>
5:28 pm - Tuesday October 10, 5758

በአዲስ አበባ ራስ ገዝ ጉዳይ ባልደራስ ፊት አውራሪ ሆኖ የስድስት ፓርቲዎች ጥምረትና ንቅናቄ ፈጥሯል..!!! (ወግደረስ ጤናው)

በአዲስ አበባ ራስ ገዝ ጉዳይ ባልደራስ ፊት አውራሪ ሆኖ የስድስት ፓርቲዎች ጥምረትና ንቅናቄ ፈጥሯል..!!!

ወግደረስ ጤናው

አዲስ ክስተት የሆነው የኢዜማ መንሸራተት ሆኗል …!!!
በዛሬው ዕለት በባልደራስ ዋና ፅ/ቤት በአዲስ አበባ ራስ ገዝነት ጥያቄ ዙሪያ ቀድሞ ቀጥሮ ከያዙት 6 ፓርቲዎች በተጨማሪ ሌሎችም ተካተው ውይይቱ እየተካሄደ ይገኛል።
ባልደራስ ለእውነተኛ ዴሞክራሲ ፓርቲ ፊት አውራሪ ሆኖ ያስጀመረው የአዲስ አበባ ራስ ገዝነት ጥያቄ ዛሬም በሌሎች ፓርቲዎች ንቅናቄን በመፍጠር ተጠናክሮ ቀጥሏል።
የአዲስ አበባ ከተማ ህዝብ የራስ ገዝነት ጥያቄውን ተቀብሎ በባልደራስ 5ቱም ፅ/ቤቶች የፊርማ ድጋፍ ማካሄድ ከጀመረ ቀናት ተቆጥረዋል።
ስብሰባው ምን ውሳኔ አሳልፎ ተጠናቀቀ…?
በባልደራስ ዋና ፅ/ቤት የተካሄደው ሁለተኛው ዙር የአዲስ አበባ የራስ ገዝነት ጥያቄ በቀጣይ ከሁለት ሳምንት በኋላ ሰለ አፈፃፀሙ ለመወያየት ለሶስተኛ ጊዜ በመቀጥር ተጠናቀቅ!!
በውይይቱ ምን ምን ጉዳዮች ተነሱ….
ኢዜማ…..የአዲስ አባባን ጉዳይ በተናጥል የምናይበት ምክንያት የለም።
#መኢአድ…. የባልደራስ በአዲስ አበባ ላይ የያዝውን አቋም ዛሬም ከፊትም ከኋላም ሆነን ከማገዝ ውጭ አማራጭ የለንም።
#አብሮነት…በመሰረታዊ ሃሳቡ እጅግ እንስማማለን። በቀጣይ ለሚመሰረተው የጋራ ኮሚቴ አብሮነት የሶስት ፓርቲዎች ድምር ስለሆነ መክረን እንድንመጣ ጊዜ ይሰጠን።
#አብን….በአዲስ አበባ ያለውን አፓርታይዳውይ አካሄድ እጅግ እንቃወማለን። በአዲስ አበባ የራስ ገዝነት ጥያቄ እኛም ተወያይተንበታል። ይሁን እንጅ ዛሬ የመጀመሪያ ተሳትፎአችን ስለሆነ በጋራ ኮሚቴው ጉዳይ በቀጣይ ከአስፈፃሚው አካል ጋር ተወያይተን ለመምጣት ጊዜ ይሰጠን!
#የጋምቤላ ህዝቦች ፓርቲ….አዲስ አበባ የሁሉም ከተማ ናት። እንኳን የአዲስ አበባ ከተማ ኗዋሪ ይቅርና የአፍሪካ መዲናም ናት። ስለዚህ በቀጣይ መክረን መጥተን እንወያያለን።
#ኢዲህ….የባልደራስ ሃሳብ ባዲስ አበባ ጉዳይ ላይ የያዘው አቋም የኛም ነው። ስለዚህ በማንኛውም ጉዳይ ከጎናችሁ ነን።
ተራማጅ….ባልደራስ ያነሳው አቋም ምንም የሚያወላዳ አይደለም። ባልደራስም ቢሆን ብዙ ፓርቲዎችን በዚህ ጉዳይ እንዲደግፉት መጠየቅ የለበትም ።የጠሩና አቋም ያላቸውን ብቻ አካቶ ባስቸኳይ የጀመረውን ማስቀጠል አለበት።
#ባልደራስ….የአዲስ አበባ የራስ ገዝነትን ጥያቄ  መፈታት የኢትዮጵያን ምስቅል የፖለቲካ ችግር መፍቻ አንዱና ዋነኛው ቁልፍ ነው።
ሰበር የመንሸራተት ዜና
በመጀመሪያው ዙር ምክክር ላይ ኢዜማ (የኢትዮጵያ ዜጎች ለማህበራዊ ፍትህ)
በአዲስ አበባ ከተማ የራስ ገዝነት ጥያቄ ላይ ከያዘው አቋም በመንሸራተት …ዛሬ ላይ…ከፓርቲዎች የጋራ ውይይት  እራሴን አግልያለሁ ሲል በላካቸው ተወካዮቹ አማካኝነት አሳውቋል።
ድል ለዴሞክራሲ!
ምክክሩ በቀጣይ ከሁለት ሳምንት በኋላ ለሶስተኛ ጊዜ እንዲካሄድ ተወሰኖ የዛሬው ምክክር በሰላም ተጠናቋል።
ድል ለዴሞክራሲ!
ጥቅምት 2013
Filed in: Amharic