>
5:13 pm - Wednesday April 19, 2305

የኢሳት ብልፅግናዊ ቲያትር!!! (ምናላቸው ስማቸው)

የኢሳት ብልፅግናዊ ቲያትር!!!

ምናላቸው ስማቸው

ኢሳትን በተመለከተ ሰሞኑን በፌስ ቡክ ገፄ ይፋ ያደረግኩት መረጃ ብዙ አወንታዊ እና አሉታዊ አስተያየቶችን እንዳስተናገደ ተመልክቻለሁ::
ያም ተባለ ይህ ግን መረጃው እውነት ስለመሆኑ ኢሳትም ሆነ ጭፍሮቹ እራሳቸው ስላረጋገጡልኝ ጉዳዩን እንደገና ለማንሳት ተገድጃለሁ::
ኢሳት ከአየር ላይ የወረደው በገንዘብ እጥረት ቢሆን ኖሮ በዚህ አጭር ጊዜ ውስጥ አየር ላይ ይመለስ ነበር? በምንም አይነት አይመለስም::
ምክንያቱም በGoFundMe በኩል 3,000 እና 2000 USD በኮታ ተሰባስቦ የገባውም ሆነ በየዋህነት የተለገሰው ጠቀም ያለው የኢሳት ገንዘብ በአጭር ጊዜ እንደማይለቀቅ እናውቃለንና!
ገንዘቡ under review ተብሎ ሳይለቀቅ ቢያንስ ስንት ቀናቶች በGoFundMe me ውስጥ እንደሚቆይ ከልምዳችን እውቀቱ አለን::
ኢሳት ውሉ ተሰርዞ ከወረደ በኃላ እንደገና ወደ አየር ለመመለስ  ቢያንስ የቅድሚያና የተወሰነ ወራት የሳታላይት የኪራይ ገንዘብ መክፈል ያስፈልገዋል:: አዲስ አበባ
ያለው ወጭም የትየሌሌ ነው::
ይህ ከሆነ ገንዘቡን GoFundMe ሳይለቅ በድጋፍ እና በፋይናንስ እጥረት ውረድኩ ያለው ኢሳት ከየት አግኝቶ በአጭር ቀናት  ሊከፍልና ወደ አየር ሊመለስ ቻለ?
– ኢዜማ – ግንቦት 7 እንደለመደው ለኢሳት በድጋሚ ከግብፅ እንዲመደብ አደረገን?
– ብልፅግና በፈረንሳዩ ካምፓኒ በኩል ያመቻቸው 5 ሚሊዮን ዶላር ለኢሳት ተለቀቀ እንዴ?
– ወይንስ ከልማታዊነት ወደ ብልፅግና  የተሸጋገሩት ባለሀብቶች የኢሳት ገበታ ተመቻቸላቸው?
እውነቱ በእጃችን ስለሆነ ውስጡን
ለቄስ ብለን አንተወውም::
እስኪ ሌላው ቢቀር የሚከተለውን
——————————
የህግ ጥያቄ መልሱልን?
——————————
ኢሳት ላለፉት 10 ዓመታት የህዝብ ገንዘብ ሲሰበስብ ኦዲት ተደርጎ ያውቃል? አበበ ገላው ይመስክር!
ኢሳት በኢትዮጵያ የተመዘገበው Share company ሆኖ በንግድ ድርጅትነት እንደሆነ እናውቃለን::
የንግድ ድርጅት ደግሞ Civic organization ስላልሆነ የሕዝብ እርዳታ መስብሰብ አይችልም::
በኢትዮጵያ በበጎ አድራጎት Agency የተመዘገቡ ሀገር በቀል የእርዳታ ድርጅቶች 10% ከውጭ 90% ከሀገር ውስጥ እርዳታ መቀበል ብቻ እንደሚችሉ የኢትዮጵያ ህግ ይደነግጋል::
Esat Share company በኢትዮጵያ የንግድ ድርጅት ሆኖተመዝግቦ እያለ እንዴት የህዝብ ገንዘብ መሰብሰብ ቻለ?
አስራት  ሚዲያ በዚህ ሰበብ በኢትዮጵያ አልተመዘገበም ተብሎ ለጊዜውም ቢሆን ከጨዋታ ውጭ እንዲሆን መደረጉ
የተዘነጋ ይመስላችኃል?
ለኢሳት የተፈቀደ  ለአስራት ሚዲያ  የተከለከለው ሸፍጥ በእጃችን ስለሆነ ዝርዝሩን በሌላ ጊዜ እንመለስበታለን::
ይህን  ተጨፈኑ ላሞኛችሁ የኢሳት ብልፅግናዊ ቲያትር እየሞገትን መቀጠል እንችላለን::
ስለጠየቃችሁኝ የአማራ ጠልነት ስልታዊ ቁርኝቱም ቢሆን ማስረጃዎች ስላሉኝ  ማቅረብ እችላለሁ::
በመጨረሻም !!!
————–
ዛሬ በጉራ ፈርዳ እና በምስራቅ ወለጋ በመንግስት መዋቅር ሰሞኑን ስለተጨፈጨፉት ወገኖቼ ሞት ከእንግዲህ ወዲያ መርዶ ነጋሪ መሆንን አልመርጥም ::
ኢሳት ዛሬ በጉራ ፈርዳ ዜጎች ተገደሉ ብሎ አልዘገበም እንዴ?
እኔ ግን ሀዘኔን አልገልፅም!!ሞታቸውን በመዘገብ ብቻም አልመለስም::
በዚህ አጋጣሚ መቼም ቢሆን የማይበርደውን ንዴቴን ግን እንድታውቁልኝ እፈልጋለሁ::
መፍትሄውም አሁን ተገልጦልኛል::
ከመርዶ ነጋሪነት ይልቅ  ወደ ድል አብሳሪነት መሸጋገር !! Strategic leadership and Action!
No more የአማራ ብልፅግና የፓርቲ ጨዋታ!!
ጠብቁ !! የቀን ጉዳይ ነው!!
በከፍታው ላይ እንገናኛለን::
ወደ ክብራችንም እንመለሳለን::
እንድንጠፋ እየተሴረበት ያለው አማራነታችንም ኢትዮጵያዊነታችንም ዳግም በትግላችን ይለመልማል!!
Filed in: Amharic