዎች ዝርዝር እንዲለጠፍ ተደርጓል። የክፍለ ከተማው ባለተራ ባለስልጣንም ለምን እንዲህ እንዳደረገ ሲጠየቅ እንደቀድሞ የወያኔ ሹሞች በንቀት ታዲያ ሌላ ምን ያስፈልጋል ዓይነት የባለጊዜ መልስ ሰጥቶ ተደምጧል። 

ጨዋው የኢትዮጵያ ሕዝብ አንድ ሰው ሕይዎቱ ካለፈች በኋላ የትኛውንም ያህል መጥፎ ነገር ቢሠራ ነብስ ይማር ከማለት ውጭ ስሙን በክፉ አያነሳም። የባለጊዜዎቹ መረን የለቀቀ የማንአለብኝነት ድርጊት ግን እንዲነሳ እያደረገው ነው። ሃጫሉ በጠባብ ዕውቀቱ ኢትዮጵያን ያቆዩልንና ወደ ስልጣኔ ያሸጋገሩንን አባቶቻችንን በሚዲያ እየቀረበ ሲዘልፍ እንደነበረ ይታወቃል። የወጣቱን እንጭጭነት በመገንዘብና ሲያድግ ይበስላል በሚል የተናገረው አልንበረም። ህልፈቱን ተከትሎ እርሱ ነፍጠኛ ባለው ሕብረተሰብ ላይ ብዙ አሰቃቂ ድርጊት ተፈፅሟል። በዓለም ላይ የኢትዮጵያን ስም ላስጠሩት ለአበበ ቢቂላ፣ ማሞ ወልዴ፣ ምሩፅ ይፍጠርና ሊሎችም የቅርብ ጀግኖች ያልተደረገውን ለዚህ ወጣት መታሰቢያነት በገፍ ሲሰየም ይታያል። አርቲስቱ ከደንብ ውጭ ካለመያዣ ከኦሮሚያ ባንክ ከ50 ሚሊዮን ብር በላይ ወስዶ በብረታብረት ንግድ ውስጥ በመግባት ከበርቴ እንደነበረ ይታወቃል። አዲሶቹ ተረኛ ሹሞችም በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር የገንዘብ ችሮታ ለቤተሰቦቹ አድርገዋል። ከአምቦ እስከ አዲስ አበባ በሃጫሉ ስም ያልሰየሙት፣ ያልገነቡትና ገና በአዲስ አበባ ለመገንባት ያሰቡት ሃውልት ምን ያህል ማንአለብኝነት እንደተጠናወታቸው ይመሰክራል። ትምህርት ቤት፣ ፓርክ፣ የባህል ማዕከል፣ መንገድ፣ የአንቦ ዩኒቨርስቲ ካምፓስ ስያሜዎች ወ.ዘ.ተ. የሚጠቀሱ ናቸው።  

ወያኔ እራሱ ገድሎ ለቅሶ እንደሚቀመጥና ፈንጅ አጥምዶ አመከንኩ የሚለውን ቆሻሻ ፖለቲካ (Dirty Politics) ብልፅግና እየተጫወተ ነው ወይስ የምርጫ ቅስቀሳ እያደረገ ነው?   

አዲስ አበባ የኦሮሞ ብቻ ሳትሆን የሁሉም የኢትዮጵያ ዜጎች ስለሆነች የኦሮሚያ ጽ/ቤት በመዲናዋ ከሆነ ሁሉም አዲስ አበባ ውስጥ ጽ/ቤት ሊኖራቸው አለያም ሁሉም ካለምንም ልዩነት በየክልላቸው መቀመጥ ይኖርባቸዋል። አዲስ አበባም የራሷ መብትና ነፃነት ያለው አስተዳደር ሊኖራት ይገባል እንጅ በዘረኛ የኦሮሞ ከንቲባና ሹመኞች መገዛት የለባትም።

 

ሀገሩን ለማሳጣት የሞከረ አምባሳደር

“An ambassador is an honest gentleman sent to lie abroad for the good of his country”

Sir Henry Wotton  

የአንድ ሀገር ዲፕሎማት ማለት የሀገሩን መንግሥት ወይም ርዕሠ – ብሔር ወክሎ ከሀገር ውጪ የሚመደብ ባለስልጣን ነው። ይህ ተሿሚ ከተመደበበት ሀገር ጋር የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚና የሶሻል ግንኙነቶችን ወ.ዘ.ተ. በተመለከተ የሀገሩን መሪ ወክሎ ስምምነቶችን ይፈራረማል፤ የሀገሩን ጥቅም ያስጠብቃል፤ በተመደበበት ሀገር ለዜጎቹ አስፈላጊው የኤምባሲ አገልግሎት መሰጠቱንና ኤምባሲው በተቻለው መጠን ለቸገራቸው ተደራሽ መሆኑን ያረጋግጣል። 

ዲፕሎማት የሚለው ቃል ራሱ ሲተረጎም ብልህና በብቃት በሰለጠነና በጨዋ አቀራረብ በሀገሩ ጥቅም የማይደራደር የበሰለ ሀገር ወዳድ ሰው ማለት ነው። አለመታደል ሆኖ በአምባሳደርነት ወይም ዲፕሎማትነት ሀገራችንን ወክለው የሚመደቡት የኛ ሀገር ተሿሚዎች አብዛኛዎቹ ከሀገሪቱ መሪ ወይም ባለስልጣናት ጋር የጥቅም፣ የጎሣና የፓርቲ ግንኙነት ያላቸው ናቸው። በጠቅላይ ሚኒስትር አቢይ ዘመን ብዙ ጥያቄ የሚነሳባቸውና ከወያኔ ጋር በደል የፈፀሙ ብቃት የሌላቸው ግለሰቦች ወደ ዘብጥያ መውረድ ሲገባቸው በአምባሣደርነት ተሹመዋል። 

ዕድሜ ልኩን በጎሣ ፖለቲካ ውስጥ ያደገውና የኢትዮጵያን ታሪክ በቅጡ ያልተረዳው በቅርቡ ኢትዮጵያ የሕዳሴ ግድብን በተመለከተ በታሪካዊ ጠላቶቿ ጫና በተፈጠረበት ወቅት በቀጥታ በማይመለከተው ጉዳይ በአባይ ላይ ምንም ዓይነት የልማት ሥራ እንዳይሠራ ብለው አፄ ምኒልክ ተስማምተው ፈርመዋል በሚል ለግብፅና ለሱዳን ጥይት ለማቀበል የሞከረውና በዚህ አድራጎቱም ምንም ያልተባለው የኦሕዴዱ የምኒልክ ስም አጠልሺ የጠቅላዩ ጓደኛ በዩናይትድ አረብ ኤምሬትስ ባለሙሉ ስልጣን አምባሣደር ሱሌማን ደደፎ ነው። ከአምባሣደር ሱሌማን ደደፎ ድርጊት ይበልጥ የሚያሳዝነው ደግሞ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢትዮጵያን ገፅታ እንዲህ ሊያበላሽ ሲሞክርና ከዚያም በላይ አሁን አንገብጋቢ በሆነው ከኅዳሴው ግድብ ጋር የሚያያዘውን የአፄ ምኒልክን የ1902 ስምምነት ፍፁም በተሳሳተና ለባላጋራ ወግኖ በሀሰት ሲመሰክር ምንም ዓይነት እርምጃ ሳይወስድበት ዝም ብሎ ማየቱ ነው።  

 

የኦሮሞ ተወላጅ የሆነችው ኢትዮጵያዊት ብርሐኔ ቤካ አፄ ምኒልክንና አርበኞቻችንን አውድሳ ለፃፈችው ጽሑፍ አምባሣደር ሱሌማን በማኅበራዊ ድረ-ገጹ ላይ ያወጣው የተቃውሞ መልስ ነው። 

 

ይህ ከላይ የተቀመጠው የአምባሣደር ሱሌማን አፄ ምኒልክን ከአብርሐም ሊንከን ጋር እያወዳደረ የከሰሰበት ጽሑፍ ሲጨመቅ የሚከተሉትን ነጥቦች ይይዛል፦ 

ሀ/ አብርሐም ሊንከን፣

  1. የአሜሪካንን የርስበርስ ጦርነት በአሸናፊነት ተወጥቶ የሀገሪቱን አንድነት ያስጠበቀ ታላቅ ሰው እንደሆነ፣
  2. የባሪያ ንግድን ያስቆመ፣
  3. ጠንካራ ሀገርና ዘመናዊ ኢኮኖሚ እንደገነባ፣ 

ለ/ አፄ ምኒልክ፣

  1. የዱር አውሬ እንደሆኑ፣
  2. በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኦሮሞዎችን፣ ጉራጌዎችን፣ ሱማሌዎችንና ሐረሪዎችን የጨፈጨፉ፣
  3. በእ.አ.አ. በ1902 ከእንግሊዝ ቅኝ ገዥዎች ጋር ባደረጉት ስምምነት በአባይ ላይም ሆነ በጣና ላይ ምንም ዓይነት ሥራ እንዳይሠራ ስምምነት በመፈረም ለዛሬው ችግር የዳረጉን ናቸው በሚል ክስ ይወነጅላቸዋል።   

አዎ አብርሐም ሊንከን ከላይ የተጠቀሱትን ጉዳዮች ለአሜሪካ አከናውነዋል። ሆኖም ግን እዚህ ላይ አብሮ መታወቅ ያለበት የባሪያ ሥርዓትን ለማስቆምና የሀገሪቱን አንድነት ለማስጠበቅ ባደረጉት ጦርነት አሜሪካ በታሪኳ እስከአሁን ያልሞተባት ከፍተኛ የሰው ኃይል ያለቀባት መሆኑን ነው። በዚያ ከ1861-1865 በተደረገ የርስበርስ ጦርነት 620,000 አሜሪካዊያን ሕይዎታቸውን ማጣታቸው መታወቅ አለበት። ይህም መስዋዕትነት የተከፈለው የባሪያ ሥርዓትን ለመስወገድና የሀገሪቱን አንድነት ለማስጠበቅ ሲባል ነው። ይህ ጦርነትና መስዋዕትነት ለአሜሪካ ወይም ለአብርሐም ሊንከን ሲሆን ቅዱስ ሆኖ ወደ ኢትዮጵያና ምኒልክ ሲመጣ ግን የሚኮነንበትና ምንሊክን በአውሬነት የሚያስመድብበት ሁኔታ አግባብ አይሆንም። አምባሣደር ሱሌማን ደደፎ የሀገሩን ታሪክ ከጥላቻና ዘረኝነት በፀዳ ሁኔታ አይቶት ቢሆን ኖሮ ልክ እንደ አብርሐም ሊንከን ምኒልክም በኦሮሞ ወረራ ተከፋፍላ የነበረች ኢትዮጵያን መልሶ አንድ ለማድረግ ሲሉ አንዳንድ አልገበርም ያሉ ገዥዎች ጋር ጦርነት አካሂደዋል። በእርግጠኝነት መናገር የሚቻለው ግን አምባሣደር ሱሌማን ደደፎም ሆነ ሌሎች የኦሮሞ ልሂቃን አጋነው እንደሚያቀርቡት ኢትዮጵያ ውስጥ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ሊሆኑ ቀርቶ በሱሌማን ደደፎ በተሞካሹት አብርሐም ሊንከን ምክንያት አሜሪካ ውስጥ የሞተውን ያክል ሰው እንኳን ኢትዮጵያ ወስጥ አልሞተም።

ሌላው መታወቅ ያለበት አፄ ምኒልክ ኢትዮጵያን መልሶ ለማዋሃድ ዘመቻ ሲጀምሩ ጊቤ አካባቢ የገዳ ሥርዓቱን አፍርሰው የየራሳቸው ትንንሽ መንግሥታት የመሠረቱና በመመሥረት ላይ ያሉ የኦሮሞ አባዱላዎች አንዱ አንዱን ለመዋጥ እርስ በእርስ ጦርነት እየገጠሙ አሰቃቂ እልቂት የሚፈፀምበት ጊዜ ነበር። ይህንንም የኦሮሞ ተወላጅ የሆኑት ዶ/ር መሐመድ ሐሰን The Oromo of Ethiopia በተባለ መጽሐፋቸው የገለፁትን እንደሚከተለው ለምሣሌ ያህል ቀንጨብ አድርጎ ማሳየት ይቻላል፦

First and foremost, all the Gibie states were the creation of war leaders. War made the Gibe Kings, and all of them made war the prime business of their administration. However, it should be noted here that all the early Gibe kings found themselves faced by serious rival, whom they faced with ruthless cruelty. This perhaps helps explain their excessive cruelty towards opponents, cruelty which included the physical elimination of rivals and the enslavement of all members of their families.

አፄ ምንሊክን ከጥላቻ በፀዳ ሁኔታ ብንዳኛቸው እንዲህ ዓይነቱን ጭካኔ የተሞላበት የርስበርስ መተላልለቅና የተሸናፊው ቤተሰብ እንዳለ ወደባሪያነት የሚለወጥበትን ፍፁም ጨካኝ ሥርዓት አፍርሰው ለሕዝብ ሰላም ያመጡ መሪ መሆናቸውን እናይላቸው ነበር። አብርሐም ሊንከን በአሜሪካ የባሪያ አሳዳሪ ሥርዓትን በማስቆሙ እንዳደነቅናቸው ሁሉ አፄ ምኒልክም ደመ – መራራ ሆኑ እንጅ በኦሮሞ ገዥዎች ዘንድ የባሪያ ሽያጭ እንደዋና ሥራ ተቆጥሮ ይካሄድ የነበረውን ድርጊት አምርረው የተቃወሙበትን የሚከተለውን ደብዳቤ ብቻ ማየቱ አፄ ምኒልክ ምን ዓይነት ፈሪሃ እግዚአብሔር ያደረባቸውና ሰው ሁሉ እኩል የእግዚአብሔር ፍጡር መሆኑን የሚያምኑ ስልጡን ንጉሥ እንደነበሩ ያሳያል፦

አፄ ምኒልክ ለአባ ጂፋር የባሪያ ንግድንና ሰውን ባሪያ እያደረጉ መያዝ እንደሌለባቸው በመግለፅ የጻፉላቸው ደብዳቤ

 

ይህ የባሪያ ሽያጭና ባሪያን እንደንብረት የመያዝ ጉዳይ በአባጅፋርና በመሰል የጊቤ ገዥዎች ዘንድ ብቻ ሳይሆን በምዕራብ ኢትዮጵያ ለነበረው ሌላው ኦሮሞ ሁሉ የተለመደና የሀብታምነት መለኪያ እንደነበር አሁንም ዶ/ር መሐመድ እንደሚከተለው ይገልፁታል፦

“By the beginning of the nineteenth century in the Gibe region of Western Oromoland the term Borana had already acquired the meaning of the noblemen, rich in cattle and slaves.” 

        

በጥላቻ የታወረውና ከአምባሣደር ሥነምግባር ውጭ የሆነው አምባሣደር ሱሌማን ደደፎ አፄ ምኒልክን አውሬ አድርጎ ሊስላቸው ቢሞክርም በዓለም ታዋቂ የታሪክ ጸሐፊዎች ግን ከእርሱ በተቃራኒ ነው የሚስሏቸው። ለምሣሌ አፄ ምኒልክ በኖሩበት ዘመን በአካባቢው የነበረውና የእርሳቸውን ሥራ አሣምሮ የሚያውቀው ታዋቂው እንግሊዛዊ ጸሐፊ አጉስቶስ ዋይልድ (Augustus Wylde)

“In the history of mankind, there has never been any other black man like Menelik, who had triggered a lasting fear and doubt in the mind of Europeans.”  ሲላቸው፣ አፍሪካዊው የታሪክ ባለሙያ ሞለፊ ኬት አሳንቴ (Molefi Kete Asante) ደግሞ እንዲህ ይገልፃቸዋል፦ 

“Menelik, the Great, inspired generation yet unborn with his daring defeat of the Italian Army at the Battle of Adwa.” ሌሎች ጸሐፊዎችም ምኒልክን የሚገባቸውን ያክል አድንቀዋቸዋል። ብዙ ጣሊያኖች ኮርቻቸውን ለመስፋትና ጫማቸውን ለመሥራት ዕድሉ ይሰጠን ብለው ሲለምኑ፣ ፈረንሳይና ደቡብ አፍሪካ ደግሞ በስማቸው ውድ የሆነውን ቸኮሌትና ሽቶዎች ሠርተው እስከአሁን ለገበያ በማቅረብ ላይ ናቸው። ብራዚል ደግሞ በምኒልክ ድል በመደነቅ Oh Menelik የሚል ጋዜጣ ታትም ነበር። 

አድዋ ወይም ምኒልክ የሚል ሽቶ               ምኒልክ የሚልና ደቡብ አፍሪካ ውስጥ የሚመረት ሽቶ

 ምን ይሄ ብቻ! በጥላቻ ዓይኑ የታወረው አምባሣደር ሱሌማን አፄ ምኒልክን የዱር አውሬ (wild Beast) ብሎ ከሰውነት ተራ ሊያወርዳቸው ቢሞክርም፣ ታዋቂው አሜሪካዊ የታሪክ ባለሙያ Raymod Jonas ገናናው አፄ ምኒልክን ከእነማን ጋር በእኩል ደረጃ እንዳስቀመጣቸው ሱሌማን እየመረረውም ቢሆን እስከአሁን ካላየው እንዲያየው መጥቀሱ አስፈላጊ ነው፦ 

In 1897, Vanity Fair featured Menelik as the subject of its colored lithograph – a distinction roughly analogous to making the cover of Time magazine in twentieth – century America. Thanks to Vanity Fair, Menelik was vaulted into the company of such international celebrities as Charles Darwin, Czar Alexander, and Napoleon III; he was tagged ‘quite an enlightened monarch’       

አምባሣደር ሱሌማን ያደነቃቸው አብርሃም ሊንከን በሀገራቸው መካከል ተነስቶ የነበረውን የርስበርስ ጦርነት ድል በማድረግና የባርነትን ሥርዓት በማስወገዳቸው ነው። ታላቁ አፄ ምኒልክ ግን ከዚያም አልፈው በመሄድ የዓለምን ሕዝብ አስተሳሰብ የቀየሩ ሰው መሆናቸውን አሁንም Raymond Jonas ይግልጻል። ሬይመንድ በምኒሊክ የተመራው የአድዋ ጦርነት በወራሪዋ ኢጣሊያ ላይ የተጎናፀፉት ድል የዓለምን ታሪክ ብቻ ሳይሆን የዓለምንም የቆየ ዕምነት/አስተሳሰብ የቀየረ ድል ነው ይለዋል። ከአድዋ ድል በፊት የነበረው የዓለም አስተሳሰብ በአንድ በኩል አፍሪካውያን ብሎም መላው የጥቁር ሕዝብ ነጭን ጥቁር ማሸነፍ ስለማይችል ለመግዛት ለተፈጠሩት ነጮች ከመገዛት በስተቀር ምን አማራጭ የለኝም ብሎ ተገዥነቱን አምኖ ተቀብሎ ከሚኖርበት የባርነት ዘመን በአሸናፊነት መውጣት እንደሚቻል ፋና ወጊ ሆኖ አስተምሮታል። በሌላ በኩል ደግሞ በነጭ የበላይነት ዘረኛ ልክፍት ዓይነ-ልቦናቸው ታውሮ የነበሩ ነጮች ጥቁርም ሰው እንደሆነና ነጭን ማሸነፍ እንደሚችል እየመረራቸውም ቢሆን አምነው እንዲቀበሉ ያደረገ ታላቅ ታሪካዊ ክስተት (Game changer) ነው። ይህንን የዓለም ታሪክና አጉል አስተሳሰብ/ዕምነት ገልብጠው በራሱ ያቆሙት ደግሞ አምባሳደር ሱሌማን እንደ አውሬ እንጅ እንደሰው አልቆጥራቸውም የሚላቸው አፄ ምኒልክ ናቸው። 

የአምባሣደር ሱሌማን የመጨረሻው ክስ አፄ ምኒልክ እ.አ.አ. በ1902 ከቅኝ ገዥዋ እንግሊዝ ጋር ያደረጉትን ስምምነት የሚመለከት ነው። ክሱም፦ 

“ዛሬም ከግብፅና ከሱዳን ጋር የሚያናቁረን የምኒልክ ጦስ መሆኑ መዘንጋት የለበትም። በአባይ ወንዝ ላይ ከጣና ጀምሮ ምንም ዓይነት ግንባታ ላይገነባ፣ ወይም እንዲገነባ ላይፈቅድ ለእንግሊዞች የፈረመ ምንሊክ መሆኑ ተረሣ? ከሱዳን ጋር መፍታት ያልተቻለው ውስብስቡ የድንበር ችግር የምንሊክ ውርስ መሆኑ ቀረ እንዴ? ኢትዮጵያ ዛሬ ወደብ አልባ ሆና የቀረችው ያኔ በተፈጠረው ታሪካዊ ስህተቶች ምክንያት ነው።” የሚል ነው። 

 

ለመሆኑ አፄ ምኒልክ የተፈራረሙት የ1902ቱ የድንበር ውል ላይ ስለጣናና አባይ ወንዝ የሚያወሳው አንቀፅ 3 ምን ይላል? አብረን እንመልከተው፦

 

ጃንሆይ ዳግማዊ ምኒልክ ንጉሠ ነገሥት ዘኢትዮጵያ ከጥቁር አባይና ከባህረ ፃና ከሶባት ወንዝ ወደነጭ ዓባይ የሚወርደውን ውሀ ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር አስቀድሞ ሳይስማሙ ወንዝ ተዳር እዳር የሚደፍን ሥራ እንዳይሰሩ ወይም ወንዝ የሚደፍን ሥራ ለማሠራት ለማንም ፈቃድ እንዳይሰጡ በዚህ ውል አድርገናል።” (መሥመር የተጨመረ) ሲል የእንግሊዝኛው ደግሞ የሚከተለው ነው፦ “His Majesty the Emperor Menelik II King of Kings of Ethiopia, engages himself towards the Government of His Britannic Majesty not to construct or to allow to be constructed, any work across the Blue Nile, Lake Tsana or Sobat which would arrest [emphasis added] the flow of their waters into the Nile except in agreement with His Britannic Majesty’s Government and the Sudan.”  

 

ከአማርኛው ሠነድ ላይ እንደምናየው ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር ሳይስማሙ ወንዝን ተዳር እዳር የሚደፍን ሥራ እንዳይሠሩ ተስማምተዋል ነው የሚለው። ወንዝን ተዳር እዳር መድፈን ማለት ምንም ውሃ እንዳያልፍ አድርጎ ውሃውን ሙሉ በሙሉ ማስቆም ወይም አንድም የውሃ ጠብታ እንዳያልፍ አድርጎ ማገድ ማለት ነው። የእንግሊዝኛው ክፍልም “…which would arrest the flow of their waters into the Nile…” ነው የሚለው። Arrest የሚለው ቃል ትርጉምም እንዳይንቀሳቀስ ማስቆም፣ ማገድ የሚል ትርጉም ስለሚሰጥ የአማርኛውና የእንግሊዝኛው ሠንዶች ትርጉም ይስማማሉ። ስለዚህ አፄ ምኒልክ ውሃውን ሙሉ በሙሉ ከዳር እዳር በመድፈን ውሃውን እንዳያልፍ እስካላደረጉ ጊዜ ድረስ አባይን ላለመገደብ አንዳችም ስምምነት አልፈፀሙም። ይህም ማለት አምባሳደር ሱሌማን አፄ ምኒልክን የሚከሰው አፄ ምኒልክ ባልፈፀሙት ወንጀል ነው። ይህ ውል አምባሣደር ሱሌማን በተረዳው ዓይነት ቢሆን ኖሮ ግብፆች ኢትዮጵያ ባልፈረመችባቸው የ1929 እና የ1959 ስምምነቶች ላይ ሙጥኝ ከሚሉ፣ በዚህ አፄ ምኒልክ በፈረሙበት ውል ላይ ተመርኩዘው ይሟገቱ ነበር። ግን አላደረጉትም፤ ምክንያቱም አያዋጣቸውማ! ምንአልባት ወደፊት አምባሣደር ሱሌማንን ጥብቅና አቁመው ይሞክሩት ይሆናል። እርሱም ቢሆን አይሳካም፤ ምክንያቱም ኢትዮጵያ ያላት ማሥረጃ የማያፈናፍን ነውና!

 

የድንበር ስምምነቱ እስከአሁን ድረስ መፍትሄ ያላገኘው እንግሊዞች ድንበሩን ሲከልሉ የስምምነቱን ውል በመጣስ ኢትዮጵያን በሚጎዳ መልኩ ስለቸከሉት ነው። ይህም ብቻ ሳይሆን ችካሉን ኢትዮጵያን በሚጎዳ ሁኔታ ከቸከሉ በኋላ አዲስ ካርታ ሠርተው አፄ ምኒልክን በአዲሱ ካርታ ላይ እንዲፈርሙ ሲጠይቋቸው አፄ ምኒልክ ፈቃደኛ አልሆኑም። አሁን ያለው ውዝግብ ሱዳኖች በችካሉ መሠረት መሬቱን አስረክቡኝ ሲሉ የኢትዮጵያ መንግሥት ደግሞ በዚህ ጉዳይ ላይ ጥልቅ ጥናት ካደረገው የኢትዮጵያ ድንበር ኮሚቴና ከኢትዮጵያ ሕዝብ በደረሰበት ጫና የሱዳንን ሕገወጥ ፍላጎት ማሟላት ባለመቻሉ ነው።  

 

ስለዚህ አምባሣደር ሱሌማን ደደፎ ክሶችህ ሁሉ በዕውነት ላይ የተመሠረቱ ሣይሆኑ በጥላቻ ላይ የተመሠረቱ የውሸት ክሶች ናቸው። የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴርም እንዲህ ለሀገሩ ጠበቃ እንዲሆን የሾመው አምባሣደሩ ከተሰጠው ተል ዕኮ ውጭ በመሄድ በክህደትና በሀሰት ለጠላት ወግኖ ሀገሩን ሲከስ መታገስ ስሌለበት በአፋጣኝ የእርምት እርምጃ ሊወስድበት ይገባል። 

 

ለወገኑ ተደራሽ ያልሆነ ኤምባሲ   

 

ኮቪድ 19 (ኮሮናን) ተከትሎ በየሀገሩ የኢኮኖሚ ውድቅት መድረሱ ይታወቃል። ከእነዚህም ሀገሮች ውስጥ በቤት ሠራተኛነት በብዛት ዜጎቻችን የሚኖሩባቸው የመካከለኛው ምሥራቅ ሀገራት ናቸው። 

 

በቤይሩት ሊባኖስ ብዙ ኢትዮጵያውያን አሠሪዎቻቸው አውጥተው ሜዳ ላይ ጥለዋቸዋል። አንዳንዶቹንም ደመወዝ ሳይከፍሉ፣ ንብረታቸውን እንኳን ሳይሰበሰቡና እንዲያው ሳያስቡት ኢትዮጵያ ኤምባሲ በር ላይ እንደቆሻሻ ሲዘረግፏቸው ታይተዋል። በእርግጥ የኤምባሲዎች በጀት ውሱን ነው። ሆኖም ግን ኤምባሲው ሀገራቸው መሆኑ እየታወቀ የቆንስላው ጽ/ቤት ዲፕሎማቶች በወረርሽኙ ሰበብ ቢሮዋቸውን ቆልፈው መጥፋታቸው ምን ይባላል? ችግሩ ከአቅማቸው በላይ ቢሆንም እንኳን በሞራል አለንላችሁ የሚል ድጋፍ መስጠትና ከዕርዳታ ሰጭዎች ጋር ግንኙነት ፈጥሮ መፍትሄ መሻት ሲገባ ተደብቀው ከርመዋል። 

 

የኢትዮጵያ የውጭ ጉዳይ መሥሪያ ቤትና በስልጣን ላይ ያለው መንግሥትም በዚህ ጉዳይ ላይ መፍትሄ ከመፈለግ ይልቅ ዝምታን መርጠዋል። ኢትዮጵያም በዚህ በደል በዓለም ታላላቅ መገናኛ ብዙሐንና ጋዜጦች በአሉታዊ ጎኑ እንድተነሣ ሆናለች። ለእነአዜብ መስፍንና ስብሐት ነጋ ቤተሰቦች አገልግሎት ሲያሸረግድ የነበረው የኢትዮጵያ አየር መንገድስ የመሣፈሪያ ዋጋ ቀንሶ ማምጣት ሲገባ ከተለመደው ዋጋ በላይ እጥፍ  መጠየቅስ ነበረበት ወይ?  

 

ብዙ ወጣቶች ተምረው ሥራ በማጣት በችግር ምክንያት ጉልበታችንን ሸጠን ራሳችንና ቤተሰቦቻችንን እንረዳለን በሚል ድንበር እየጣሱ ወደ መካከለኛው ምሥራቅና ሌሎች አፍሪካ ሀገራት ይጎርፋሉ። 

 

አንዳንዶችቹ ቀንቷቸው ጉልበታቸውን መሸጥ ሲችሉ፣ ብዙዎቹ ግን የአትላንቲክ ውቅያኖስ ውሃ ሲበላቸው፣ ሌሎች ደግሞ በደላላዎችና ተባባሪዎቻቸው ታርደው ኩላሊታቸው ሲዘረፍና ከዚህ ሰቆቃ የተረፉትም በጠረፍ ዘቦች እየተያዙ ወደ ዘብጥያ ይወርዳሉ። በቅርቡ በየመን በተቀሰቀሰው ጦርነት ወደ ሳዑዲ ለመግባት ሲሉ ተይዘው በየእሥር ቤቱ የታጎሩ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ዜጎች በዚህ ወረርሺኝ ዘመን በአንድ ላይ እንደከብት ተዘግቶባቸው ለማየት ተችሏል። ይህም ወቅታዊ የዓለም መገናኛ ብዙሐንና ሰብአዊ መት ተሟጋች ድርጅቶች መነጋገሪያ ሆኗል። የኢትዮጵያ መንግሥት ግን ይህንን አስከፊ ክስተት አፍኖ መያዝ መርጧል። በየትኛውም ደርጃና የትም ቦታ ያለው ወገናችን ዜጋ እንደመሆኑ መጠን ለሌላው አስተማሪ በሚሆን መንገድ ልሕዝብ መገለፅና ዕርዳታ አሰባስቦ ወደ ሀገር የሚመለሱበት መንገድ በአስቸኳይ ሊፈለግለት ይገባል። በሳዑዲ አረቢያ የሚገኘው የኢትዮጵያ ኤምባሲ ጉዳዩ ከአቅሙ በላይ እንደሆነ ቢታወቅም፣ መፍትሄ የማፈላለጉ ተግባር ላይ ሊያተኩርና ከጎናቸው ሊቆም ይገባል። 

 

ጽሑፌ ለትችት ክፍት ነው። 

shegyen@gmail.com

Filed in: Amharic