>

የጊዜው ገዥዎችእባካችሁ ህዝባችን ከዚህ ጉድ እናድነው ! ! ! ! (አሰግድ ገብረሥላሴ)

የጊዜው ገዥዎችእባካችሁ ህዝባችን ከዚህ ጉድ እናድነው ! ! ! !

አሰግድ ገብረሥላሴ

ይድረስ ለትግራይ ክልል እርሻ ቢሮ ፣ለትግራይ ክልል ፕረዝዳንት ደ/.ደብረጽዮን  በአሁኑ ወቅት የአንበጣ መንጋው ወሮናል ።  በመላው የኢትዮጱያ ህዝባችን ፊት ረሀብ ስደት ፣ህምም ፣ሞት ተደቅኗል ህዝባችን በራሱ ተነሻሽነት በተናጠልን በቡዱንም ፣እንዲሁም በትእዛዝ የተሰባሰቡ መንጋው ለመከላከል ሲሳማሩ ሰንብታል አርሶ አደርም አብዛኛ በተናጠል ቡዙ ነገር ሰርቷል ። የአብይ አህመድ ቡዱንና የክልል መሪዎችም ስለስልጣናቹሁ እድሜ  መራዘም በሚመለከት በፕሮፕጋንዳ ስትጠመዱ ስለ ሰብል ፣እጽዋት አውዳሚ  የአንበጣ መንጋ  መከላከል በሚመለከት የምታደርጉት ቅስቀሳ ለይስሙላ ነው ። ሚዲያዎቻችሁም እንደዚሁ  ምንም እንኳ  እንዳይባሉ ትንሽ የሚተነፍሱ ቢሆንም ለፓለቲካ ቅስቀሳ ከሚሰጡ ጊዜ አንጻር ሲታይ እጅጉን ትንሽ ነው። በእናንተ መሪዎቻቸው የምትሰጡወቸው መመሪያ መሰረት  ። በፕሮፕጋንዳ አቅጣጫችሁ ነው የሚነዱት ። እኔ እምሰጣችሁ ማሳሰብያ (አስተያዬት )   ፋኦ (የአለም ምግብ ድርጅት ከ8 ወር በፊት የሰጣቹሁ  የቅድመ ሁኔታ የመከላከል ማስጠንቀቅያ  ዝግጅት ታደርጉ ዘንድ ባታደርጉትም ፤እሱ ይቆይ የሚጠየቅበት ሊኖር ይችላል እኔ ምለው ያለሁ ግን አሁን ምን እናድርግ ፤
1ኛ     አንበጣው ለመከላከል ብሎም ለማጥፋት  መጀመሪያ በከተማም በገጠርም ላለው ህዝብ መቀስቀስ  ፍላጎት መፍጠር ፣  አንበጣው ልክ እንደወታደር የሚመጣበት አቅጣጫ ማጥናት
2ኛ    ሁሉም ህዝብ በግብረሀይል ማዳራጀት በየተደራጀበት ለዘመቻ ማዛጋጀት  ፣ኃላ በዚህ ታዬ በሚባልበት ተደራጅቶ የቀዬ ማንቀሳቀስ ፣
3ኛ  ለዘማቹ ምግብ እንደ በየገበያው ያለው ቆሎ ፣ብስኩት ገዝቶ ማቅረብ ፣
4 መጓጓዣ ለዘማቹ የሚያንቀሳቅሱ ፣የውሀ ቦቴዎች ከተቻለም ሀይላንድ ውሃ ማዛጋጀት ፤
5ኛ   አንቡላንሶች ሀኪሞች መድሀኒት በተለይ ለዲሀይድረሽን መከላከያ ማዛጋጀት ፣ እስከ ቃሬዛ ማዛጋጀት መሆን አለበት ፣
6ኛ የደረሰ እህል ማጨድ ለዚሁ  የሚሆን ማጭድ መዘጋጀት ማከፋፈል ፤
7 ኛ  ከሚካል ካለ ከሚካል የሚረጩ የአርሻ ሰራተኞች ስለማይበቁ ወጣቶች በማሰልጠን ሌት ተቀን የሚረጩ በፈረቃ ማዳራጀት በተጠንቀቅ ማስቀመጥ ፣
8 ኛ የሚሰበሰብ ገንዘብ በመከላከል ስራ  እየዋለ መሆኑ መረጋገጥ  ፣
9ኛ ከአብይ አህመድ ያላቹሁ ልዩነት ይግል ክብራችሁ ወደ ጎን አቆይታችሁ የአንበጣ መንጋ ለመከላከል  መእከል ያደረገ ፤   የትግራይ ህዝብ በሀገራችን ያለው የአንበጣው መከላከያ ቁሳቁስ መድሀኒት አየር  ተጠቃሚ ይሆን ዘንድ ተግባብታችሁ ብትሰሩ በተጨማሪም ከውጭ ተገዝቶ ማስገባት ቡዱኑ ለማስተገበር ግዴታው መሆኑ እንዲያውቅ ማድረግ ፤እምብ ካለ በትግራይ ህዝብ ላይ ሞት ፍርድ ማወጁ ስለሆነ ለኢትዮጱያ ህዝብ ፣ለአለምም ማስታወቅ ።
            ይህ ሀሳብ  ለማንሳት የተገደድኩበት ምክንያት ባለፈው ሳምንት ለአንበጣ መከላከል የተደረገው ምንም እንኳ የተሰማራው ህዝብ  ጥሩ ስሚት ሞራል  ቢነረው የተገኜው ህዝብ በመሉ ወደ አንበጣ የታየበት ሲዘምት በአንድ ጊዜ ስለሚደክም የአንበጣው  ማጥቃት ስራ  ቀጣይነት አልነበረውም። በተጨማሪም ስራው ቀጣይነት እንዲኖሮው በፈረቃ በመደራጀት አንዱ ቡዱን ሲደክም የሚተካው ቡዱን ስላልነበረ መንጋው በማኸሉ የማውደም እድል ያገኝ ነበር ።አሁንም እንደዛው ነው እየሄደ ያለው ።የሰው ሀይሉ ለቀንና ለሊት ተበሎ ስላልተከፈለ ፣ ቀን የተሳማራ የሰው ሀይል ለሊት መንጋው  ለመጨፍጨፍ እጅጉን ስለሚደክም ስራው ይቋረጣል ።
        ትልቁ ስህተት ደግሞ የክልሉ አማራሮች  በራሳቸው መኪና ወደ መንጋው አከባቢ ሄደው ካሜራ እየተነሱ በተለብዥን መታዬት ካልሆነ በስተቀር የመከላከል ስራው በቅርብ ሆኖ የሚመሩ  አልነበረም ።ትልቁ ስህተት ደግሞ ሲደረግ የሰነበተ እንቅስቃሴ ለፖለቲካ ፍጆታ ማእከል ያደረገ ስለነበር ለሚመለከተው ሁሉ ጥሩ መንፈስ አልፈጠረም ። በመሆኑም በየደረጃው ያሉ የክልል ፣ የማህበራት አማራሮች ዋና ስራቸው በደጀን  በፊት በመሰለፍ ፊት በመሆን ስራው  ቀጣይነት እንዲነረው የሰው ሀይል በፈረቃ እያዳራጁ መሳማራት አስፈላጊ ሎጅስትክስ በመግፋት መረባረብ ነበረባቸው ።ሰው በመቀስቀስ ረገድም እጅጉን ደከማ ነበር ።ትልቁ ሌላው ስህተትም  ደግሞ አንበጣው እየተነሳበት ያለው በአፋር ክልል ስለሆነ  በጉያችን ገብቶ ካጠቃን በኃላ ነው ጫፍ ጫፍ እየተከላከልን ያለነውን እንጅ ከአፋር ህዝብና መሪዎች ተወያይቶ እዛው መፈልፈያው ሄዶ ለመጨፍጨፍ ይቻል ነበር ።ግን ምን ይሁን የክልል አማራሩ በራሱ ፖለቲካ ተጠምዷል ፣አሁንም ግን ለአውዳሚው አንበጣ ለመከላከል ማኸል ያደረገ ስራ እንደ መስራት ፈንታ ከአብይ አህመድ ጋር ያላቸው ሰጣገባ ቂም መዋጣጫ ሲጠቀሙበት ይታያሉ ።
አብይ አህመድ እኮ እውነቱ ነው እየተከተለው ያለ ስትራተጅ  የአያቱ  እና አባቱ የዘውዳዊ ስርአትና የፋሽሽታዊ ደርግ   ስርአት  ተከትሎ የትግራይ ህዝብ ለመግዛት መጀመሪያ አስርበህ  ማንበርከክ የሚል ለጋሲያቸው ነው እየተከተለው ያለው ።ሌላ የአብይ አህመድ በዚሁ የአንበጣ መንጋ አስቀድሞ  ለመከላከል  የሰጠው አትኩሮት በአማራም ፣በኦሮሞም ፣በሀረር  ፣በድሬዳዋ በትግራይ   ወ ዘ ተ ያለው ውድመትም እኮ ከመጤፍም አላየውም በራሱ አለም ነው ያለው ። አብይ አህመድ እኮ ለዝህች አገር እና እዝቦቻ የሚያስብ ቢሆን ኖሮ የአለም ምግብ ድርጅት ከ8 ወር በፊት የተናገረው መረጃ ተቀብሎ በመፈልፈያው ሄዶ  ለማጥፋት ይችል ነበር። ፋኦ እኮ ለአፍሪካ  መንግስት ቢሊዮኖች ዶላር መድቧል ።ከዚሁ ለኢትዮጱያ ቡዙ ሚሊዮኖች  ደርሷቷል  በመሆኑም የትግራይ ክልል አማራርም ከአብይ አህመድ በመወናጀል ጊዜ ከሚያሳልፉ የራሳቸው አመርቂ  ስራ ቢሰሩ ይሻል ነበር ። መቸ ለራሳቸውስ አመርቂ ስራ ሰሩና ።
Filed in: Amharic