>

የኦህዴድ መርሹ ብልጽግና አዲስ አበባን የመሰልቀጥ አጀንዳ...!!! (ሰይፉ ታሪኩ)

የኦህዴድ መርሹ ብልጽግና አዲስ አበባን የመሰልቀጥ አጀንዳ…!!!

ሰይፉ ታሪኩ


ጠ/ሚ አብይ  ያረንጓዴ ልማት ላይ ተሳክቶላቸዋል። አዲስ አበባንም ሽገር መጋላ የማድረግ እቅዳቸው የተሳካ ይመስላል።ከዚህ በኋላ አዲስ አበባ የአዲስ አበቤዎች አትሆንም።አዲስ አበቤዎችም የራሳቸውን ሻማ በረሳቸው እጅ ይሚለኩሱበት አጋጣሚ ተዘግቷል።ለችግኝ ተከላቸው እና ለፓርካቸው አሁንም ስኬታቸውን ተቀብለን ቅድሚያ መስጠት ያለባቸው አንግብጋቢ ጉዳይ መጠቆም እንወዳለን።ፈርንጆቹ “elephant in the room “ይሉታል።

ኦህዴድ መርሹ ብልጽግና ከአዲስ አበባ የዘለለ ፖለቲካ ያለው አይመስልም።የጠ/ሚ አብይ አዲስ አበባን ለማስዋብ በቢልየን የሚቆጠር ገንዘብ ማውጣታቸው…..ተገቢ ቢሆንም ቅድሚያ ሊሰጠው ይገባል ወይ ተብሎ ሲታሲብ አጠያያቂ ያደርግዋል ።በውስጧ የሚኖሩ ሕዝቦች ደህነት ከመቼውም በላይ ተባብሷል።የብዙዎች ህይወትም አደጋ ላይ ወድቋል። ።47% ነዋርዎቿ ቋሚ ገቢ የሌላቸውና ከድህነት ወለል በታች ናችው…..  የንጹህ ውሀ መጠጥ አቅርቦት የሌላቸው ናቸው  ።በድህነቱ ላይ ህዝቡ እሽግ ውሀ በመግዛት እየተበዘበዘ ነው ።በትንሹ እንኳ ብክሎሪን የነጻ የመጠጥ ውሀ ለነዋሪዎቿ መስጠት ያቃታት ከተማ ነች አዲስ አበባ ። ዛሬ ላስ ቤጋስ ብቻ የሚገኝ  የመንገድ ምሽት መብራት አስገባን ብሎ ፉከራ እንዳው ትንሽ ለመዋጥ ያስቸግራል።ማስረጃ እናቀርባለን፥-አዲስ አበባ በቂ የውሀናየመብራት አቅርቦት የሌልባት የአፍሪካ ከተማ ነች ሲል ኬንያ ዲይሊ ኔሽን 2003 አ.ም ስለ አዲስ አበባ እድገት ጽፎ ተችቷል። ያ ችግር አሁንም አለ።አዲስ አበባ 29ኙ ደሀ የአፍሪካ ከተሞች 24 ኛውን ትይዛለች በ መርሰር ሜድ(mercer ) አለማቀፍ የከተማ ልማት መስፈርት ።በፎርብስ ገልጻ ደግሞ አዲስ አበባ 6ኛዋ ቆሻሻ ከተማ ብሏታል ።የአፍሪካን ቢዝነስ ሜጋዚን ከአፍሪካ ከተሞች በኑሮ ደረጃ መለኪያ(ኳሊቲ ኦፍ ለይፍ)30ኛ ደርጃ ነው ያደረጋት።

የአለም ሜትሮ ፖሊታን ቻርተር በ2018 ባወጣው    አለም ከሚታውቁ ደሀ ከተማዎች ደርጃ 17 ተኛውን ይዛለች።ሌላው ባለመመቸትና በኢንፍራስራክቸር እንዲሁም   በሰርቪስ አሰጣጥ ከፍሪካ ከተሞች 34ኛውን እንደሆነች(ኢንፍራስርክቸር ኢን አፍሪካ) የሚባለው የሜትሮ ፓሊታን ጥናት መጽሄት 2018 አመታዊ እትሙ አስቀምጧል…..። ይህው መጽሄት መንገዶች ቁጥር አልባ…..፡ ቤቶችና ህንጻዎች ቁጥር አልባ…. በመሆናቸው አድራሻ….በቀላሉ..ለማግኘት(navigateለማድረግ)አስቸጋሪ መሆኑን ያትታል።.አንዳንዴም 21 ክፍለዘመን ላይ መሆናችን ማሰብ አዲስ አበባ ላይ ሆኖ ይከብዳል ይለናል።

2019 ዘ ኢንዲፐንዳንት መጋዚን ለኢንቨስትመንት ምቹ ካልሆኑ ከተሞች አንዷ መሆኗን ሲያትት የዩናትድ ስቴትስ  ክላይሜት ኦፍ ኢንቨስቲመንት የሚባለው ተቋም ኦክቶበር 2019 ባውጣው እትሙ ለኢንቨስትመንት አደገኛ ከተማ አድርጓታል።  ኢትዮጵያንም በጥቅልሉ  ለኢንቨስትምአንት አደኛ አገር ውስጥ  አስገብቷታል ።ይህ ብቻ አይደለም በሀገር ደርጃ 2010 አፍሪካን ቢዝነስ ቴክ የሚባልው  የጥናት ቡድን ለኢንቨስትመንት ምቹ ሀገር  ከ10 የፍሪካ አገሮች አንዷ ኢትዮጵያ ብሎ ሲበቃ  በ2020 ግን ደርጃ ወርዶ አስተማምኝ ሰላም የለም ይላል። ኢቨስትመንት ለማምጣት ረጅም መንገድ ይጠብቃታል ይላል።

ለዚህ ሁሉ ምክንያት ሰላም እጦት ነው!

ኢትዮጵያ በአሁኑ ሰአት  የሪሶአስና ለኢቨስትመንት ምቹ ባለመሆኗ ሳይሆን የአገሪቱ ፖለቲካ “አይንን ጨፍነው ሲገልጹ” ሁሉ ነገር በቅጽበት ተቀይሮ ሊያገኙት ይችላሉ በሚል የኒውስ ዊክ መጽሄት የሰኔ ወር 2020 እትም የጠ/ሚ አብይን መንግስት በገመገመበት ጽሁፉ ያቀረበውን ልብ ይሏል።

የጠ/ሚችንን ስራ እያጣታልኩ አይደለም ለምሳሌ ትሪፕ አድቫይዘር ይህንን ይጠ/ሚራችንን የከተማ ዙ ደርጃ ሰጥቶታል።ሳዲያጎ ካሊፎኒያ usa ያለውን ዙ አንዳኛ ሲደርግ አዲስ አበባ ያለውን ዙ መጨረሻ አድርጎታል።(the best and the worst በሚልው መስፈርቱ) ። አለም በጣም ጠባብ ነች አሁን።አይናችሁን ጨፍኑ ላሞኛችሁ ዘመን አልፎል።ከአለም አንደኛ ምናምን አትበሉን።

ጠ/ሚ አብይ ከቤተመንግስት ፊትለፊት ያለው ቦታ ጉርሻ ይሸጥበት እንደነበር ተናግረዋል።አሁን ታረኩ እንደተቀየረ ተናግረዋል።ምነው “የአሊባባን ታሪክ ባያስመስሉብን ጥሩ ነበር” አዎ ያ ቦታ ጉርሻ በመሽጥ እንደ አቅሚቲ ህይውት የምትቀጥልበት ቦታ ነበረ። አሁን እድሜ ለውያኔ  ጉርሻው ራሱ ሰፈሩን ቀየረ…

ከተከበርው ቤተመንግስት ጉርብትና ወደ ጅሞ ወደ ላፍቶ ወደ ጣፎ  ወደ መሪ. …. ወያኔ አፈናቀለቻቸው እንጂ የነሱ ህይወት ስለተለውጠ ወይም ትራንስፎርም ስላደረገ አይደለም ።አሁንም ተጎራባች ቀብሌዎች ተክልዬ.. ጎላን…. ጣሊያን ሰፈርና…. ገዳም ሰፈር ጉርሻ አለ።አመት አልሞላኝም አንዷን መትቻለሁ ።አሁን ግን 25 ሳንቲም አይደለም 25 ብር እንጂ ክቡርነትዎ

ይህ መሬት ቀድሞ ክፍት ሆኖ ያሁኑን ልማት ላድርግልህ ቢሉት  አብይ ካልሆነ አልቀበልም አይልም ነበር በርግጠኝነት። አሁንም የጠቅላይ ሚንስትራችንን ስራ እያጣጣልኩ አይደለም።ቅደም ተከተል ላይ ማተኮር አለበት መንግስታችን ለማለት ነው የተፈለገው።አንደኛ ሰላም….. ሁልትኛ ሰላም…… ሶስተኛ ሰላም……ቅድሚያ ሰላም በሁሉም ሁኔታ ጸጥታና ሰላም።

ያለዚያ የተተከለው በሆነ አጋጣሚ… በሆነ ቅጽበት ይነቀላል…የተሰራውም ይፈርሳል

ከዚ በመለስ ደሞ የከተማ ድህነትንና ምቹነትላይ… በሲርቪስ እና በኢንፍራስትራክቸር… ድህነት ቅነሳ ላይ ማተኮር ይቀድማል ለማለት ነው።መሰረታዊ ለውጥ  ለማምጣትም የስራ እድሎች ላይ ትኩረት አድርጎ ባይተዋሩ የአዲስ አበባ ወጣት ላይ መስራት ይገባል።በምግብ ራሱን ያልቻለ ሀገርና ሰላም ወጥቶ በሰላም መግባት የማይችል ህዝብ ባለበት ሀገር ላይ….ትንሿ ዱባይ በ4ኪሎ ፊለፊት ተሰርታለች ማለት ከባድ ነው። እነዚህ  ቅድሚያ  ችግሮች ፈትቶ ግን ወደ “ከተማ ውበት” ቢያቀና ጉዞው እጅግ ይመረጣል።ያ ማረም ይሆናል።

ጠ/ሚ ራችን እጅግ ወደ ሚወዷቸው የገልፍ አገሮች ፈታቸውን አስመትተው አዲስ አበባን ለማስዋብ የሄዱበት መንገድ ምን ያህል አድካሚ እንደሆነ ያሳያል። የገበታ ለሸገርም የሄዱበት መንገድ በጣም ብልጠት የተሞላው ቢሆንም ለሙስና እንዳይጋለጥ መጠንቀቅ ይጠይቃል። የአንጎላው  ፕሬዝዳንት ዶሴ ኤድውርዶ ዶሳንቶስ  በጦርነት የደቀቀችውን አገራቸውን ለማበልጸግ ተመሳሳይ መንገድ ነበር የተጠቀሙት። የሀገሪቱን የነዳጂ ከበርቴዎችና በአልሀብቶች ተቆጣጠሩ ።ከፕሪዝዳንቱ ጋር እራት ላይ የምታዩ vip  ዎች ተባሉ።ከህግ በላይ ሆኑ። አገሩቱ በሙስና ተጥለቀለቀች።ያ ብቻ አይደለም   ፕሪዝዳንቱ እጅግ ሀለኛ አደረጋቸው።ወጣትነት… ስልጣን… ባልጠግነት ተጨምሮበት አንጎላ በመዳፋቸው ውስጥ ገባች ።ቤተሰቦቻቸው በለጸጉ ዛሬ በአልማችን  ሀብታም ሴቶች   ከአማዞን ባለቤት ቤዞስ ማኪንዚ ቤዞስ  ጎን ከሚጠቀሱ ኤዛቤላ ዶሳንቶስ አንዷ ናት።38 አመት አገሪቱን የገተዙት ዶሳንቶስ ሀብታቸው ከርዮ ዲጀነሮ ጀምሮ እስከ ሎንዶን ተዘርግቶ ከ2017 ሰኔ ወር ጀምሮ በመርመር ላይ ይገኛል።  ወንድልጃቸውም እጂግ  በበዛ ሙስና የዛሬ ሁለት ቀን ዘብጥያ ወርዷል።

አጼ ሀይልስላሴ በጣም ገናና ያደርጋቸው እውቀታቸውና የዲፕሎማሲያዊ ብቃታቸው ብቻ ሳይሆን ያካበቱት ሀብትም መሆኑን መዘንጋት የለበትም።ዛሬ ጠ/ሚ ስትራችን የሀገሪቱ ቱጃሮች ከሳቸው አንድ ሜትር ርቀት እንዲሰባሰቡ አድርገዋል።ማን ምን ሀላፊነት እንዳለው አይታወቅም።በህግ የተቀመጠ ነገርም የለም።የኛ አገር  ሀብታም።የማይደማው ሀብታም ።ቻሪቲ የማያውቀው ሀብታም…… 10 ሚሊዮን አውጥቶ አጎንብሶ ይሄዳል  ብሎ ማመን የሚያዳግት ነው።የኢትዮጵያ ሀፕታሞች የሞራል ድሀዎች ናቸው።ከሙሁሩ እኩል የህዝቡ ችግር ናቸው።አብዛኛው በኑሮ ውድነት እንድንታበጥ ያረጉ ነብሰበላ ሀብታሞች ከጠ/ሚ አብይ ጋር እራት ተቀምጠዋል። በኢትዮጵያ ዉስጥም ሁለት ዜጋ ሊኖር ነው ። VIP እና መናኛ

የሸገር ገበታ የጌቶቹ ምሳ፡

የት አገኝሻለሁ ብቀመጥ ብነሳ ። ማለት ጀምሯል አዝማሪም።

ጠ/ሚ አብይ በአዲስ አበባ የመጣብኝንም አለቅም ብለውናል ጦርነትም ገባለሁ ብለውናል።እኛም እጅ ሰተናል።

የአዲስ አበባ ሰው ሰማይ ነው።ሁሉን ይችላል።አስገዶምን ከጉንዳጉንዶ…….ጨቤሳንም ከአቦምሳ እንቀበል የለ? ለከንቲባነትም?።

“በመልካም ጠርጥረው” ብልዋል አባት ሙፍቲ ሸህ እንድሪስ።እድሜቸውን ያብዛውና

በተለይ የጠ/ሚ አብይ አይነት ዲፕሎማሲያዊ አወሳሰድ(diplomatic  silent take over)

እየሳቁ እያሳስቁ እንደቀበና ወንዝ… እንሆ በመልካም ጠርጥረናል።

እኛ ኢትዮጵያውያን በስሜት ይምንነዳ ስለሆንን ሁልጊዜ

የፊታችንን እንጂ የዘመናትን አናስብም ። ተጽፎል ” ግዜውን ዋጁት ተብሎ” ዛሬ ሆናችሁ ነገን ያዙ. ….እንኪያስ ጠ/ሚንስትራችን እኛም በአፍሪካዋ ላስ ቬጋስ ተማርከናል።”ናኖ ኬና ሽገር መጋላ  ….ኒቢልሶና።”አ!

Attachments area
Filed in: Amharic