>
5:28 pm - Saturday October 10, 7131

የማይበርድ የሥልጣን ጥማት....!!! (ሰይፉ ታሪኩ)

የማይበርድ የሥልጣን ጥማት….!!!

ሰይፉ ታሪኩ


 

በንጉስ ሄሮ ዘመን የነበረው ፊዚዚስት እና ማቲማቲሽያን አርኪሜዲስ ችግርላይ ወደቀ።የሳይንቲስቶችና የጠቢባን ቀበኛ የነበረው ንጉስ ሄሮ አስጠርቶት ሲበቃ”አናቴ ላይ ያለውን ዘውድ ንጽህ ወርቅ መሆኑን ወይም ቅልቅል በስቸኳይ እወቅ ተባለ።”ካላወክ ደግሞ ሞት ይጠብቅሀል ሆነ።

አርኩሜዲስ በጣም ተቸገረ ዘውዱን አያቀልጠው ነገር….በእጅይም አይነካው ነገር….ተቸገረ።አርኪሜዲስ የስትንፋሱ መጨረሻ እንደቀረበች አመነ።ቢሆንም ተስፋ አቆልረጠም።እሺ ጊዜ ይሰጠኝ አለ ።ንጉሱም ጊዜ ሰጠው። ቀንና ሊሊት ሞትን እያሰበ ምርምሩን ቀጠለ። በቃ የቻልውን የሚውቀውን የሚገምተውን ሁሉ ሞከረ አቃተው።የመጨረሻ ደቂቃ ከመምጣቷ በፊት ገላውን መታጠብ ፈለገ። ምነልባት ጭንቀቱን ቢያጥብለት አስቦ ይሆናል…..ምናልባትም መቃብር ሲገባ ጉጓዱን አካሉ ላይ ያለው ቆሻሻ እንዳይከብደው ፈርቶ ሊሆን ይችላል።

ምናልባት።….ብቻ አይታወቅም

የውሀ ገንዳውን በውሀ ሞላ ለመታጠብ ዝግጁ ሆነ።ልብሱን አውለቀ ገንዳው ውስጥ አንድ እግሩን አስገባ……በዚያው ቅጽበት ዩሪካ እያለ መጮህ ጀመረ።በመጮሕ ብቻ አልቆመም ከነመለመሉ ራቆቱን እየሮጠ ወደቤተ መንግስት አቀና።Eureka Eureka “አገኘሁት “እያለ።

አርኪሜድስ ቲዎሪ ከዛዘመን ጀምሮ ተተግብሮ እንማረውለን።”የማግለል ሳይንስ” decplesment.ማለት ነው።በውስን ፈሳሽ በተሞላ እቃላይ አንድ ጥጣር ነገር ብናስግባ ውሀው ይፈሳል። የፈሰሰው ውሀ ቢለካ ከጠጣሩ እኩል ነው።በሆኑም አርኪሜዲስ በድንገት በተገለጠለት ምርምር ውጤት ሞትን አመለጠ።”አገኘሁት”ዩሬካ ለረጅም ጊዜ ፈልገህው አንድ ነገር ስታጣው ፈርንጆቹ የአርኪሚድስን(EUREKA moment)የዩሬካን አጋጣሚ ይመኙልሀል።

ዶክተር ብርሀኑ ነጋ ድሮ ያኔ ወጣት ከነበረበት ጊዜ ጀምሮ ስልጣን እያሳደደ ነው። ግን አልተሳካለትም። እንደፈርንጆቹ አቆጣጠር በ1977 ኢትዮጵያን ነጻ ለማውጣት ከኢትዮጵያ ህዝቦች አብዮታዊ ፓርቲ ተቀላቅሎ አሲምባ ገባ። የአሲምባ የትግሬ እና የኢሀፓ ታጋዮች ለካ የሚበሉት አፈር በስኳር ነው፡፡ አንዳንዴ እንጨትም፡ ቅጠልም ነው። እነዚ ደግሞ የሚበሉት ለዛውም ከተገኙ እንደ እድልና አጋጣሚ ነው።

በአሲምባ ቆይታው የተማረን ያልተማረ ሊመራው አይገባም በሚል ንትርክ ሰበብ አርጎ ከተጋዳላይ ወደ ኮብላይ ተቀየረ። እናም እግር አውጭኝ ወደ ሱዳን።

ሱዳን ጥገኝነት አግኝቶ ወደ USA አቀና።በአሜሪካም የፕልፈር ዩንቨርስቲ ምሩቅ ሆነ ማለፊያ ነው። ግን ያቺ የዩሬካ ቅጽበት ልትመጣ አልቻለችም። በ1994አ.የእምቢልታ ጋዜጣ አዘጋጅ ሆነ።  የተጋዳላይ ስሜቱ እንዳዲስ ተቀጣጠለ።

ኤርትራን ባስገነጠሉ 2ኛው አመት1995 የ.ተ.መ.ድ.ስብሰባ ላይ አቶ መለስ ዜናዊ በክብር ተገኙ፡፡ አዲስና ወጣት መሪ፡ ጥሩ ተናጋሪ ፡እንዳውም ፡ ፈላስፋ ተባሉ። የኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣ መለስንና ኢሳያስን ተንትኖ ሲያበቃ”there is real chance of democracy” ብሎ ጻፈ። (ደግነቱ ኒዮርክ ታይምስ ጋዜጣ ለለፉት 75 አመታት በኢትዮጵያ ዙሪያ ትክክል ሆኖ አያውቅም) አቶ መለስ ከጉባኤው ጎን ለጎን ትኩርት የሚስብ ነገር ስሩ።

ለምሳሌ በኒዮርክ የሚገኘውን የኢንቫይሮመንት ጥበቃን ቢሮ በድንገት ጎበኙና በሪዮ ዲጀነሮ ሊካሄድ ለታቀደው ስብሰባ ድጋፍ ሰጡ። ማንም አፍሪካዊ መሪ ሞክሮትም እንደችግር አይቶትም ባለማወቁ. ….ይሄ ትልቅ የሚዲያ ጩህትን ፈጥሮላቸው ነበር። ከዚ ሌላ ኢትዮጵያውያንና ትውልደኢትዮፕያውያን ያነጋግሩ ነበር።ከነዚህም ውሥጥ የአሲምባ ፎቶአቸውን ይዘው ብቅያ ሉት ዶ/ርብርሀኑነጋ ይገኙበታል። መለስ ባያስታውሱትም…..ብቻ አስታወሱት በቦታው የነበሩ እንደሚያስረዱት።

ኢኮኖሚስት መሆኑን ተናግሮ የምርምር ጽሁፍ ሰጠ ለአቶ መለስ ዜናዊ። ወረቀት የሚበላው መለስ ያንብበውም አያንብበውም የታወቀ ነገር የለም ብቻ ተቀበለ።

ዶ/ር ብርሀኑ 1996 አ.ም የኢትዮጵያን ኢኮኖሚክ አሶሴሽን አቋቋመ። ወደ መለስ አቅናና ቢያንስ የኢኮኖሚ ልማት ሚኒስትርነት ቦታ ይገኝ እንደሆነ ቢጠይቅም አልተሳካም። የሚመኛት የዩሬካ ቅጽበት አሁንም አልመጣችም። እነፕሮፌሰር መስፍንን ይዞ መታገልን መርጠ። ከሰብአዊ መብት ጉባኤ ራሳቸውን ያገለሉት አንጋፋው ፖለቲከኛ ከኋላ ሆነው በመምራት ቀስተደመና ተቋቋመ። ታሰሩ፡ተፈቱ፡፡

2003 የፓርቲዎች ውህደት አዲስ አየር ነፈሰ።ቅንጅት፡አንድነት ለፍትህ ለዲምራሲ ተቁቁመ። በአልታሰበ ፍጥነት ቅንጅቱ አገርን ማዳረሱ አሁን ላይ ሆነው ሲስቡት ያስገርማል።

ምርጫ 2005 ግንቦት ወር ተካሄደ። ቅንጂት ኢሀዴግ ባምነው 517 ወንበር 180 ወንበር አሽነፈ። አዲስ አበባ ከ138 ውስጥ 137 ቱን ማሽነፉ ተነገረ።በመላ ሀገርቱ ያሉ ዋና ከተማዎች ከመቀለ በስተቀር ቅንጅቶች ማሽነፋቸውን በማግስቱ ጠ/ሚ መለስ በፋና ሬድዬ ለደጋፊዋቻቸው አውጁ ሀዘን እና ተስፋ የተሞላ መላእክት አስተላለፉ,።”ህዝቡ ቅንጅትን ስለውደ ሳይሆን እኛ ስለጠላ ነው”አሉ መለስ ለደጋፊዋቻቸው። አሁን ያቺ ተአምረኛ ዶ/ር ብርሀኑ ዩሬካ ቅጽበት መጣች።ለስልጣን ቸኩሏል…..

ነገር ግን ዶ/ር ብርሀኑና ጓደኞቹ ሕዝብ የሰጠውን ድምጽ ሳይቀበልሉ ቀሩ።የአቶ ልደቱ ፓርቲ ስለሆነ በአብዛኛው ብቅንጅቱ ውስጥ ያሽነፈው ገናለገና ትልቁን የስልጣን ድርሻ ልደቱ ሊወስድ ይችላል በሚል ሥም ማጥፋት እና የባህሪ ገደላ (caracter assasnation) በዶ/ር ብርሀኑ አቀነባባሪነት በነጻ ፕሪስ ፊተውርውሪነት በሰፊው ተፈጸመ።ቅንጅት “እንደ ሙቀጫ ተንከባለለ” ቢንጎ….!።የወያኔ መንግስት በደስታ እየነዳች ቃሊቲ አወርደቻቸው።የ ዶ/ር ብርሀኑ……የዩሬካ ቅጽበት እንደገና ማእበል መታው….

ግንቦት 7 2008 አመተ ምረት “ግንቦት 7 ፓርቲ” ተመሰረተ።የተቃዋሚ ሀይሎች ምስረታ ውይይት ተጀመረ ኦነግን ጨምሮ። አልተሳካም።ለምን? የኢትዮጵያ ተቃዋሚዎች ” ሆዳቸው አንድ ጭንቅላታቸው አስር ስለሆነ”።

ቀጣይ ወያኔን ተቃውሞውና ትግሉ በኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪቭን ሆነ።ወያኔን ድንገት ሳይታሰብ ሳይዘጋጁ ማእበል መታት ነሀሴ 20 /2012 አቶ መለስ ዜናዊ ሞቱ።የአሜሪካ ኮንግረስ አባላት ከዚ በኋላ እንደልብ እንደሚገኙ የታወቀ ሆነ።የዶ/ር ብርሀኑ ዩሬካ ቅጽበት እንደገና አንሰራራች።

2013 መለስ የሌለበት ፖለቲካ ቢያንስ የዲፕሎማሲዊ እና የቁሳዊ የበላይነት ሊስገኝ እንደሚችል ያመነው ዶ/ ር ብርሀኑ ከተቃሚዎች ጋር ህብረት ለመፍጠር በድጋሚ ውይይት ጀመረ።ኦነግ በልዩነቱ አብሮ ሊታገል ተስማማ.።4 ኦነጎች ነበሩ ስማቸውን ቢቀይሩ የዲማ ነጎ፡የለንጮ ለታ፡ከማል ገልቹና የዳውድ ኢብሳ። የትግርዩ ደምሂት እና አርበኞችን ለመቀላቀል ተሞከረ አልተቻለም።ከአፋር ህዝብ ፓርቲ ኪትዮጵያ አንድነት ለፍትህ ፓርቲ እንዲሁም ኢትዮጵያ ለፍትህና ለድድሞክራሲ ጥምረት ግንባር ፈጠሩ።ይህ የዲሲ የተለመደ የዲያስፖራ ፓርቲ ስለሆነ እውነተኛ በተግባር የትደገፈ ፓርቲ መቀላቀል እንደሚስፈልግ በመታመኑ በትጥቅ ትግል ላይ ያሉትን የአርበኞች ግንባር የአማራ አንድነት ድርጂት እና ደምሂት አንድ አድርጎ ለመታገል እንውስቃሴ ተጀመረ። አርበኞች እና የአማራ አንድነት ድርጂት ከግቦት 7 ጋር እንዲቀልቀሉ ጥሪ ተካሄደ።ሁለቱም ፈቃደኛ ሳይሆኑ ቀሩ።

ሁለት ስትራቴጂ ተነደፈ ይመጀመሪያው አቶ አዳርጋቸው ጽጌ ከአርበኞች ጋር ቀድሞ ግንኙነት ያለው በምሆኑ እሱ እንዲያግባባቸው ማድረግ ሲሆን ሌላው ኢሳያስ አፈወርቂን አግኝቶ ማነጋናገር ሆነ።

በአሜርካ በሚገኘው የኤርትራ ቆንስላ ጽፈት ቤት አማካኝነት የተገኙት ኢሳያስ አፈወርቂ ማነጋገር ብቻ ሳይሆን በኤርትራ መሬት ላይ ኦፕሬሽን እንዲካሂዱ ፈቀዱ። ከኢሳት ጋርም ቃለምልልስ አደረጉ።ኢሳትና ዶ/ር ብርሀኑ አቶ ኢሳያስ ኢትዮጵያን እንደሚወድ ስብከት ተጀመሩ።
በዚ ሂደት ውስጥ አቶ የማነ ገብረአብ የአርብኛውን አመራር አስጠርተው አስፈራሩ ።እንዲዋሀዱም ባስቸኳይ መመሪያ ሰጡ።

አቶ አንዳርጋቸው ምነምን ዘለቀ እነ ዶ/ር አዚዝ በአስመራ ተገኙ።አርበኞች ግንቦት 7 በኢሳያስ አፈውርቂ መንግስት ተጽኖ ውህደት ተፈጸመ።ለዲያስፖራ ገንዘብ መሰሰቢያ ፎቶና ቪዲዮ ሲያነሱ ከረሙ ወደ አሜሪካ ተመለሱ። mission accompliched (የተሳካ ተልእኮ) ነበር።አንዳርጋቸውና ቡድኑ የቀርጹትን ፊልም ለ ዶ/ር ብርሀኑ ገንዘብ መለመኛ አስረክበው ወደ አስመራ ተመለሱ።በአስመራ ትንሽ ቆይታ በኋላ አንዳርጋቸው ወደ DC ተመለስ።ፐሮፖጋንዳው ተጧጧፈ።የተቃዋሚዎችም ውህደት እንዲሁ።

ብዙም ሳይቆይ ከአሜሪካ መልስ አንዳርጋቸው ተጠለፈ።ይሄ ትልቅ ሎተሪ ነበር ለዶ/ር ብርሀኑ።በቀላሉ የአንዳርጋቸው፡መጠለፍ በተለይ ዲያስፖራውን አንድ አደርገው።

በኢሀዴግ ጠላቻ በሀገር ፍርቅር ስሜት የታሰረው ዲያስፖራ ወያኔን ለማስወገድ አንድነቱን ለማስመለስ ለሚደረገው ትግል የውታደራዊ ስንቅናትጥቅ መግዣ በገፍ ሰጠ። ከዋሽንግተን ዲሲ እስከ አውሮፓ ኖርዌይ ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ተሰበሰበ።

አሁን ደ/ር ብርሀኑ ነጋ ኤርትራ ዘለቀ። ከኢሳያስ አፈውርቂ ጋርም በአካል ተገናኙ። በትክክል ምክንያቱ አይታወቅ እንጂ ከውቅቱ የግብጽ ደህንነት ሹም ጋር ካይሮ ላይ በሁለቱም የደርሶ መልስ ጉዞ ተገናኝቷል።(ስልዚ ጉዳይ ሲጠየቅ
“ከየትኛውም አቅጣጫ እርዳታ ካገኝን እንቀበልስለን ነው ያለው”)

ወደዋሺንግተን ሲመለሱ ከሚታዩት አርበኞች ተንቀሳቃሽ ምስል ጋር የዲስፖራው ተሳትፎ ሞራል እንደተጠበቀው ማእበል ሆነ። ከገንዘብ በተጨማሪ ነጻነትን እውነት ለማድረግ የአውሮፓ ጂሀዲስቶች አይሲስ ወደሚገኙበት ወደ ሶርያ ሲሄዱ ኢትዮጵያውያን ከወያኔ ነጻ እንደምትወጣ ያመኑ ደግሞ ወድ ኤርትራ አቀኑ። ትልቅ ስኬት ተባለ። የድ/ር ብርሀኑ የዩሬካ ቅጽበት ቅርብ እየሆነ መጣ።

ሚዚያዝ24/2015 አርበኛዉ ፕሮፌሰር ብርሀኑ ነጋ ወደ ዳግማዊ አሲምባ ተጠቃሎ ገባ ተባለ። ይሄኛው ግን ልዩነት አለው ከተማዋም አስመራ ነች የጉራጌ ክትፎ ባይገኝ ካርቤቶ አለ።ሜታ ቢራ ባይኖር ሞሎቲ አለ።ታጋዩም ከአስመራ ከተማ ሳይወጣ..ይሰንብታል ኦፕሮፖጋንዳው ግን ጋሽ ባርካ ላይ ዶ/ሩ የጦር አዛዥ ሆኖ እያዋጋ እንደነበረ ነው።እሱ ግን ወጣም ካለ ደግሞ የሚሄደው ለጉብኝት ብቻ ነበር ለዛውም በሻብያ

ወታደሮች ታጅቦ።ብዙውን ጊዜ የኢትዮፕጵያን ባንዲራ አሲዞ አርብኞቹን ፎቶ ከማንሳት የዘለል እንስቃሴ አልነበረም። ወቅታዊ መረጃን ለደጋፌዎች ገንዘብ ለማሰባሰብ እና ወያኔን ለማስደንበር ይጠቀምሙበት ነበር።የወታደራዊ ዩንፎርም ለብሶ የሚለቀቁ ፎቶዎች አብዛኛዎቹ በቅንብር እንጂ ከታግዮች ጋር ቆይታ ፈጽሞ ኖሮት አይደለም።ከወር በላይ የቆየበት አጋጣሚ የለም እሱም በአስመራ ነው።መመላለሱንና የኢሳያስ አፈውርቂ ሰዎች ጋር እስከመጨረሻው ተጣብቆ እንደነበረ ታጋዮቹ አሁንም በህይወት አሉ ያስረዳሉ።በሌላ መልኩ በነአቶ መአዛው የሚመራው የቀድሞው አርብኛው ግን በአብድራፊ፡ በመተማ፡ በሳንጃና ከፊል ጎንደር እስክ ዳባት ዳንሻ ድረስ ሽምቅ ውጊያውን አጧጡፎ ነበር።ይህን እንቅስቃሴ በዶ/ር ብርሀኑ እንደሚመራ ተናገረ ይህም ራሱ ከብዙ ውሽቶች ውሳጥ አንዱ ነው ይላሉ በህይወት ያሉ ታጋዮቹ።

ዶ/ር ብርሀኑ በአብዛኛው ሲደርግ የነበረው የፕሮፓጋንዳው ፈረስ ከውጭ አገር በመጫን ወያኔን በሀገርውስጥ ነውጥ ማንበርከክ ነበር።ኤርትራ በቀንደኛነት ተሳታፊ ነበረች። ሶሻል ሚድያዎች በአማራ በትግሬ በኦሮሞ ስሞች በመቶ የሚቆጠሩ ፌስ ቡኮች ተክፍተው ኦፕሬት ማድረግ ነበር ዋና ስራቸው ይላሉ አሁንም በህይወት ያሉ ታጋዮች።በመሆኑም በተሳካው ፕሮፖግንዳ ኢትዮጵያን የሳት ቋያ ለበለባት።ወያኔ በመላም በዱላም አገሪቱ መግዛት አቃታት በየቀኑ በአዳዲስ አስቸኳይ ጊዜ አዋጆች በማውጣት አገር ማስተዳደር ሞከረች።

2017 መስከረም ወር ኢሬቻ የኦሮሞን አመጽ የወያኔን መጨረሻ መጀመሪያ መሆኑን አሳየ። የፕ/ር ብርሀኑ የዩሬካ ቅጽበት ቀረበች። በግልጽ ወታደራዊ ልብስ አርገው ወያኔን ማስጠንቀቅ ያዙ።

ኦህዴድ አማራን ጋልቦ ወደፊት ገሰገስ። ኢሀዲግ የውስጥ ለውጥ አመጣ።ፈዛዛው ሀይለማሪያም በንቁው ወጣት መሪ ተተካ።

የፕ/ር ብርሀኑ ነጋ የዩሬካ ቅጽበት ቀርበች።
አዲሱ መሪ የአስመራ ሹርቤዎች ነብይ አሉት ጓየላ ወርዱለት።superman ሱፕርማን ተባለ።7ኛው ንጉስ ተባለ።እንደአሽን የፈሉት ሐዋርያቶች እና ነብዮች “የኢትዮጵያ ሙሴ፡መድህንና ነብይ “መሆኑን በእግዚያብሄር ተናገረኝ ፋሽን” በየፕሮቴስታንቱ ቤ/ስቲያን ተገለጠ። ፕ/ር ብርሀኑ በግልጽ ስማቸው ተጠርቶ በፓርላማ ይቅርታ ተጠየቁ።ጥሪም ተላለፈ።

በቃ ክላሽ አያስፈልግም ባንዲራን አንገት ላይ አድርጎ ከነ ከግብራበሮቹ ከዋሽንግተን ዲስ ወደ ከዷት አዲስ አበባ በታላቅ አጀብድና ጀግንነት ታጅበው ገቡ። ሰርግና ምላሹ አበቃ ።

የቄሮ ዘመን ተጀመረ

ብዙምአልቆየበቡራዩየኦሮሞብሄረሰብተውላጅባልሆኑላይየበደኖእናየውተርአይነትጭፍጨፋ ተመሳሳይበዜጎችላይተፈጸመ ።የገደሉት እያሉ የአዲስ አበባ ወጣቶች ጫት በመቃምና ሺሻ በማጨስ ውንጀል በኦሮምያ ፓሊስ ተለቅመው ውደጦላይ ተጫኑ።

ፕ/ር ብርሀኑ ድርጊቱን እንኳ አላወገዘም።ቀጠለ በጉጂ ኦሮሞ ጭፍጨፋ ተካሄደ ቢያንስ ድርጊቱን ከሰበዊነት አኳያ እንኳ አላወገዘም።ቀጠል በሰሜንሽዋ በአጣዬአና አካባቢዋ ዘግናኝ ጭፈጨፋ በቄሮ ተካሄደ አሁንም ዝምታው ቀጣለ በምንጃርና ሽንኮራ ተጎራባቾች ቀበሌዎች ለይ እንዲሁ፡ጭፍጨፋ ተከሄደ ፕ/ር ብርሀኑ እና ጓደኞቹ አሁንም አላወገዙም።በደንቢዶሎ የአማራ ተውላጅ የሆኑ አንስት ተማሪዎች ተጠለፉ አሁንም አላወገዘም ።ማእራብ ኦሮምያ የሚኖአሩ አማሮች ከቴፒ እስከ ደንቢዶሎ.. ..ከሀረር ጭናቅሰን እስከ ባሌ ሮቤ በቄሮ ገጀራ ተበሉ።ፕሮፌሰሩ አሁንም ዝምታን መርጠ። የአሩሲው ማእበል አሜርካዊው ጃውር ሙሀመድ ባስነሳው የፐለቲካ አቧራ 200 ሰው በላይ አለቀ። ዶ/ር ብርሀኑ ዝም አለ።

ሀጫሉ የቄሮ ኦሮሞ ፈርስት አቀንቃኝ ተገደለ። ከሰኔ 30 ጀምሮ የኦርቶዶክስ ቤተክርስቲያን አማኞች እና አባቶች ላይ አማራ እና ክርስቲያን በመሆናቸው ብቻ ታረዱ ።የአማራ ሀብትና ንብረት ላይ ተዘመተ።ዶ/ር ብርሀኑ አለም አውግዞ ከጨረሰ በኋላ የድርጊቱን አሳዛኝነት አልሳልሶ አቀረበ ። ይህ ሁሉ አብይ ትንሽ ክፍተት ፈልጎ ለስልጣን መጋራት የሚበቃ የይለፍ ካርድ ይሰጠናል የሚል ምኞት ነው።

ይህ ብቻ ታከለ ኦማ ከአሩሲ ከባሌ ከውለጋ ከሀረር ቂሮ እያመጣ ሶሻል social enginering ሲርግ ዝምታን መርጠጧል።ዝምታ መምረጥን ብቻ ሳይሆን የጠ/ሚ አብይ አብሪ ጥይት በመሆን የፕሮፖጋንዳ ስራ የሰራበትን ወቅት ያስታውሷል።

እንዳውም ድምጹን ለተነጠቀው የአዲስ አበባ ህዝብ ድምጽ ለመሆን የሞከረውን ባልደርሱን ና ታጋይ እስክንድር ነጋን በመንግስት በማስጠቆር ከጀርባ የሚንቀሳቀሰው ዶ/ር ብርሀኑ ነበር።

ይህ ብቻ አይደለም የመላው አዲስ አበባ ህዝብ ቄሮ በሚባለው የሽፍታ ቡድን ህልውናው አደጋላይ ውድቆ ዝምታን ነው የመረጠው። የአዲስ አበባ ህዝብ ከ138 ወንበር ውስጥ አንድ ብቻ ሲቀር ድምጽ የሰጠው ዶ/ር ብርሀኑ አልቀበም ብሎ ለዚህ ሁሉ መክራ ይየጣለን የስልጣን ረሀብተኛ ነው።የዲስ አበቤዎችን መታነቂያ ገመድ ያቀበለ ነው። የጊዜ ጉዳይ ነው ዶ/ር ብርሀኑ ስልጣን ለማግኘት የትኛውንም ካርድ የሚመዝ” 40 አመት ስልጣን አርግዞ የሚኖር ሰው ” ነው።ዶ/ር ብርሀኑ ያለበት የተቃዋሚ ስብስብም። ትርፉ ኪሳራ ነው።ልእውነተኛ

የፖለቲካ ለውጥ የሚታገሉ ብዙ ኢዜማ ውስጥ እንዳሉ እናውቃለን በስተመጨርሻም ቢሆን ዶ/ር ብርሀኑ እንዴት እንደፈቀደላቸውም ባይታወቅም በአዲስ አበባ ላይ እይተሰራ ያለውን ሽፍጥ ለመናገር ሞክረዋል። አዲስ አበቦች ምን ያህል የከፋ ጨለማ ላይ እንደውደቁ አርጋግጠዋ በጥቂት ኢዜማውስጥ ባሉ ዝምታው ይሰበር ብለው በደፈሩ ጀግኖች ነው ይሄ ሊሆን የቻለው ።አስፈላጊ ከሆነ በስምም መጥቀስ እንችላለን።አሁን እስክንድር ነጋ ሲጮህ ነበረው ለፍትህ መሆኑን ዘግይተው መረዳታቸው ተገቢ ነው።አዎ ስለ አዲስ አበባ ህዝብ እና ላልፉት ሁለት አመታት በአማራው ህዝብ ላይ እየደረስ ያለው ጭፍጨፋ ሳይሆን ዶ/ር ብርሀኑ የሚስበው የኢሳያስ አፈውርቂና የዶ/ር አብይ ስልጣን ነው ግድ የሚለው።አዎ ዳህላክ ላይ ውድውፊት የሚያሰራው ሪዞርትናአሁን በኢትዮጵያ ያሉ ኢንቨስትመንቶቹ ናቸው የሚሳስቡት።ባስታ!

Filed in: Amharic