>
5:28 pm - Sunday October 10, 8675

ጠቅላዩና "ለምን ፣ እንዴት?" የማያውቀው ፓርላማቸው...!!! (ይድነቃቸው አዲስ)

ጠቅላዩና “ለምን ፣ እንዴት?” የማያውቀው ፓርላማቸው…!!!

በይድነቃቸው አዲስ

አምታታው በፓርላማ
“ፍርድ ቤት ለሚሰጣቸው ፍርዶች፣ ብያኔዎች፤ ምንም ሳናወላዳ መቀበል ያስፈልጋል። እኛ ያላከበርነው ፍርድ ቤት እኛ ያልታዘዝንለት ፍርድ ቤት ነፃ እና ገለልተኛ ሁን ማለት ከንቱ ነገር ነው የሚሆነው” ይህን ያሉት ጠቅላይ ሚኒስተር ዶ/ር አብይ አህመድ ዛሬ በፓርላማ በነበራቸው ቆይታ ነው።
– ይህን ባሉበት በዚች ቀን አቶ ልደቱ አያሌውን ለተደጋጋሚ ጊዜ ፍርድ ቤቱ ነፃ ቢለውም “ከላይ በመጣ ትዕዛዝ” በሚል ፖሊስ ሊለቀው አልቻለም። የፍርድ ቤት ዳኞቹም “ከዚህ በላይ ምን እናድርግ” በሚል ምሬታቸውን ገልፀው- የዳኞች ውሳኔ አለመከበር እንደሚያሳስባቸው ገልፀዋል። ክቡር ጠቅላይ ሚኒስተር የእቃቃ ጨዋታውን ትተው በቃልዎ ተገኙ። ህዝብ ይታዘባል።  ልደቱ በማን ትዕዛዝ ፍርድ ቤት የወሰነለት ውሳኔ ሊተገበር አለመቻሉት ለምናወቅ ይህ ንግግርዎ አሳዛኝ ነው። አሁንም ደጋግመን እንላለን- ከትላንት የህወሓት እብሪት ተማሩ። የህግ የበላይነትን አክብሩ!
ተማክረው መዋሸት እንኳን አልቻሉም !! 
———————
* ጠቅላይ ሚንስትሩ 6.1 በመቶ የኢኮነሚ ዕድገት
   አስመዝግበናል ሲል
* የገንዘብና ኢኮኖሚ ልማት ሚንስትሩ 7 በመቶ አድገናል  ብለዋል።
ጠቅላዩ ድፍረታቸው አይጣል ነው። ድንዝዝ ያሉት ፓርላማው አባላት ብቻ ሳይሆኑ ዓለም እንደሚሰማቸው እያወቁ ምንም ድንቅፍ ሳይላቸው …
“የነፍስ ወከፍ ገቢ (GDP per capita)  1ሺህ ዶላር ደርሰናል ብለው ሲያበቁ  ይህም መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ኢትዮጵያን ማሰለፏን ያረጋግጣል ብለው እርፍ አሉት።  እንኳን አቶ ቡልቻ ደመቅሳ ያልኖሩ   Lol
የጠቅላዩን በድፍረት የተሞላ ቅጥፈት  በቀላሉ ለመረዳት አጠቃላይ አመታዊ አማካይ ብሄራዊ ምርት፣ለጠቅላላ የህዝብ ቁጥር አካፍለን የእያንዳንዱን ሰው የነፍስ ወከፍ ገቢ እናገኛለን፡፡
እንደ ጠቅላዩ ገለፃ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ የነፍስ ወከፍ ገቢ አንድ ሽህ ዶላር ወይም (37 ሽህ ብር ) በዓመት ገቢ ያገኛል ብለን ተስማምተን ብናሰላው እንኳን …
1000 ሽህ ዶላር በአመት በ12 ወራት ሲካፈል 83.3 ዶላር ይሆናል ለ 30 ቀን ሲካፈል ደግሞ 2.8 ዶላር በቀን በ8 ሰዓት ሲካፈል 0.35 ሳንቲም እስኪ አሁን  በምን  ተዓምር ነው  መካከለኛ ገቢ ወዳላቸው አገራቶች ተርታ የምንገባው ?  ይሁን ብለን እሳቸው በጠሩት 1ሺ ዶላር  አስልተን በሰዓት 0.35 ሣንቲም እያገኘን  መካከለኛ ገቢ ካላቸው አገራት ተርታ ተሰልፈናል ማለት ምን ማለት ነው ?
የመካከለኛ ገቢ አገሮች የነፍስ ወከፍ ገቢ  በራሱ  1ሺ ሳይሆን 10.000 (አስር ሽህ ) ዶላር  መሆኑን አላውቀውም እያሉ ይሆን ??
Filed in: Amharic