>

ጠ/ሚ/ር  አብይ:- "ከማንዴላ ወደ  አባዱላ" ? (ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ)

ጠ/ሚ/ር  አብይ:- “ከማንዴላ ወደ  አባዱላ” ?

ታምሩ ገዳ/ህብር ራዲዮ

ጠ/ሚ/ር  አብይ አህመድ የዛሬ ሁለት አመት ወደ ስልጣን በመጡበት ወቅት ከተሰጣቸው የታላቅ መሪነት እርከን ወደ “አምባገነነት እያሽቆለቆሉ” ናቸው የሚሉ ተቺዎች ተበራክተዋል ተባለ።
የአሜሪካው ብሮድካስቲንግ  ኮርፖሬሽን  (ABC) ዛሬ  እንደ ዘገበው  ወደ ስልጣን  በመጡ  ማግስት ለህዝቡ እና ለአለማቀፉ ማህበረሰብ  በሰጡት መልካም  ተስፋ  እና በወሰዷቸው የተለያዩ እርምጃዎች የተነሳ የአለም የሰላም ኖቤል ሽልማትን እስከ መሸለም  የበቁት  አብይ አህመድየቀድሞው  የደቡብ አፍሪካው  የነጻነት ታጋይ  እና  የመጀመሪያው ጥቁር ፕሬዜዳንት ከነበሩት ኒልሰን ማንዴላ  ጋር እስከ መነጻጸር  እንደደረሱ ያወሳው፣ “በርካታ ባለሙያዎች/ ኤክስፐርቶች እንዳወጉኝ” ያለው  ዜና ዘገባው
“የጠ/ሚ/ር አብይ  አቋማቸው ተንሸራቶ ፣ቃል የገቡበት ጉዳይ እንኳን ተቀልብሶ፣የዛሬ ሁለት አመት በፊት  የፖለቲካ እስረኞች ናቸው በማለት ከእስራት  ነጻ ያደረጓቸው  ሰዎችን ዳግም ወደ እስር ቤት እንዲወረወሩ አድርጓቸዋል፣ በሰላም ሒደቱ ሳቢያ ወደ አገር ቤት የመጡት ፖለቲከኞች ውስጥ የተወሰኑ ታስረዋል ዶ/ር አብይ  የፌደራል ብሄርተኙነቱ ስርአቱን ትተው አደገኛ አሃዳዊ  ፍልስፍናን ያቀነቅናሉ፣ በኮሮና ምክንያት  ገደብ የለሽ የምርጫ ጊዜ እንዲከሰት ፈቅደዋል ፣ አብይ አህመድ  ከኒልሰን ማንዴላ ደቀመዝሙርነት ወደ  ጉልቤ እና አምባገነንነት ተሽጋግረዋል የሚሏቸው ተበራክተዋል” ብሏል።
በአንድ ወቅት የጠ/ሚ/ር አብይ አህመድ ዋንኛ ደጋፊ  አድናቂ  እና የኖቤል ሽልማት  እንዲያገኙ መጣራቸውን የሚናገሩት  ፣ከቅርብ ጊዜያት ወዲህ ግን   በተቃርኖ ጎራ የሚገኙት  በለንደኑ የኬል  ዩኒቨርስቲ የህግ  መምህር የሆኑት ዶ/ር እዎል አሎ ቀዳም ሲል  የጠ/ሚ/ሩ  ራእይን ይደግፉ እንደ ነበር አውስተው” ለአብይ አህመድ የተሰጣቸው  አድናቆት እና ውዳሴ ህዝቡ ከነበረበት የተስፋ መቁረጥ  ሳቢያ  እና ከአፋቸው  ከሚወጡት አማላይ ቃላት  የተነሳ እንጂ፣ አብይ አህመድ ኢትዮጵያን ወደ ቀድሞው ኢምፔሪያል/አሃዳዉ  ዘመን ለመውሰድ ይጥራሉ፣ለስርአታቸው አልታዘዝም ያሏቸውን አብይ ያስራሉ ያሳስራሉ”በማለት ይወቅሳሉ።
በአሜሪካው የጆርጂያ  ጋዊኔት  ኮሌጅ  የፖለቲካ ሳይንስ መምህር የሆኑት ዶ/ር ዮሐንስ ገዳሙ  በበኩላቸው “አብይ አህመድ  የወረሱት በከፍተኛ ደረጃ   በጨቆና የታወቀ ስርአትን ነው ፣ አብይ አህመድ ዛሬም ቢሆን  አብረዎቸው ያሉት እነዚያ የቀድሞው ሬጅም ውጤቶች ጋር ነው።ጠ/ሚ/ሩ ኢትዮጵያን ወደ  ዲሞክራሲነት ስርዓት  አሸጋግራለሁ ማለታቸው  እንደተጠበቀ ሁሉ   ጠ/ሚ/ሩ  ዙሪያ ገባቸው ያሉት አማካሪዎቻቸው እና ግለሰቦች  ኢትዮጵያን እጅ ለእጅ  ተያይዘው የመምራት ክህሎቱ ባለቤቶች ስለመሆናቸው   እጠራጠራለሁ” ብለዋል።
የጠ/ሚ/ር አብይ አስተዳደር ከላይ በተሰነዙርት  አሰተያየቶች  ዙሪያ እስከ አሁን ድረስ የሰጠው  አስተያየት የለም።
Filed in: Amharic