>

የትራምፕ ንቀት ላብይ አህመድ ገጸበረከት (መስፍን አረጋ)

የትራምፕ ንቀት ላብይ አህመድ ገጸበረከት 

 

የዶናልድ ትራምፕ ንግግር ለጦቢያውያን ትልቅ ንቀት ቢሆንም፣ ለዐብይ አህመድ ግን ትልቅ ገጸበረከት ነው፡፡  ገጸበረከትነቱም አብይ አህመድ በቀጥታና በተዛዋሪ በሚያካሂደው ዘር ተኮር ጭፍጨፋና አፓርታይዳዊ አስተዳደር ምሥረታ ሳቢያ የተነሳበትን ከፍተኛ ተቃውሞ አቅጣጫ ማስለወጫ ምክኒያት መሆኑ ነው፡፡ 

 ‹‹ኢትዮጵያ በፈጣሪዋ ታምና በሕዝቧ አንድነትና ጽናት የቆመች አገር ናት››፣ ‹‹ኢትዮጵያን ነክቶ በሰላም የኖረ የለም›› እና የመሳሰሉት ዐረፍተ ነገሮች የሚያነሆልሉት፣ ለጦቢያ ክብር ቀናኢ የሆነውን፣ በነጭና ባረብ መደፈርን ከትልቅ ውርደት የሚቆጥረውን የአማራን ሕዝብና የተዋሕዶን መዕምን እንደሆነ ዐብይ አህመድ ጠንቅቆ ያውቃል፡፡  ሌላው ቀርቶ የአማራ ሕዝብ የሚጸየፈውን፣ የብልጽግና መሪ ቃል የሆነውን ‹‹ሕዝቦች›› የሚለውን ቃል በመግለጫው ላይ ይልተጠቀመው ሥራየ ብሎ ነው፡፡     

ስለዚህም የዐብይ አህመድ መግለጫ ዶናልድ ትራምፕን መቃወሚያ የተቃውሞ መግለጫ ሳይሆን፣ ያማራን ሕዝብና የተዋሕዶን መዕምን መደለያ የድለላ መግለጫ ነው፡፡  ዐብይ አህመድን የዐባይ ግድብ ጉዳይ የሚያስጨንቀው ከሆነ፣ የሚያስጨንቀው ስፍረተሕዝብን (demography) በመቀየር ግድቡን የኦሮሙማውያን የግል ንብረት ለማድረግ ቀን ከሌት እየሠራ በመሆኑ ብቻና ብቻ ነው፡፡  ዐብይ አህመድ ‹‹ስንኖር ኢትዮጵያ፣ ስንሞት ኢትዮጵያዊ›› እያለ ጦቢያውያንን በማታለል ጦቢያን የሚገድል ሸፍጠኛለ ነው፡፡    

በመሆኑም፣ ሰፊው ያማራ ሕዝብና የተዋሕዶ መዕምን፣ ዐብይ አህመድ ማለት ንግግሩና ተግባሩ ፍየል ወዲያ ቅዝምዝም ወዲህ የሆኑ የአማራና የተዋሕዶ ቀንደኛ ጠላት መሆኑን መቸም ሳይዘነጋ፣ ከዚህ ኦነጋዊ ጠላት ጋር የሚያካሂደውን የሞት ሽረት ትግል አጠናክሮ መቀጠል አለበት፡፡ 

 

ዐብይ አህመድ አሊ የኦነጉ ኦቦ

አፉና ምግባሩ ሐራምባና ቆቦ፡፡

ያብይ አህመድ ሒሳብ፣ ኦነጋዊ ቀመር

በተግባር ቀንሶ፣ በወሬ መደመር፡፡ 

 

መስፍን አረጋ 

  mesfin.arega@gmail.com

Filed in: Amharic