>
5:13 pm - Tuesday April 18, 4643

እኛ እያወራን ያለነው መተኪያ ስለሌለው የሰው ልጅ ህይወት ፤ እናንተ የምታወሩልን ስለ ልማት... በምን እንግባባ...??? (መርእድ እስጢፋኖስ)

እኛ እያወራን ያለነው መተኪያ ስለሌለው የሰው ልጅ ህይወት ፤ እናንተ የምታወሩልን ስለ ልማት… በምን እንግባባ…???

መርእድ እስጢፋኖስ


በጥቅሉ 30 አመት ሆኖታል።በተለይ ደግሞ 3 አመት ሆኖታል።የመጀሪው ዙር በወያኔ መሪነት ለ27 አመት አመት የተካሄደ ነው።ሁለተኛው ዙር ደሞ ወያኔ በወላደቻቸው ቄሮዎች እና ኦነጎች የቀጠለ የዘር  ጭፍጨፋ ነው።
ተስፋ ያደረግንባቸው ስለ ኢትዮጲያ የሰበኩን ጠቅላይ ሚ /ር አብይ በህዝብ ተውካዮች ምክር ቤት ተገኝተው በሰጡት ማብራሪያ “የምሰራውን ልማት እዩ …. የተከልኩትን ዛፍ እዩ….  እንጦጦን ፓርክ እዩ…..  ሽገር ፓርክን እዩ ….. በተለይ ለፓርኮቹ አንድም የመንግስ በጀት ሳልጠይቅ ተአምር የሰራሁትን እዮ ብለዋል።
እኛም አይናችንን አልጨፈንም አይተናል።ገንዘብ ሊሰራ የሚችለውን አይተናል።ተቃውሞ የለንም የአድናቆት ችጋራሞችም አይደለንም።እኛ እያወራን ያለነው በገንዘብም በእውቀትም ማንም ሊመልሳት የማይችላትን ውድ “ነብስ ” ጉዳይ ነው።
እኛ እያወራን ያለለነው እርስዎ ለሚኩራሩበት ለአባይ ግድብ ላለፉት 9 አመታት ከመቀነቷ ፈትታ ገንዘቧን ስታዋጣ ለነበረችው በግፍ ስለታረደችው ደሀ እናት ነው።
እኛ እያወራን ያለነው ግብር የሚከፍለው ገበሬው በአራጆች እጅ እየተቀጠፈ ስላለ ነው። እኛ እያውራን ያለነው እርስዎ ሰራሁ ላሉት ልማት ገንዘቡን ያዋጣው ገበሬ እርስዎ በሚያውቋቸው መደዴዎች መገደሉ ማብቂው የት ላይ  እንደሆነ ውሉ ስልጠፋን ነው።
እኛ እያውራን ያለነው እርስዎና አመራርዎ ስለማታወሩት ነው ።ስልማትናገሩት ስለምትደብቁት ነው። ለመሆኑ ጠ/ሚ አብይ” ሕይወቱን ያጣው እያለ እሱ ባዋጣው ገንዘብ ለተሰራ ልማት ጮቤ እንርገጥ?”
24 ሰአት የሚሰበክላቸው የርስዎ ፓርኮችዎ በራስዎ መንገድ እንዳሰሩ በመኩራራት ተናግረዎል። አዎ 60% በድህነት የሚኖር ህዝብን በኑሮ ውድነት የሚጠብሱ ወንጀለኛ ነጋዴዎች የተሰበሰበ ገንዘብ ነው።corrupt ከሆኑ የኢትዮጵያ አላግባብ ከበለጽጉ  ሚሊየንሮች የውሰዱት  ገንዘብ ነው። የርስዎ ሀብታሞች ከሰማይ አልዘነበልቸውም።ከድሀው ህዝብ ባንድም በሌላም መንገድ የሰበሰቡት ነው።በኢትዮጵያ በስራና በችሎታቸው የበለጸጉ ሀብታሞች በጣት የሚቆጠሩ ናቸው።ይታወቃሉ።ስለዚ አሁንም ለርስዎ ፓርክ ያዋጣው ድሀው ኢትዮጵያዊ ነው።መልካም ስራ ልዩ ዲስኩር አያፈልገውም እኮ።ይሄ ድሀ ወገን ግን እይታጨደ ነው በግፍ።ለምን?
የተከበሩ ጠ/ሚ እርስዎ እንጦጦ ፓርክን ሲመርቁ በዛው እለት 14 አማራዎች መተከል ላይ ተገደሉ። መረጃው እንደመሪ ይኖርዎታል።ቢያንስ ድርጊቱን በዛው መድረክ ማውገዝ ሲችሉ ዝምታን ነው የመረጡት።ማውገዝ ቢያንስ ማውገዝ ምን ያህል ዋጋ ይጠይቃል?
እናስታውሳለን 2019 አ.ም 25ኛ አመት የሩዋንዳ ጂኖሳይድ መታሰቢያ በአል ላይ በኪጋሊ ተገኝተው ሩዋንዳውያን ያለፍበትን እና የደረሱበትን ባደነቁበት እለት በአጣዮ በካራቆሬ በማጀቴ 75 አማራዎች በግፍ የተጨፈጨፉበት 2ኛ ቀን ነበር።ከዚያ የበለጠ መልካም አጋጣሚ አልነበረም ግን ለማውገዝ እንኳ አልሞከሩም።እንዲህ እያልን መቀጠል እንችላለን ማለቂያ የለውም። እያወራን ያለነው ስለሰው ህይወት ነው።
የርስዎን ስራ ያሳነሰ የለም ።ከዛፍና ከሰው ዛፍን መርጠዋል ነው።የእርስዎ ሚድያ በየቀኑ ስለሠሩት ፓርክ እና ስል ኢኮኖሚው እድገት የተዛባ መረጃ ላይ ቀኑን ሙሉ ሲያባክን ለአንዲት ደቂቃ እንኳን ስለሚገደሉ ሰዎች  ሲያወራ ተሰምቶ አያውም።
በፈረንሳይ ሀገር በ18 አመት አፍጋንስታናዊ ጂሀዲስት ሳሙኤል ፓቲ የተባሉ መምህር ታረዱ።ከፈረንሳይ ዘልቆ መላ አለምን አስደንግጧል።ይህ አሳዛኝ ክስተት ታዲያ ሁሉንም ሙስሊም ፈረሳዊ የሚወክል ባይሆንም በዋናነት ሀላፊነትን እየውሰዱ ያሉት ለህሊናቸው ያደሩ ሙስሊም ፈረንሳያን ናቸው።ምክንያቱም ነገ በነሱ ላይ ሊደርስ ይችላል።ስለዚህ ከክርስቲያን ወንድሞቻቸው ጋር በመሆን በማውገዝ መንግስት በሚወስደው እርምጃ ላይ ተባባሪ እይሆኑ ይገኛሉ።
መምህር ሳሙኤል ከታረዱበት እለት ጀምሮ ትላንት በታላቅ ከብር ሬሳቸው እስካረፈበት ኦክቶበር 21

/2020 በከማሼ በቢንሻንጉል በምተከል 27 ሰው ሞቷል።የኛ መንግስት ቁርጠኝነት ስለሌለው ነው እንጂ ይሄ ድርጊት ፈጽሞ ኢትዮጵያዊ ስላልሆነ ሊቆም በተገባው።ዛሬ ይህን በምናነብበት ሰአት 1 ህጻንን ጨምሮ 14 ሰዋች ሽኮ ዞን  በጉራ ፈርዳ ተገለዋል።በቃ እንድንለምደው ተፈልጓል ማለት ነው? ትንሽ ነው የሞተው?ከሚኖረው አይበልጥም?
የፈረንሳዩ ፕሬዝዳንት ኢማኑኤል ማክሮን በጀግኖች ክብር ቦታ መምህር ሳሙኤልን አሳርፈዋል።ከህዝቡ እኩል አልቅሰዋል።ጂሀዲስቶች ላይ እርምጃ መውሰድ ጀምረዋል።
የኛ ነብስ ከአንድ ፈረንሳዊ በምን ትለያለች?። የኛስ መሪ ከፈረንሳይ መሪ በምን ይለያል? ሰው ነው ሮቦት አይደለም።አንድ አላግባብ ለታረደ  ወገኑ የሚያለቅስ መሪ በቴቪዝን መስኮት እያየን በዛው ቴሊቪዝን መስኮት የሞቱት ካልሞቱት ያንሳሉ።”የሞቱት በቁጥር ከሚኖሩት አይበዙም” የሚል ቃል መስማት የሚዘገንን ነው።
ክቡር ጠ/ሚ አብይ ስንት አማራ ?ስንት ክርስቲያን መታረድ አለበት እርስዎ የችግሩን ክብደት አምነው እስኪቀበሉ።
እርስዎ ተአምር እንደሆኑ  እርስዎ ለኢትዯጵያ መድን እንደሆኑ ልማት እንደሆኑ 24/7 የኢትዮጵያ ቴሊቪዥን የፋና ሬድዮና ቴሌቪዥን    እይጨቀጨቁን ነው። ልክ እንደወያኔ ጊዜ። የኢትዮጲያ ቴልቪዥን ለ100 አመታት ባካበተው የውሸት ልምዱ ለ100 አመታት ባካበተው ለመንግስት የመወገን ልምዱ።ልክ እንደ መለስ ዜናዊ ታላቁ መሪ የልማት መሪ የሰላም መሪ እየተባሉ ነው።የሚገርመው ግን እየሞተ እየተገደለ ካለው ድሀ ህዝብ የተሰበሰበ ግብር ነው የኢትዮጵያ ቴሌ ቭዥን ሰራተኞች ደመወዝ የሚከፈላቸው።ከርስዎ ኪስ አይደለም።ለነዚ ጋዜጠኞች ስንት ሰው ቢሞት ይበቃል? የትኛው ብሄር? የትኛው ሀይማኖት?
ከእንጦጦ አራት ኪሎ ከአባሻውል ጅማ በመመላልስ በአህዮቹ የባህርዳር የአማራ ኢሊቶች ካባ መልበስ እና መሞገስ መሬት ላይ ያለውን እውነት አይቀይርም።መንግስት ለዜጎቹ የሚሰጠው የመጀመሪያ ትንሹ ነገር የመኖር ዋስትና ነው።የደህንነት ዋስትና ነው።
እየተገደሉ ያሉ ኢትዮጵያውያን ምናልባት ለእርስዎ አንዱ ከለላው ይለይ ይሆን እንዴ? ።ፊንጨአ ላይ ባደረጉት ንግግር የኦሮሞ ደም ከዚ በኋላ አይፈስም ብለዋል። የሌላውስ? ክቡር ጠ/ሚ እርስዎኮ የሁሉም መሪ ነዎት።ያለማቋረጥ በመጨፍጨፍ ላይ ያለው አማራስ? በቃ ላለመገደል ሲል ኦሮሞ መሆን አለበት?
እውነቱ ሲነገር በተለመደው የውሽት ቴሊቪዥን ጣቢያ ብቅ ይሉና በብሄር እየቅሰቅሱት ይላሉ። በህይማኖት እይቀስቅሱት ይላሉ።ነገር ግን ድርጊቱን ለማስቆም ቀርቶ ለማውገዝ እንኳ ደፍረው አያውቁም።
“የሞተው ካልሞተው ትንሽ ነው” “የሞተው ካልሞተው አይበዛም” ከአንድ መሪ ምን የሚሉት ንግግር ሊባል ይችላል??

Filed in: Amharic