>
5:28 pm - Wednesday October 9, 7061

የክብር ዶክተር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ...!!! (ሰለሞን ወረደ ቃል)


የክብር ዶክተር ሎሬት አርቲስት ለማ ጉያ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ…!!!

ሰለሞን ወረደ ቃል
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 16፣ 2013 (ኤፍ.ቢ.ሲ) ሰአሊ ሎሬት ሻምበል የክብር ዶክተር አርቲስት ለማ ጉያ ዛሬ ከዚህ አለም በሞት ተለዩ፡፡
የክብር ዶክተር አርቲስት ለማ ጉያ በህክምና ሲረዱ ቆይተው በተወለዱ በ92 ዓመታቸው ዛሬ ከዚህ አለም በሞት ተለይተዋል፡፡
አርቲስት ለማ ጉያ ላለፉት 65 ዓመታት ከ10 ሺህ በላይ ሥዕሎችን በፍየል ቆዳ ላይ በመሳል አድናቆትን ማትረፍ ችለዋል፡፡
ሥራዎቻቸውንም በቢሾፍቱ ከተማ በሚገኘው ለማ ጉያ የሥነ-ጥበብ ማዕከል ውስጥ ለጎብኝዎች ያሳዩ ነበር።
የቀብር ስነ ስርዓታቸው ሀሙስ በቢሾፍቱ የሚፈፀም መሆኑን ከቤተሰቦቻቸው ለመረዳት ችለናል፡፡
Filed in: Amharic