>
5:28 pm - Saturday October 10, 6978

አንቱታው ይቅር (መስፍን አረጋ)

አንቱታው ይቅር

 

መስፍን አረጋ 


ይህች አጭር አስተያየት የተከተበቸው ዐብይ አህመድን በጨዋ ደንብ አንቱ/እሳቸው እያሉ ለሚጠሩ የኢትዮ360 ባልደረቦችን ለመሳሰሉ ሕብረ ብሔራዊ ጦቢያውያን ነው፡፡  ጨዋነት የጦቢያዊነት መለያ ባሕሪ ነው፣ ይልቁንም ደግሞ ነበር፡፡  ጨዋነት ትርጉም የሚኖረው ግን ለጨዋ ብቻ ነው፡፡  ማር ላህያ አይጥማትም፡፡

ዐብይ አህመድ ደግሞ ከወያኔ ጋር ተናንቆ ለስልጣን ያበቃውን ሰፊውን አልኦሮሞ የጦቢያ ሕዝብ አይንቁ ንቀት የናቀ ስድ ከመሆኑ በላይ፣ እኔን ብትነኩ መቶ ሺወች ይታረዳሉ በማለት ቅንጣት ሳይሰቀጥጠው በኩራት መንፈስ የተናገረ፣ በአራጅ ቄሮወች የሚተማመን ኦነጋዊ አረመኔ ነው፡፡  

በቡራዩ፣ በሻሸመኔ፣ በመተከል፣ ወዘተ. ለተፈጸሙት ዘር ተኮር ጭፍጨፋወች በቀጥታም ሆነ በተዛዋሪ ዋናው ተጠያቂ፣ ለማስመሰል ያህል እንኳን አዘኔታውን መግልጽ ያልፈለገው ኦነጋዊው ዐብይ አህመድ ነው፡፡  አልኦሮሞ ጦቢያውያንን በተመለከተ፣ ኦነጋዊው ዐብይ አህመድ ያስፈጸመው ፋሽስቱ ቤኒቶ ሙሶሊኒ ካስፈጸመው እጅግ የከፋ ነው፡፡  ፋሽስቱ ሙሶሊኒ አንቱ እንዳይባል፣ ይህም ከሞሶሊኒ እጅግ የከፋ ኦነጋዊ አረመኔ አንቱ መባል የለበትም፡፡ 

ዐብይ አህመድ በጦቢያ ፍርስራሽ ላይ የኦሮሙማን አጼጌ ለመገንባቶ ቆርጦ የተነሳ፣ ቀንደኛው የጦቢያ ጠላት ነው፡፡  ማናቸውም ጠላት ደግሞ በቅድሚያ መጠቃት ያለበት በማንነቱ በኩል በመግባት ነው፡፡  በተለይም ደግሞ ጠላትን በከበሬታ በመጥራት ሰብእናውን ከፍ ማድረግ ከመደገፍ ይቆጠራል፡፡

የጦቢያ ሕዝብ ሲያከብረው አልከበርም ያለው፣ ከበሬታ የማይወድለት፣ ክብረቢሱ ዐብይ አህመድ፣ አንቱ/እሳቸው ቢሉት የፈሩት እንጅ ያከበሩት ስለማይመስለው፣ ይህን ኦነጋዊ አረመኔ አንቱ/እሳቸው ማለት ይቁም፡፡       

 

ዐበይ አህመድ አሊ የኦነጉ ኦቦ

አፉና ምግባሩ ሐራምባና ቆቦ፡፡

በዲስኩሩ አክብረን ብናወጣው ላይጌ

በምግባሩ ዘቅጦ ወረደ እታችጌ

ተነስ አይባልም ክብረቢስ ባለጌ፡፡    

 

Filed in: Amharic